የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 12/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • በአእምሯችን ለሚጉላሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው?
    በአእምሯችን ለሚጉላሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው?
  • ለቤተሰቦች የሚሆን ተጨማሪ እርዳታ
    ንቁ!—2018
  • መከራ የማይኖርበት ጊዜ ይመጣል?
    መከራ የማይኖርበት ጊዜ ይመጣል?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 12/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ልጆች አምላክን እንዲወዱ ማስተማር የሚቻለው እንዴት ነው?

አንድ ወላጅ ተፈጥሮን እያሳየ ልጁን ሲያስተምር

ልጆቻችሁ አምላክን እንዲያውቁትና እንዲወዱት ለመርዳት በተፈጥሮ ላይ የሚታዩ ነገሮችን ተጠቅማችሁ አስተምሯቸው

አንድ ወላጅ ተፈጥሮን እያሳየ ልጁን ሲያስተምር

ልጆቻችሁ አምላክን እንዲያውቁትና እንዲወዱት ለመርዳት በተፈጥሮ ላይ የሚታዩ ነገሮችን ተጠቅማችሁ አስተምሯቸው

ልጆቻችሁ አምላክን ሊወዱ የሚችሉት አምላክ መኖሩንና ለእነሱም ፍቅር እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካገኙ ብቻ ነው። ልጆች አምላክን እንዲወዱት ከተፈለገ ስለ እሱ ማወቅ ይኖርባቸዋል። (1 ዮሐንስ 4:8) ለምሳሌ ያህል፣ ‘አምላክ ሰውን የፈጠረበት ዓላማ ምንድን ነው? አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው? አምላክ ወደፊት ለሰው ልጆች ምን ያደርግላቸዋል?’ ስለሚሉት ጉዳዮች ማወቅ አለባቸው።—ፊልጵስዩስ 1:9⁠ን አንብብ።

ልጆቻችሁ አምላክን እንዲወዱት ለመርዳት እናንተ ራሳችሁ እሱን እንደምትወዱት ልታሳዩአቸው ይገባል። ለአምላክ ያላችሁን ፍቅር ሲመለከቱ የእናንተን ምሳሌ መከተላቸው አይቀርም።—ዘዳግም 6:5-7⁠ን እና ምሳሌ 22:6⁠ን አንብብ።

የልጆቻችሁን ልብ መንካት የምትችሉት እንዴት ነው?

የአምላክ ቃል ኃይል አለው። (ዕብራውያን 4:12) በመሆኑም ልጆቻችሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን መሠረታዊ ትምህርቶች እንዲያውቁ እርዷቸው። ኢየሱስ የሚያስተምራቸውን ሰዎች ልብ ለመንካት ሲል ጥያቄዎችን ይጠይቃቸው፣ ያዳምጣቸው እንዲሁም ጥቅሶችን ያብራራላቸው ነበር። እናንተም የልጆቻችሁን ልብ ለመንካት የኢየሱስን የማስተማሪያ ዘዴዎች መኮረጅ ትችላላችሁ።—ሉቃስ 24:15-19, 27, 32⁠ን አንብብ።

በተጨማሪም አምላክ ከሰዎች ጋር ስለነበረው ግንኙነት የሚናገሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ልጆቻችሁ አምላክን እንዲያውቁትና እንዲወዱት ሊረዷቸው ይችላሉ። ለዚህ ዓላማ ተብለው የተዘጋጁ ጽሑፎችን www.jw.org/am በተባለው ድረ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል።—2 ጢሞቴዎስ 3:16⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 14 ተመልከት

መጽሐፉን www.jw.org/am ላይም ማግኘት ይቻላል፤ ወይም ደግሞ በገጽ 2 ከተገለጹት አድራሻዎች ወደ አንዱ በመጻፍ መጽሐፉ በነፃ እንዲላክልህ መጠየቅ ትችላለህ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ