የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp17 ቁጥር 4 ገጽ 16
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ጭንቀትን እንድትቋቋም ሊረዳህ ይችላል?
  • ጭንቀት የሚወገድበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?
  • ጭንቀትህን ሁሉ በይሖዋ ላይ ጣል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • የሚያስጨንቃችሁን ነገር ሁሉ በይሖዋ ላይ ጣሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • ጭንቀት
    ንቁ!—2016
  • በወንዶች ላይ የሚከሰት ጭንቀት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን የመፍትሔ ሐሳብ ይሰጣል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
wp17 ቁጥር 4 ገጽ 16
አንድ ቤተሰብ በገነት ውስጥ

በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር ሰዎች ‘በብዙ ሰላም እጅግ ደስ ይላቸዋል።’—መዝሙር 37:11

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

መጽሐፍ ቅዱስ ጭንቀትን እንድትቋቋም ሊረዳህ ይችላል?

ምን ብለህ ትመልሳለህ?

  • አዎ

  • አይ

  • እኔ እንጃ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“የሚያስጨንቃችሁንም ነገር ሁሉ [በአምላክ] ላይ ጣሉ፤ ምክንያቱም እሱ ስለ እናንተ ያስባል።” (1 ጴጥሮስ 5:7) መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ ከሚያስጨንቁህ ነገሮች ሁሉ እፎይታ እንድታገኝ ሊረዳህ እንደሚችል ማረጋገጫ ይሰጣል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • በጸሎት አማካኝነት ‘የአምላክን ሰላም’ ማግኘት ትችላለህ፤ ይህ ደግሞ ጭንቀትህን ለማቅለል ይረዳሃል።—ፊልጵስዩስ 4:6, 7

  • በተጨማሪም የአምላክን ቃል ማንበብ ውጥረት የሚፈጥሩ ሁኔታዎችን እንድትቋቋም ሊረዳህ ይችላል።—ማቴዎስ 11:28-30

ጭንቀት የሚወገድበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

አንዳንዶች ምን ብለው ያምናሉ? ጭንቀትና ውጥረት የሕይወታችን ክፍል እንደሆኑ አድርገው የሚያስቡ ሰዎች አሉ። ከጭንቀት የምንገላገለው ስንሞት ብቻ ነው ብለው ያምናሉ። አንተስ ምን ይመስልሃል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አምላክ ለጭንቀት መንስኤ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ ያስወግዳል። “ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።”—ራእይ 21:4

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • የአምላክ መንግሥት ምድርን በሚገዛበት ወቅት ሰዎች በሰላምና በጸጥታ ይኖራሉ።—ኢሳይያስ 32:18

  • ጭንቀትና ውጥረት የተረሱ ነገሮች ይሆናሉ።—ኢሳይያስ 65:17

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 3 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ