መግቢያ
ምን ይመስልሃል?
አምላክ ከሰጠን ስጦታዎች ሁሉ የሚበልጠው ስጦታ የትኛው ይመስልሃል?
መጽሐፍ ቅዱስ “አምላክ ዓለምን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ . . . አንድያ ልጁን ሰጥቷል” ይላል።—ዮሐንስ 3:16
ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም አምላክ፣ ኢየሱስ ወደ ምድር እንዲመጣና ለእኛ ሲል እንዲሞት ያደረገው ለምን እንደሆነ እንዲሁም ለዚህ ስጦታ ያለንን አድናቆት ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።