የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 6/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥሩ ወላጅ ለመሆን ምን ያስፈልጋል?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ልጆቻችሁ ይሖዋን እንዲወዱ አስተምሯቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ወላጆች፣ ልጆቻችሁ ይሖዋን እንዲወዱ እርዷቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • የቤተሰብህን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?—ክፍል 2
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 6/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ጥሩ ወላጅ ለመሆን ምን ያስፈልጋል?

አባትና ልጅ አንድን የውኃ ተርብ ሲመለከቱ

ልጅህ አምላክን እንዲወድ ታስተምረዋለህ?

እርስ በርስ የሚዋደዱና የሚከባበሩ ወላጆች ያሏቸው ልጆች በጥሩ ሁኔታ ያድጋሉ። (ቆላስይስ 3:14, 19) ጥሩ ወላጆች ልክ እንደ ይሖዋ አምላክ ልጆቻቸውን ይወዳሉ እንዲሁም ያሞግሷቸዋል።—ማቴዎስ 3:17⁠ን አንብብ።

የሰማዩ አባታችን አገልጋዮቹን ያዳምጣል እንዲሁም ለስሜቶቻቸው ትኩረት ይሰጣል። ወላጆችም የይሖዋን ምሳሌ በመከተል ልጆቻቸው የሚናገሩትን ማዳመጣቸው ተገቢ ነው። (ያዕቆብ 1:19) ወላጆች ልጆቻቸው የሚያሰሙትን ቅሬታ ጨምሮ ስሜታቸውን ሲገልጹ መስማት ይኖርባቸዋል።—ዘኁልቁ 11:11, 15⁠ን አንብብ።

ልጆቻችሁን ኃላፊነት የሚሰማቸው እንዲሆኑ አድርጋችሁ ማሳደግ የምትችሉት እንዴት ነው?

ወላጅ እንደመሆንህ መጠን መመሪያ የመስጠት ሥልጣን አለህ። (ኤፌሶን 6:1) በዚህ ረገድ አምላክ የተወውን ምሳሌ ተከተል። አምላክ ግልጽ ደንቦችን በማውጣትና ደንቦቹን መተላለፍ የሚያስከትለውን መዘዝ በመግለጽ ለልጆቹ ፍቅር እንዳለው አሳይቷል። (ዘፍጥረት 3:3) አምላክ ሰዎች እንዲታዘዙት ከማስገደድ ይልቅ ትክክል የሆነውን ነገር ማድረጋቸው ምን ጥቅም እንደሚያስገኝላቸው ያስተምራቸዋል።—ኢሳይያስ 48:18, 19⁠ን አንብብ።

ልጆችህ አምላክን እንዲወዱ የመርዳት ግብ ይኑርህ። እንዲህ ካደረግክ ከአንተ ጋር በማይሆኑበት ጊዜም ጭምር በጥበብ መመላለስ ይችላሉ። አምላክ፣ ራሱ ምሳሌ በመሆን እንደሚያስተምር ሁሉ አንተም ለልጆችህ ምሳሌ በመሆን አምላክን እንዲወዱት አስተምራቸው።—ዘዳግም 6:5-7⁠ን፤ ኤፌሶን 4:32⁠ን እና 5:1⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 14 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ