የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp16 ቁጥር 2 ገጽ 16
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዲያብሎስ ማን ወይም ምንድን ነው?
  • ዲያብሎስ ሰዎችን መቆጣጠር ይችላል?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ኢየሱስ እንዳደረገው “ዲያብሎስን ተቃወሙት”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ዲያብሎስ አፈ ታሪክ የወለደው አይደለም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ሰይጣንን ተቃወሙት፣ ከእናንተም ይሸሻል!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
wp16 ቁጥር 2 ገጽ 16
ኢየሱስ የሰይጣንን ፈተና ሲቃወም

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

ዲያብሎስ ማን ወይም ምንድን ነው?

ምን ትላለህ? ዲያብሎስ . . .

  • መንፈሳዊ አካል ነው?

  • በሰዎች ውስጥ ያለ ክፋት ነው?

  • ሰዎች በምናባቸው የፈጠሩት ነገር ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ዲያብሎስ ኢየሱስን አነጋግሮታል፤ እንዲሁም ‘ፈትኖታል።’ (ማቴዎስ 4:1-4) ስለዚህ ዲያብሎስ በምናብ የተፈጠረ ነገር ወይም የክፋት ሐሳብ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ክፉ የሆነ መንፈሳዊ አካል ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • በመጀመሪያ ዲያብሎስ ቅዱስ መልአክ ነበረ፤ ነገር ግን “በእውነት ውስጥ ጸንቶ አልቆመም።” (ዮሐንስ 8:44) ሐሰተኛ ከመሆኑም ሌላ በአምላክ ላይ ዓመፀ።

  • ሌሎች መላእክትም ከሰይጣን ጋር በመተባበር በአምላክ ላይ ዓመፁ።—ራእይ 12:9

  • ዲያብሎስ፣ ስለ እሱ መኖር እንዳያውቁ ብዙዎችን አሳውሯል።—2 ቆሮንቶስ 4:4

ዲያብሎስ ሰዎችን መቆጣጠር ይችላል?

አንዳንዶች ምን ይላሉ? ‘ዲያብሎስ ሰዎችን ይቆጣጠራል’ የሚባለው ነገር ማታለያ እንደሆነ የሚሰማቸው አሉ፤ ሌሎች ደግሞ ክፉ መናፍስት እንዳይቆጣጠሯቸው በጣም ይፈራሉ። አንተ ምን ይመስልሃል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“መላው ዓለም . . . በክፉው ቁጥጥር ሥር ነው።” (1 ዮሐንስ 5:19) ዲያብሎስ በሰው ዘር ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድር ቢሆንም እያንዳንዱን ሰው ይቆጣጠራል ማለት ግን አይደለም።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • ዲያብሎስ በሰዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ለማሳደር ሲል ማታለያዎችን ይጠቀማል።—2 ቆሮንቶስ 11:14

  • ክፉ መናፍስት አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን ይቆጣጠራሉ።—ማቴዎስ 12:22

  • በአምላክ እርዳታ፣ ዲያብሎስን ‘መቃወም’ ትችላለህ።—ያዕቆብ 4:7

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የሚል ርዕስ ያለውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 10 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ