የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 3/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ ማክበር ያለብን እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • የጌታ እራት ይከበር የነበረው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ‘ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 3/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የኢየሱስን ሞት ማስታወስ ያለብን ለምንድን ነው?

ሰዎች ገነት በሆነችው ምድር ላይ በደስታ ሲኖሩ

የኢየሱስ ሞት ወደፊት የትኞቹ ተስፋዎች እውን እንዲሆኑ ያደርጋል?—ኢሳይያስ 25:8፤ 33:24

በታሪክ ውስጥ ከተከሰቱት ነገሮች ሁሉ ትልቁ የኢየሱስ ሞት ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ የሞተው የሰው ልጆች ያሉበት ሁኔታ ወደ ቀድሞው እንዲመለስ ለማድረግ ሲል ነው። ሰዎች ሲፈጠሩ መጥፎ ነገሮችን የማድረግ ዝንባሌ አልነበራቸውም፤ እንዲሁም አይታመሙም ወይም አይሞቱም ነበር። (ዘፍጥረት 1:31) ነገር ግን ኃጢአት በመጀመሪያው ሰው በአዳም በኩል ወደ ዓለም ገባ። ኢየሱስ እኛን ከኃጢአትና ከሞት ለማዳን ሲል የራሱን ሕይወት ሰጥቷል።—ማቴዎስ 20:28⁠ን እና ሮም 6:23⁠ን አንብብ።

አምላክ ልጁን ወደ ምድር በመላክ እንዲሞትልን ማድረጉ ለእኛ ታላቅ ፍቅር እንዳለው ያሳያል። (1 ዮሐንስ 4:9, 10) ኢየሱስ፣ ተከታዮቹ ቂጣና የወይን ጠጅ በመጠቀም ቀለል ባለ መንገድ የእሱን ሞት እንዲያስታውሱ አዝዞ ነበር። በየዓመቱ እሱ ባዘዘው መንገድ ሞቱን ማስታወሳችን አምላክና ኢየሱስ ላሳዩን ፍቅር አድናቆታችንን የምንገልጽበት አንዱ መንገድ ነው።—ሉቃስ 22:19, 20⁠ን አንብብ።

ከቂጣውና ከወይን ጠጁ መካፈል ያለባቸው እነማን ናቸው?

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ሞቱን እንዲያስታውሱ መጀመሪያ በተናገረበት ወቅት ስለ አንድ ቃል ኪዳን ወይም ውል ተናግሮ ነበር። (ማቴዎስ 26:26-28) ይህ ቃል ኪዳን ለእነሱና የተወሰነ ቁጥር ላላቸው ሌሎች ሰዎች ከኢየሱስ ጋር በሰማይ ነገሥታትና ካህናት የመሆን አጋጣሚ ከፍቷል። የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ የሚያከብሩት ሰዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቢሆኑም ከቂጣውና ከወይን ጠጁ የሚካፈሉት ግን በቃል ኪዳኑ ውስጥ የታቀፉት ብቻ ናቸው።—ራእይ 5:10⁠ን አንብብ።

ይሖዋ ወደ 2,000 ለሚጠጉ ዓመታት ያህል ነገሥታት የሚሆኑትን ሰዎች ሲመርጥ ቆይቷል። (ሉቃስ 12:32) በምድር ላይ በገነት ውስጥ የመኖር ተስፋ ካላቸው ሰዎች ጋር ሲነጻጸር የእነዚህ ሰዎች ቁጥር ጥቂት ነው።—ራእይ 7:4, 9, 17⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 5 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ