የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 9/1 ገጽ 7
  • የምንሰብከው ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የምንሰብከው ለምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለቤተሰቦች የሚሆን ተጨማሪ እርዳታ
    ንቁ!—2018
  • በአእምሯችን ለሚጉላሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው?
    በአእምሯችን ለሚጉላሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው?
  • መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት እገዛ ማግኘት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—JW.ORGን መጠቀም
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 9/1 ገጽ 7
ሁለት የይሖዋ ምሥክሮች በአንድ የመኖሪያ አካባቢ ሲሰብኩ

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | የይሖዋ ምሥክሮች እነማን ናቸው?

የምንሰብከው ለምንድን ነው?

ከቤት ወደ ቤት፣ በአደባባይና ሰዎች በሚገኙበት ቦታ ሁሉ የምናከናውነው ሰፊ የስብከት ሥራ በዋነኝነት ተለይተን የምንታወቅበት ተግባር ነው። የምንሰብከው ለምንድን ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች የሚሰብኩት አምላክ እንዲከበርና ስሙ እንዲታወቅ ስለሚፈልጉ ነው። (ዕብራውያን 13:15) በተጨማሪም ክርስቶስ ኢየሱስ ‘ሂዱና ከሁሉም ብሔራት ሰዎችን ያዘዝኳችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው’ በማለት የሰጠውን ትእዛዝ ማክበር ስለምንፈልግ ነው።—ማቴዎስ 28:19, 20

ከዚህም ሌላ ሰዎችን ሁሉ እንወዳለን። (ማቴዎስ 22:39) እርግጥ ነው፣ አብዛኞቹ ሰዎች የራሳቸው እምነት እንዳላቸውና መልእክታችንን መስማት የሚፈልገው ሁሉም ሰው እንዳልሆነ እንገነዘባለን። ያም ሆኖ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ሕይወት እንደሚያስገኝ እናምናለን። ከዚህም የተነሳ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች እንዳደረጉት ሁሉ ‘ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን ምሥራች ያለማሰለስ ማስተማራችንንና ማወጃችንን’ እንቀጥላለን።—የሐዋርያት ሥራ 5:41, 42

የሥነ ኅብረተሰብ ጥናት ባለሙያ የሆኑት አንቶኒዮ ኮቫ ማዱሮ “የይሖዋ ምሥክሮች በብዙ ጥረትና ልፋት፣ ጉልበታቸውን ምንም ሳይቆጥቡ . . . የቅዱስ ጽሑፉን መልእክት እስከ ምድር ዳር ድረስ አዳርሰዋል” በማለት ጽፈዋል።—ኤል ኡኒቨርሳል ጋዜጣ፣ ቬንዙዌላ

ጽሑፎቻችንን የሚያነቡ አብዛኞቹ ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች አይደሉም። እንዲሁም ከእኛ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን የሚያጠኑ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ናቸው። ይሁንና የይሖዋ ምሥክሮች ወደ ቤታቸው መጥተው ስለሚያነጋግሯቸው አመስጋኞች ናቸው።

እርግጥ፣ የይሖዋ ምሥክሮችን በተመለከተ ሌሎች ጥያቄዎችም ሊኖሩህ ይችላሉ። ከሆነ በሚከተሉት መንገዶች መልሶቹን ማግኘት ትችላለህ፦

  • የይሖዋ ምሥክሮችን በመጠየቅ።

  • www.jw.org ድረ ገጻችንን በመጎብኘት።

  • ክፍያ በማይጠየቅባቸውና ለሁሉም ሰው ክፍት በሆኑት ስብሰባዎቻችን ላይ በመገኘት።

ኢየሱስ እንዲሰብኩ ሁለት ደቀ መዛሙርትን ሲልክ
አናቱ በበረዶ የተሸፈነ ተራራ

የይሖዋ ምሥክሮችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት www.jw.org ላይ የይሖዋ ምሥክሮች—ምሥራቹን ለመስበክ የተደራጀ ሕዝብ የሚለውን ረጅም የቪዲዮ ፊልም ተመልከት። (የሕትመት ውጤቶች > ቪዲዮዎች በሚለው ሥር ይገኛል)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ