የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 3/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ኢየሱስ የተሠቃየውና የሞተው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
  • ጥያቄ 2፦ ስሞት ምን እሆናለሁ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • የኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ለአንተ ምን ትርጉም አለው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 3/1 ገጽ 16
ገነት በሆነች ምድር ላይ ሰዎች ባሕር ዳርቻ ላይ ሲዝናኑ፤ ልጆች ደግሞ ሲዋኙ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የኢየሱስ ሞት የሚጠቅመን እንዴት ነው?

አምላክ ሰዎችን የፈጠረው ሕመምም ሆነ ሞት ሳይደርስባቸው በምድር ላይ ለዘላለም እንዲኖሩ አስቦ ነበር። ይሁን እንጂ የመጀመሪያው ሰው አዳም ፈጣሪን ባለመታዘዙ ለዘላለም የመኖር አጋጣሚውን አጣ። እኛም የአዳም ዘሮች እንደመሆናችን መጠን ከእሱ ሞትን ወርሰናል። (ሮም 5:8, 12፤ 6:23) እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ግን አዳም ያሳጣንን ነገር መልሰን እንድናገኝ ሲል ልጁን ኢየሱስን እንዲሞት ወደ ምድር ላከው።—ዮሐንስ 3:16ን አንብብ።

ኢየሱስ የሞተው የሰው ልጆች የዘላለም ሕይወት እንዲያገኙ ለማስቻል ነው። ሰዎች በምድር ላይ ለዘላለም በሚኖሩበት ጊዜ ሕይወት ምን ሊመስል እንደሚችል መገመት ትችላለህ?

የኢየሱስ ሞት የኃጢአት ይቅርታና ፍጻሜ የሌለው ሕይወት እንድናገኝ በር ከፍቷል። መጽሐፍ ቅዱስ እርጅና፣ በሽታና ሞት የሚወገድበት ጊዜ ሲመጣ በምድር ላይ ያለው ሕይወት ምን ሊመስል እንደሚችል ፍንጭ ይሰጠናል።—ኢሳይያስ 25:8⁠ን፣ ኢሳይያስ 33:24ን እና ራእይ 21:4, 5ን አንብብ።

የኢየሱስን ሞት ማሰብ የሚኖርብን እንዴት ነው?

ኢየሱስ፣ ቀለል ያለ ሥነ ሥርዓት በማዘጋጀት ሞቱን እንዲያስቡ በመጨረሻው ምሽት ላይ ለተከታዮቹ ነግሯቸዋል። የኢየሱስን ሞት በየዓመቱ በዚህ መንገድ ማሰባችን ኢየሱስና ይሖዋ የሰው ልጆችን ምን ያህል እንደሚወዱ ለማሰላሰል ያስችለናል።—ሉቃስ 22:19, 20ን እና 1 ዮሐንስ 4:9, 10ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 4 እና 5 ተመልከት

www.jw.org/am ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማውረድ ይቻላል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ