የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 8/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ ለእኛ ያለው ዓላማ ምንድን ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ጥያቄ 1፦ ሕይወቴ ዓላማ አለው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 8/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ሕይወት ይህ ብቻ ነው?

አንድ ትልቅ ሰውና አንድ ትንሽ ልጅ ፊት ለፊት ሲመለከቱ

አንዳንድ ጊዜ ሕይወት በጣም አጭር እንደሆነ ይሰማሃል?

‘ሕይወት ሲባል መጫወት፣ መሥራት፣ ትዳር መመሥረት፣ ልጅ መውለድ እንዲሁም ማርጀት ብቻ ነው?’ ብለህ ጠይቀህ ታውቃለህ? (ኢዮብ 14:1, 2) መጽሐፍ ቅዱስ ጠቢብ የነበሩ ሰዎችም እንኳ ይህ ጉዳይ ያሳስባቸው እንደነበር ይናገራል።—መክብብ 2:11⁠ን አንብብ።

ታዲያ ሕይወት ከዚህ ያለፈ ትርጉም አለው? በቅድሚያ ግን ሕይወት ራሱ እንዴት ጀመረ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ማግኘት አለብን። ብዙዎች አንጎላችንና ሌሎች የአካል ክፍሎቻችን የተሠሩበትን አስደናቂ መንገድ ከተመለከቱ በኋላ ከዚህ ሁሉ በስተ ጀርባ ጠቢብ የሆነ ፈጣሪ መኖር አለበት ወደሚለው መደምደሚያ ደርሰዋል። (መዝሙር 139:14⁠ን አንብብ።) ይህ ከሆነ ደግሞ ፈጣሪ እኛን የፈጠረበት ዓላማ አለው ማለት ነው! ይህን ዓላማ ማወቃችን ሕይወታችን ትርጉም እንዲኖረው ያደርጋል።

የሰው ልጆች የተፈጠሩበት ዓላማ ምንድን ነው?

አምላክ የመጀመሪያዎቹን ጥንዶች የባረካቸው ሲሆን አስደሳች ሥራም ሰጥቷቸው ነበር። በመሆኑም እነሱን የፈጠረበት ዓላማ ምድርን እንዲሞሉ፣ ገነት እንዲያደርጉና ለዘላለም እንዲኖሩ ነበር።—ዘፍጥረት 1:28, 31⁠ን አንብብ።

የሰው ልጆች በአምላክ አገዛዝ ላይ በማመፃቸው የአምላክ ዓላማ በወቅቱ ሊፈጸም አልቻለም። ሆኖም አምላክ ለሰው ልጆችም ሆነ ለምድር ያለውን ዓላማ አልቀየረም። መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ለማዳን እንዲሁም ለምድር ያለውን ዓላማ ዳር ለማድረስ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጫ ይሰጣል! ስለሆነም አምላክ መጀመሪያ አስቦት የነበረውን ዓይነት ሕይወት እንድታጣጥም ይፈልጋል። (መዝሙር 37:29⁠ን አንብብ።) አንተም ይህ የአምላክ ዓላማ ሲፈጸም ተጠቃሚ መሆን የምትችለው እንዴት እንደሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ መማር ትችላለህ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የሚል ርዕስ ያለውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 3 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ