የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w19 የካቲት ገጽ 31
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምኩራቦች—ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ የሰበኩባቸው ቦታዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • መሰብሰባችሁን አትተዉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • ኢየሱስ በቅፍርናሆም ታላላቅ ሥራዎችን አከናወነ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • የክርስትና እምነት በመጀመሪያው መቶ ዘመን ለነበሩት አይሁዶች ተዳረሰ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
w19 የካቲት ገጽ 31

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በጋምላ የሚገኘው በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረ ምኩራብ

በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረ ምኩራብ፦ ይህ ሞዴል በመጀመሪያው መቶ ዘመን ከገሊላ ባሕር በስተ ሰሜን ምሥራቅ አሥር ኪሎ ሜትር ገደማ ርቆ በሚገኘው በጋምላ የነበረውን ምኩራብ አንዳንድ ገጽታዎች ያሳያል። ይህም በጥንት ዘመን የነበረው ምኩራብ ምን ሊመስል እንደሚችል እንድንገነዘብ ይረዳናል

በምኩራቦች መጠቀም የተጀመረው እንዴት ነው?

“ምኩራብ” የሚለው ቃል የመጣው “ስብሰባ” ወይም “ጉባኤ” የሚል ትርጉም ካለው የግሪክኛ ቃል ነው። ከጥንት ጀምሮ የአይሁድ ማኅበረሰብ ለመማርና አምልኮ ለማቅረብ በምኩራቦች ይሰበሰብ ስለነበር ለዚህ ቦታ እንዲህ ያለ ስያሜ የተሰጠው መሆኑ ተገቢ ነው። የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ስለ ምኩራቦች በቀጥታ አይናገሩም፤ ሆኖም የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት በግልጽ እንደሚያሳዩት በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም. ምኩራቦች ለመሰብሰቢያነት ያገለግሉ ነበር።

አብዛኞቹ ምሁራን ምኩራቦችን መጠቀም የተጀመረው አይሁዳውያን በግዞት ወደ ባቢሎን በተወሰዱበት ወቅት እንደሆነ ያምናሉ። ኢንሳይክሎፒዲያ ጁዳይካ እንዲህ ይላል፦ “አምልኮ የሚያቀርቡበት ቤተ መቅደስ ያልነበራቸውና በባዕድ አገር ይኖሩ የነበሩት ግዞተኞች ከጭንቀታቸው ለመጽናናት ሲሉ አልፎ አልፎ ምናልባትም በሰንበት ቀን ተገናኝተው ቅዱሳን መጻሕፍትን ያነብቡ ነበር።” አይሁዳውያኑ ከግዞት ነፃ ከወጡ በኋላም አንድ ላይ ተገናኝተው መጸለያቸውንና ቅዱሳን መጻሕፍትን ማንበባቸውን የቀጠሉ ይመስላል፤ ለዚህም ሲሉ በሰፈሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ምኩራቦችን ይሠሩ ነበር።

በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም. ምኩራቦች በሜድትራንያን፣ በመላው መካከለኛ ምሥራቅ፣ ሌላው ቀርቶ በእስራኤል ጭምር ለነበሩ አይሁዳውያን የሃይማኖትና የማኅበራዊ ሕይወት ማዕከል ሆኑ። በኢየሩሳሌም የሚገኘው የሂብሩ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ሊ ለቪን እንዲህ ብለዋል፦ “[ምኩራቦች] ለማጥናት፣ የተቀደሱ ምግቦችን ለመመገብ፣ ፍርድ ነክ ጉዳዮችን ለማከናወን፣ የጋራ ገንዘብ ለማስቀመጥ እንዲሁም ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ስብሰባዎችን ለማድረግ የሚያገለግሉ ቦታዎች ነበሩ።” አክለውም “በዋነኝነት ግን ሃይማኖታዊ አገልግሎቶችን ለማከናወን ይውሉ ነበር” በማለት ተናግረዋል። ከዚህ አንጻር ኢየሱስ አዘውትሮ ወደ ምኩራቦች ይሄድ የነበረ መሆኑ አያስገርምም። (ማር. 1:21፤ 6:2፤ ሉቃስ 4:16) ኢየሱስ በምኩራቦች ውስጥ ያስተምር፣ ይመክርና በዚያ የተገኙትን ያበረታታ ነበር። የክርስቲያን ጉባኤ ከተቋቋመ በኋላ ሐዋርያው ጳውሎስም ብዙ ጊዜ ወደ ምኩራቦች እየሄደ ይሰብክ ነበር። መንፈሳዊ ፍላጎት የነበራቸው ሰዎች በአብዛኛው ወደ ምኩራቦች ይሄዱ ነበር፤ በመሆኑም ጳውሎስ ወደ አንድ ከተማ ሲገባ በቅድሚያ ወደ ምኩራብ ሄዶ የመስበክ ልማድ ነበረው።—ሥራ 17:1, 2፤ 18:4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ