የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 9/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአምላክ መንግሥት ተቋቁሟል!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • መጽሐፍ ቅዱስ—ትክክለኛ ታሪክና አስተማማኝ ትንቢት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ተማሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • መጽሐፍ ቅዱስ—ትክክለኛ ትንቢት የያዘ መጽሐፍ፣ ክፍል—7
    ንቁ!—2012
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 9/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

መጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ ትንቢት መያዙ ምን ያሳያል?

በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ኢየሱስ ከአንዳንድ ሐዋርያቱ ጋር እየተነጋገረ

መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በዘመናችን ስለሚፈጸሙ ክስተቶች የተጻፈው ለምንድን ነው?—ሉቃስ 21:10, 11

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዝርዝር የሰፈሩ ብዙ ትንቢቶች ይገኛሉ። ወደፊት የሚፈጸሙ ነገሮችን በዝርዝር መተንበይ የሚችል ሰው የለም። በመሆኑም የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ፍጻሜ ማግኘታቸው መጽሐፉ የአምላክ ቃል እንደሆነ አሳማኝ ማስረጃ ነው።—ኢያሱ 23:14⁠ን እና 2 ጴጥሮስ 1:20, 21⁠ን አንብብ።

ፍጻሜ ያገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች በአምላክ ለማመን ጠንካራ መሠረት ይሆኑናል። (ዕብራውያን 11:1) በተጨማሪም አምላክ ወደፊት የተሻለ ጊዜ እንደሚመጣ የሰጣቸው ተስፋዎች እንደሚፈጸሙ እርግጠኞች እንድንሆን ያደርጉናል። በመሆኑም የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት የተረጋገጠ ተስፋ እንዲኖረን ያስችላል።—መዝሙር 37:29⁠ን እና ሮም 15:4⁠ን አንብብ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች የሚጠቅሙን እንዴት ነው?

አንዳንድ ትንቢቶች የአምላክ አገልጋዮች እርምጃ እንዲወስዱ ማስጠንቀቂያ ይዘዋል። ለምሳሌ ያህል፣ የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች አንዳንድ ትንቢቶች መፈጸማቸውን ሲያዩ ኢየሩሳሌምን ለቀው ወጥተዋል። አብዛኛው የኢየሩሳሌም ሕዝብ ኢየሱስን ባለመቀበሉ ከተማዋ ከጊዜ በኋላ ስትጠፋ ክርስቲያኖች ከአካባቢው ርቀው ሰላም በሰፈነበት ስፍራ ላይ ይገኙ ነበር።—ሉቃስ 21:20-22⁠ን አንብብ።

ፍጻሜ ካገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች መረዳት እንደምንችለው የአምላክ መንግሥት በቅርቡ ሰብዓዊ መንግሥታትንና መስተዳድሮችን ጠራርጎ ያጠፋል። (ዳንኤል 2:44፤ ሉቃስ 21:31) ስለሆነም እያንዳንዱ ሰው አምላክ የሾመውን ንጉሥ ይኸውም የኢየሱስ ክርስቶስን ሞገስ ለማግኘት አሁኑኑ አጣዳፊ እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል።—ሉቃስ 21:34-36⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የሚል ርዕስ ያለውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 5 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ