የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w19 ጥር ገጽ 31
  • አዲስ የበላይ አካል አባል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አዲስ የበላይ አካል አባል
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አዲስ የበላይ አካል አባል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • አዲስ የተሾሙ የበላይ አካሉ አባላት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • አዲስ የአስተዳደር አካል አባላት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ሁለት አዳዲስ የበላይ አካል አባላት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
w19 ጥር ገጽ 31
ኬኔዝ ኩክና ባለቤቱ ጄሚ

ወንድም ኬኔዝ ኩክና ባለቤቱ ጄሚ

አዲስ የበላይ አካል አባል

ረቡዕ ጥር 24, 2018 በዩናይትድ ስቴትስና በካናዳ የሚገኙት የቤቴል ቤተሰብ አባላት ወንድም ኬኔዝ ኩክ የበላይ አካል አባል ሆኖ እንደተሾመ የሚገልጽ አስደሳች ማስታወቂያ ተነገራቸው።

ወንድም ኩክ ተወልዶ ያደገው በማዕከላዊ ደቡብ ፔንስልቬንያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ነው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ከማጠናቀቁ ከጥቂት ጊዜ በፊት፣ አብሮት ከሚማር አንድ ልጅ እውነትን ሰማ፤ ከዚያም ሰኔ 7, 1980 ተጠመቀ። መስከረም 1, 1982 የዘወትር አቅኚ በመሆን የሙሉ ጊዜ አገልግሎቱን ጀመረ። ለሁለት ዓመት በአቅኚነት ካገለገለ በኋላ ወደ ቤቴል ተጠራ። የቤቴል አገልግሎቱን የጀመረው ጥቅምት 12, 1984 በዎልኪል፣ ኒው ዮርክ ነበር።

ወንድም ኩክ በቀጣዮቹ 25 ዓመታት በሕትመት ክፍል እንዲሁም በቤቴል ቢሮ ውስጥ በተለያዩ የሥራ ምድቦች አገልግሏል። በ1996 ጄሚ ከተባለች እህት ጋር ትዳር መሠረተ፤ እሷም ቤቴል ገብታ በዎልኪል አብራው ማገልገል ጀመረች። ታኅሣሥ 2009 ወንድም ኩክና ባለቤቱ በፓተርሰን፣ ኒው ዮርክ ወደሚገኘው የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የትምህርት ማዕከል የተዛወሩ ሲሆን በዚያም ወንድም ኩክ በደብዳቤ ልውውጥ ክፍል ውስጥ እንዲያገለግል ተመደበ። ሚያዝያ 2016 ወንድም ኩክና ባለቤቱ ለአጭር ጊዜ ያህል ወደ ዎልኪል ከተመለሱ በኋላ ወደ ብሩክሊን፣ ኒው ዮርክ ተዛወሩ። ከአምስት ወር በኋላ በዎርዊክ፣ ኒው ዮርክ ወደሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ተዛውረው ማገልገል ጀመሩ። ጥር 2017 ወንድም ኩክ የበላይ አካሉ የጽሑፍ ዝግጅት ኮሚቴ ረዳት ሆኖ ተሾመ።

በአሁኑ ጊዜ የበላይ አካሉ የሚከተሉትን ስምንት በመንፈስ ቅዱስ የተቀቡ ወንድሞች ያቀፈ ነው፦

ኬኔዝ ኩክ፤ ሳሙኤል ኸርድ፤ ጄፍሪ ጃክሰን፤ ስቲቨን ሌት፤ ጌሪት ሎሽ፤ አንቶኒ ሞሪስ፤ ማርክ ሳንደርሰን፤ ዴቪድ ስፕሌን

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ