የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp17 ቁጥር 5 ገጽ 7-8
  • መላእክት ሊረዱህ የሚችሉት እንዴት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መላእክት ሊረዱህ የሚችሉት እንዴት ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መላእክት የጥንቱን የክርስቲያን ጉባኤ ረድተዋል
  • መላእክት አንተን ሊረዱህ የሚችሉት እንዴት ነው?
  • መላእክት ሊረዱህ የሚችሉት እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • መላእክት በሕይወታችን ውስጥ ምን ሚና ይጫወታሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • መላእክት—“የሕዝብ አገልጋዮች የሆኑ መናፍስት”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ከአምላክ መላእክት የሚገኝ እርዳታ
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
wp17 ቁጥር 5 ገጽ 7-8

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክት ምን ይላል?

መላእክት ሊረዱህ የሚችሉት እንዴት ነው?

ታማኝ መላእክት ከሰው ልጆች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በትኩረት የሚከታተሉ ሲሆን የይሖዋን ፈቃድ በትጋት ያስፈጽማሉ። አምላክ ምድርን በፈጠረበት ጊዜ መላእክት ‘በአንድነት እልል ብለዋል እንዲሁም በደስታ ጮኸዋል።’ (ኢዮብ 38:4, 7) መላእክት ከጥንት ጀምሮ፣ በምድር ላይ የሚፈጸሙ ክንውኖችን አስመልክቶ የተነገሩ ትንቢቶችን ፍጻሜ “ለማየት” ከፍተኛ ጉጉት ነበራቸው።—1 ጴጥሮስ 1:11, 12

መላእክት ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መልኩ ለእውነተኛ የአምላክ አገልጋዮች ጥበቃ ያደረጉባቸው ጊዜያት እንዳሉ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (መዝሙር 34:7) ለምሳሌ ያህል፦

  • ይሖዋ በክፋት የተሞሉትን ሰዶምና ገሞራን ባጠፋበት ወቅት ሎጥና ቤተሰቡ ከጥፋቱ መትረፍ እንዲችሉ መላእክት ረድተዋቸዋል።—ዘፍጥረት 19:1, 15-26

  • በጥንቷ ባቢሎን የነበሩት ሦስት ዕብራውያን ወጣቶች በእቶን እሳት ውስጥ በተጣሉበት ጊዜ አምላክ “መልአኩን ልኮ አገልጋዮቹን [ታድጓቸዋል]።”—ዳንኤል 3:19-28

  • ጻድቅ ሰው የነበረው ዳንኤል በተራቡ አንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ተጥሎ አንድ ሌሊት ካሳለፈ በኋላ በአንበሶች ከመበላት የተረፈው እንዴት እንደሆነ ሲናገር “አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ” ብሏል።—ዳንኤል 6:16, 22

አንድ መልአክ ዳንኤልን በአንበሶች ከመበላት ጠብቆታል

መላእክት ከጥንት ጀምሮ የአምላክን ታማኝ ሕዝቦች ረድተዋል

መላእክት የጥንቱን የክርስቲያን ጉባኤ ረድተዋል

መላእክት የአምላክ ፈቃድ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ የጥንቱ የክርስቲያን ጉባኤ ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች እርዳታ ሰጥተዋል። ለምሳሌ ያህል፦

  • አንድ መልአክ ሐዋርያት ታስረው የነበሩበትን እስር ቤት በሮች ከፍቶ ካስወጣቸው በኋላ በቤተ መቅደስ መስበካቸውን እንዲቀጥሉ ነግሯቸዋል።—የሐዋርያት ሥራ 5:17-21

  • አንድ መልአክ ወንጌላዊው ፊልጶስን ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚወስደው የበረሃ መንገድ እንዲሄድ ትእዛዝ ሰጥቶታል፤ ይህን ያደረገው ለአምልኮ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ በመመለስ ላይ ለነበረ አንድ ኢትዮጵያዊ እንዲሰብክለት ነው።—የሐዋርያት ሥራ 8:26-33

  • አምላክ አይሁዳውያን ያልሆኑ ሰዎች ክርስትናን እንዲቀበሉ የሚፈቅድበት ጊዜ ሲደርስ አንድ መልአክ ለሮማዊው መቶ አለቃ ለቆርኔሌዎስ በራእይ ተገልጦለት ሐዋርያው ጴጥሮስን ወደቤቱ እንዲያስጠራ መመሪያ ሰጥቶታል።—የሐዋርያት ሥራ 10:3-5

  • ሐዋርያው ጴጥሮስ ታስሮ በነበረበት ወቅት አንድ መልአክ መጥቶ ከእስር ቤት አውጥቶታል።—የሐዋርያት ሥራ 12:1-11

መላእክት አንተን ሊረዱህ የሚችሉት እንዴት ነው?

አምላክ ሰዎችን በተአምራዊ መንገድ ለመርዳት በመላእክት እንደተጠቀመ የሚገልጹ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ቢኖሩም በዛሬው ጊዜም ተመሳሳይ ነገር እንደሚያደርግ የሚያሳይ ማስረጃ የለም። ሆኖም ኢየሱስ የእኛን ዘመን አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ “ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24:14) የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ይህን ሥራ የሚሠሩት በመላእክት አመራር ሥር ሆነው እንደሆነ ታውቅ ነበር?

የአደባባይ ምሥክርነት በሚሰጥበት አካባቢ የሚተላለፉ ሰዎች

መላእክት ምሥራቹ በዓለም ዙሪያ እንዲታወጅ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ

የራእይ መጽሐፍ፣ መላእክት በምድር ዙሪያ ያሉ ሰዎች ስለ ይሖዋ አምላክና እሱ ለሰው ዘር ስላለው ዓላማ እንዲማሩ ለመርዳት በትጋት እንደሚሠሩ ይገልጻል። ሐዋርያው ዮሐንስ እንዲህ በማለት ጽፏል፦ “ሌላም መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤ እሱም በምድር ላይ ለሚኖር ብሔር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ሕዝብ ሁሉ የሚያበስረው የዘላለም ምሥራች ይዞ ነበር። እሱም በታላቅ ድምፅ ‘አምላክን ፍሩ፤ ክብርም ስጡት፤ ምክንያቱም የሚፈርድበት ሰዓት ደርሷል፤ በመሆኑም ሰማይን፣ ምድርን፣ ባሕርንና የውኃ ምንጮችን የሠራውን አምልኩ’ አለ።” (ራእይ 14:6, 7) በዛሬው ጊዜ መላእክት ለዓለም አቀፉ የስብከት ሥራ ድጋፍ እንደሚሰጡ የሚያሳዩ በርካታ ተሞክሮዎች አሉ። አንድ ኃጢአተኛ እንኳ ንስሐ ገብቶ ወደ ይሖዋ ሲመለስ “በአምላክ መላእክት ዘንድ ደስታ ይሆናል።”—ሉቃስ 15:10

የስብከቱ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላስ? የነገሥታት ንጉሥ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ “ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ታላቅ ቀን [በሚካሄደው] ጦርነት” ማለትም በአርማጌዶን ሲዋጋ በሰማይ ያሉት የመላእክት “ሠራዊቶች” አብረውት ይዋጋሉ። (ራእይ 16:14-16፤ 19:14-16) ጌታ ኢየሱስ “ስለ ጌታችን ኢየሱስ ለሚገልጸው ምሥራች በማይታዘዙት ላይ የበቀል እርምጃ” በሚወስድበት ጊዜ ኃያላን መላእክት የመለኮታዊ ፍርድ አስፈጻሚዎች ሆነው ያገለግላሉ።—2 ተሰሎንቄ 1:7, 8

ስለሆነም መላእክት በግለሰብ ደረጃ እንደሚያስቡልህ እርግጠኛ ሁን። መላእክት አምላክን ለማገልገል የሚፈልጉ ሰዎች ደህንነት በጣም ያሳስባቸዋል፤ በመሆኑም አምላክ በምድር ላይ ያሉ ታማኝ አገልጋዮቹን ለማበርታትና ለመጠበቅ በተደጋጋሚ በመላእክት ተጠቅሟል።—ዕብራውያን 1:14

እንግዲያው እያንዳንዳችን ወሳኝ ምርጫ ቀርቦልናል። በዓለም ዙሪያ እየታወጀ ያለውን ምሥራች ለመስማትና ለመታዘዝ ፈቃደኞች ነን? በአካባቢህ የሚኖሩት የይሖዋ ምሥክሮች የአምላክ ኃያላን መላእክት ከሚሰጡት ፍቅራዊ እርዳታ መጠቀም የምትችልበትን መንገድ በማሳየት ረገድ አንተን ለመርዳት ፈቃደኞች ናቸው።

መጽሐፍ ቅዱስ ታማኝ የሆኑና ታማኝ ያልሆኑ መላእክትን አስመልክቶ ምን እንደሚል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 10 ተመልከት። መጽሐፉን ለማግኘት jw.org/amን መመልከት ትችላለህ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ