የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 6/1 ገጽ 16
  • ምድር የተፈጠረችው በዓላማ ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ምድር የተፈጠረችው በዓላማ ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ ፕላኔታችን እንደምትተርፍ ቃል ገብቷል
    ንቁ!—2023
  • ፈጣሪ ለሰው ልጆች የሰጠው ዘላለማዊ ስጦታ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ሕይወት ያላት ፕላኔት
    ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው?
  • በዚህ የንቁ! እትም ላይ
    ንቁ!—2023
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 6/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ምድር የተፈጠረችው በዓላማ ነው?

አንድ ወጣት የተለያየ ቀለም ስላላቸው ፍጥረታት በማሰብ በተፈጥሮ ላይ ሲያሰላስል

ምድር የተፈጠረችው ለሰው ልጆች አስደሳች መኖሪያ እንድትሆን ነው

አንድ ወጣት የተለያየ ቀለም ስላላቸው ፍጥረታት በማሰብ በተፈጥሮ ላይ ሲያሰላስል

ምድር የተፈጠረችው ለሰው ልጆች አስደሳች መኖሪያ እንድትሆን ነው

ምድር ሕይወትን ለማኖር ፍጹም ተስማሚ ናት። ለሕይወት በጣም አስፈላጊ የሆነው ውኃ ምድር ላይ በብዛት ይገኛል። የምድር ጋደል ያለ አቀማመጥ እንዲሁም በራሷ ዛቢያ ላይም ሆነ በፀሐይ ዙሪያ መሽከርከሯ ውቅያኖሶች ቀዝቅዘው ወደ በረዶነት እንዳይለወጡ በሌላ በኩል ደግሞ ተነው እንዳያልቁ ለመከላከል ይረዳሉ። እንዲሁም የምድር ከባቢ አየርና መግነጢሳዊ መስክ ምድርን አደገኛ ከሆነ ጨረር ይጠብቋታል። በምድር ላይ ያለው እርስ በርስ የተሳሰረ የዕፅዋትና የእንስሳት ሕይወትም ቢሆን በጣም አስደናቂ ነው። በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ምድር የተፈጠረችው በዓላማ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል።—ኢሳይያስ 45:18⁠ን አንብብ።

ይሁን እንጂ ‘መከራና የፍትሕ መጓደል የዚህ ዓላማ ክፍል ናቸው?’ ብለህ ታስብ ይሆናል።—ዘዳግም 32:4, 5⁠ን አንብብ።

ለምድር የታሰበው ዓላማ ይፈጸም ይሆን?

ምድር የተፈጠረችው እርስ በርሳቸው ለሚከባበሩና ፈጣሪያቸውን ለሚወዱ ሰዎች አስደሳች መኖሪያ እንድትሆን ነበር። የሰው ልጆች ሕይወት ከዕፅዋትም ሆነ ከእንስሳት ሕይወት የላቀ ዓላማ አለው። ምክንያቱም እኛ ፈጣሪያችን ማን እንደሆነ ማወቅ የምንችል ሲሆን የእሱን ፍቅርና ፍትሕ ልናደንቅ ብሎም በእነዚህ ባሕርያቱ ልንመስለው እንችላለን።—መክብብ 12:13⁠ን እና ሚክያስ 6:8⁠ን አንብብ።

ፈጣሪያችን ዓላማውን ሁሉ ከግብ ማድረስ ይችላል። በመሆኑም ወደፊት መከራንና የፍትሕ መጓደልን እንደሚያስወግድ እንዲሁም ምድርን ለሰው ዘር አስደሳች መኖሪያ እንደሚያደርጋት እርግጠኞች መሆን እንችላለን።—መዝሙር 37:11, 29፤ ኢሳይያስ 55:11⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 3 ተመልከት

www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ