መጽሐፍ ቅዱስ—ትክክለኛ ታሪክና አስተማማኝ ትንቢት
መጽሐፍ ቅዱስ ከታሪክ አንጻር ትክክል እንደሆነ የሚያሳዩ ምን ማስረጃዎች አሉ? መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ትንቢቶች ወደፊት እንደሚፈጸሙ እርግጠኛ እንድንሆን የሚያደርጉን ከዚህ በፊት የተፈጸሙ የትኞቹ ትንቢቶች ናቸው? የእነዚህ ጥያቄዎች መልስ መጽሐፍ ቅዱስ—የእውነትና የትንቢት መጽሐፍ የተባለው ዲቪዲ ከያዛቸው ሦስት ፊልሞች መካከል መጽሐፍ ቅዱስ—ትክክለኛ ታሪክና አስተማማኝ ትንቢት በሚለው በሦስተኛው ክፍል ውስጥ ይገኛል። ፊልሙን ከተመለከታችሁ በኋላ ቀጥሎ ለቀረቡት ጥያቄዎች መልስ ስጡ።
(1) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው አስተማማኝ መረጃ ምንጭ ማን ነው? (ዳን. 2:28) (2) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጥንቷ ግብጽ ምን ትክክለኛ መረጃ ይዟል? በኢሳይያስ 19:3, 4 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው ትንቢት የተፈጸመው እንዴት ነው? (3) መጽሐፍ ቅዱስ አሦራውያንን፣ የአሦርን ንጉሥና የአሦርን ጥፋት የገለጸበት መንገድ ትክክል እንደነበር የአርኪኦሎጂ ግኝቶች ያረጋገጡት እንዴት ነው? (ናሆም 3:1, 7, 13) (4) ከባቢሎን ጋር በተያያዘ የትኞቹ ትንቢቶች ትክክለኛ መሆናቸው ተረጋግጧል? (ኤር. 20:4፤ 50:38፤ 51:30) (5) ከሜዶ ፋርስ ጋር በተያያዘ የትኛው ትንቢት በትክክል ተፈጽሟል? (ኢሳ. 44:28) (6) ዳንኤል 7:6 እና 8:5, 8 ከግሪክ ጋር በተያያዘ ፍጻሜያቸውን ያገኙት እንዴት ነው? (7) ሮም የዓለም ኃያል መንግሥት ሆና ስትነሳ ዳንኤል 7:7 ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? (8) በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱት የትኞቹ ቄሳሮች ናቸው? (9) በኔሮ የግዛት ዘመን በክርስቲያኖች ላይ ምን ደርሶባቸዋል? (10) በራእይ 13:11 እና 17:10 ላይ የሚገኙት ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን ያገኙት እንዴት ነው? (11) ስምንተኛው ንጉሥ ተለይቶ የሚታወቀው በምንድን ነው? (12) በቪዲዮው ውስጥ የመክብብ 8:9ን እውነተኝነት የሚያረጋግጥ ምን ነገር ተመለከትክ? (13) የትኞቹ ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን ሲያገኙ ለመመልከት ትጓጓለህ? (14) መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ ምንጭ እንዳለው ለሰዎች ለማስረዳት ይህንን ቪዲዮ እንዴት ልትጠቀምበት ትችላለህ?