የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp17 ቁጥር 2 ገጽ 3-4
  • ወደር የሌለው ስጦታ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወደር የሌለው ስጦታ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከሁሉ የላቀው የአምላክ ስጦታ—ውድ የሆነበት ምክንያት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • ከሁሉ የላቀው ስጦታ ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • ኢየሱስ ክርስቶስ—መልእክቱ ለአንተ ምን ትርጉም አለው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ቤዛው—ከሁሉ የላቀ የአምላክ ስጦታ
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
wp17 ቁጥር 2 ገጽ 3-4
አንድ ሽማግሌ ለአንድ ትንሽ ልጅ የጀልባ ቅርጽ ያለው መቅረጫ ሲሰጠው

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | ከሁሉ የላቀውን የአምላክ ስጦታ ትቀበላለህ?

ወደር የሌለው ስጦታ

ጆርዳን የያዘው የጀልባ ቅርጽ ያለው የእርሳስ መቅረጫ ምንም የተለየ ነገር ያለው አይመስልም። ለጆርዳን ግን ትልቅ ቦታ አለው። ጆርዳን “የቤተሰባችን ወዳጅ የሆኑት ራስል በጣም ትንሽ ልጅ ሳለሁ የሰጡኝ ስጦታ ነው” በማለት ተናግሯል። አያቱ እና ወላጆቹ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በነበሩበት ወቅት እኚህ ሰው ረድተዋቸው ነበር፤ ጆርዳን ይህን ያወቀው ራስል ከሞቱ በኋላ ነው። እንዲህ ሲል ተናግሯል፦ “አሁን ስለ ራስል በደንብ ስላወቅኩ ይህን ትንሽ ስጦታ ከቀድሞው የበለጠ ከፍ አድርጌ እመለከተዋለሁ።”

የጆርዳን ምሳሌ እንደሚያሳየው አንድ ስጦታ ለሌሎች ሰዎች እምብዛም ቦታ ላይኖረው ይችላል። ተቀባዩ ግን አድናቆት ስላለው ስጦታው ለእሱ ውድ አልፎ ተርፎም በዋጋ የማይተመን ሊሆን ይችላል። በብዙዎች ዘንድ የሚታወቅ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በዋጋ ሊተመን ስለማይችል አንድ ስጦታ ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “አምላክ ዓለምን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ በልጁ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ ሲል አንድያ ልጁን ሰጥቷል።”—ዮሐንስ 3:16

ይህ ስጦታ ለተቀባዩ የዘላለም ሕይወት ያስገኛል! ከዚህ የሚበልጥ ስጦታ ሊኖር ይችላል? አንዳንዶች ይህ ስጦታ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው አይገነዘቡም፤ እውነተኛ ክርስቲያኖች ግን ይህን ስጦታ የሚመለከቱት እንደ “ውድ” ነገር ነው። (መዝሙር 49:8፤ 1 ጴጥሮስ 1:18, 19) ለመሆኑ አምላክ የልጁን ሕይወት ለመላው ዓለም ስጦታ አድርጎ የሰጠው ለምንድን ነው?

ሐዋርያው ጳውሎስ መልሱን እንደሚከተለው በማለት ተናግሯል፦ “በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ፤ . . . [ሞትም] ለሰው ሁሉ ተዳረሰ።” (ሮም 5:12) የመጀመሪያው ሰው አዳም ሆን ብሎ የአምላክን ትእዛዝ በመጣስ ኃጢአት ስለሠራ የሞት ቅጣት ተፈረደበት። በአዳም አማካኝነት ደግሞ ሞት ለዘሮቹ ሁሉ ማለትም ለሁሉም የሰው ልጆች ተዳረሰ።

“የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነውና፤ አምላክ የሚሰጠው ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው።” (ሮም 6:23) አምላክ የሰውን ዘር ከሞት ባርነት ለማላቀቅ ሲል ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ እንዲሰጥ ወደ ምድር ላከው። “ቤዛ” ተብሎ በሚታወቀው በዚህ መሥዋዕት አማካኝነት በኢየሱስ ላይ እምነት ያላቸው ሁሉ የዘላለም ሕይወት ማግኘት ይችላሉ።—ሮም 3:24

ጳውሎስ፣ አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ለአገልጋዮቹ ስለሚሰጠው በረከት ሲናገር “በቃላት ሊገለጽ ለማይችለው ነፃ ስጦታው አምላክ የተመሰገነ ይሁን” ብሏል። (2 ቆሮንቶስ 9:15) በእርግጥም ቤዛው እጅግ አስደናቂ ከመሆኑ የተነሳ በቃላት ሊገለጽ አይችልም። ይሁንና ቤዛው፣ አምላክ ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ስጦታዎች ሁሉ የላቀ ነው የምንለው ለምንድን ነው? ይህን ስጦታ የተለየ የሚያደርገው ምንድን ነው?a ለዚህ ስጦታ ያለንን አድናቆት ማሳየት የምንችለውስ እንዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ በቀጣዮቹ ሁለት ርዕሶች ላይ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

a ኢየሱስ በፈቃደኝነት ‘ሕይወቱን ለእኛ አሳልፎ ሰጥቷል።’ (1 ዮሐንስ 3:16) ይሁንና ይህ መሥዋዕት የአምላክ ዓላማ በመሆኑ እነዚህ ተከታታይ ርዕሶች በዋነኝነት የሚያተኩሩት ቤዛውን ባዘጋጀው አካል ማለትም በአምላክ ላይ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ