የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 1/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እንስሳት
    ንቁ!—2015
  • እንስሳት ወደ ሰማይ ይሄዳሉ?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • አምላክ ለእንስሳት ያስባል?
    ንቁ!—2011
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 1/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ብዙ ሰዎች ፈጣሪ መኖሩን እንዲያምኑ ያደረጋቸው ምንድን ነው?

አንዲት እናት ልጇን በአድናቆት ስትመለከት

ሕይወት በራሱ ተአምር ነው

ከ3,000 ዓመታት በፊት አንድ ገጣሚ “ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁ” በማለት ጽፎ ነበር። (መዝሙር 139:14) አንድ ሕፃን በእናቱ ማሕፀን ውስጥ ከአንዲት ቅንጣት ሴል ተነስቶ እድገት የሚያደርግበትን መንገድ ስታስብ አትደነቅም? ብዙ ሰዎች፣ ሕይወት ያላቸው ነገሮች እንዲገኙ ያደረገው ፈጣሪ እንደሆነ ያምናሉ።—መዝሙር 139:13-17⁠ን እና ዕብራውያን 3:4⁠ን አንብብ።

አጽናፈ ዓለምን የፈጠረውና ምድርን ለመኖሪያነት ምቹ አድርጎ ያዘጋጀው አካል ሕይወት ያላቸው ነገሮችንም ፈጥሯል። (መዝሙር 36:9) ከዚህም በተጨማሪ ፈጣሪ ለሰው ልጆች ስለ ራሱ ተናግሯል።—ኢሳይያስ 45:18⁠ን አንብብ።

ሰዎች የመጡት ከእንስሳት ነው?

አካላችን በብዙ መንገድ ከእንስሳት አካል ጋር ይመሳሰላል። ይህ የሆነው ግን ፈጣሪ ሰዎችንም ሆነ እንስሳትን የፈጠረው በምድር ላይ እንዲኖሩ አስቦ ስለሆነ ነው። ፈጣሪ የመጀመሪያውን ሰው የፈጠረው ከእንስሳ ሳይሆን ከአፈር ነው።—ዘፍጥረት 1:24⁠ን እና 2:7⁠ን አንብብ።

ሰዎች ከእንስሳት የሚለዩባቸው ሁለት ዋና ዋና መንገዶች አሉ። አንደኛ፣ ሰዎች ፈጣሪያቸውን የማወቅ፣ የመውደድና የማክበር ችሎታ አላቸው። ሁለተኛው ደግሞ ሰዎች የተፈጠሩት ለዘላለም እንዲኖሩ ሲሆን እንስሳት የተፈጠሩት ግን ለዘላለም እንዲኖሩ አይደለም። አሁን ግን ሁሉም ሰዎች ይሞታሉ፤ ምክንያቱም ሁሉም የተገኙት የፈጣሪን መመሪያ ለመቀበል እምቢተኛ ከሆነው ከመጀመሪያው ሰው ነው።—ዘፍጥረት 1:27⁠ን እና 2:15-17ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 1 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ