መጽሐፍ ቅዱስ—ትክክለኛ ታሪክና አስተማማኝ ትንቢት ከሚለው የቪዲዮክርትምህርት ማግኘት
ይህን ቪዲዮ ካየህ በኋላ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ ትችላለህ? (1) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለሚገኘው አስተማማኝ እውቀት ምንጩ ማን ነው? (ዳን. 2:28) (2) መጽሐፍ ቅዱስ የጥንቷን ግብፅ እንዴት አድርጎ በትክክል ገልጿታል? በኢሳይያስ 19:3, 4 ላይ የተነገረው ትንቢት ፍጻሜ ያገኘው እንዴት ነው? (3) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አሦራውያን፣ ስለ ነገሥታቶቻቸው እንዲሁም ስለ አሦር መጥፋት የሚናገረው ታሪክ እውነት መሆኑን የአርኪኦሎጂ ጥናት ያረጋገጠው እንዴት ነው? (ነህ. 3:1, 7, 13) (4) ባቢሎንን አስመልክቶ የተነገሩት የየትኞቹ ትንቢቶች እውነተኝነት ተረጋግጧል? (5) ሜዶ ፋርስ በአምላክ ሕዝቦች ላይ ምን ተጽዕኖ አሳድሯል? (6) በዳንኤል 8:5, 8 ላይ የሚገኘው ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? ትንቢቱ የተነገረው ከመፈጸሙ ከስንት ዓመት በፊት ነው? (7) ኢየሱስ እውነተኛው መሲሕ መሆኑን ያረጋገጠው እንዴት ነው? (8) በራእይ 13:11 እና 17:11 ላይ የሚገኙት ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን ያገኙት በየትኞቹ የዘመናችን የፖለቲካ ኃይሎች ነው? (9) ቪዲዮው መክብብ 8:9 ላይ የተነገረው አባባል እውነት መሆኑን ያረጋገጠው እንዴት ነው? (10) ቪዲዮው መጽሐፍ ቅዱስ ስለወደፊቱ ጊዜ በሚናገረው ተስፋ ላይ ያለህን እምነት ያጠነከረልህ እንዴት ነው? (11) መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ ምንጭ ያለው መጽሐፍ እንደሆነ ሌሎችን ለማሳመን ይህን ቪዲዮ እንዴት ልትጠቀምበት ትችላለህ?