የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/93 ገጽ 1
  • ወጣቶች ሆይ፤ በጥበብ ተራመዱ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወጣቶች ሆይ፤ በጥበብ ተራመዱ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ወጣቶች ሆይ፣ የይሖዋን ልብ አስደስቱ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • አገልግሎትህን በተሟላ ሁኔታ እየፈጸምክ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ሚያዝያ—‘ጠንክረን የምንሠራበትና የምንጋደልበት’ ወር
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • መልካም ለማድረግ የምትቀኑ ሁኑ!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 5/93 ገጽ 1

ወጣቶች ሆይ፤ በጥበብ ተራመዱ

1 አባታችን ይሖዋ የወጣቶችን መንፈሳዊ ዕድገት ይከታተላል። ወጣቶች ጥበበኞች በመሆን ፍቅራዊ ትዕዛዛቱን ቢሰሙና ቢከተሉ የይሖዋን ልብ ከማስደሰታቸውም በላይ ለነፍሳቸውም ዕረፍት ያገኛሉ። (ምሳሌ 27:11፤ ማቴ. 11:28–30) ይሖዋ በጥበብ ለመራመድ የሚችሉበትን መመሪያ እንዲሰጣቸው ይፈቅዱለታል። — ምሳሌ 16:9

2 ክርስቶስ ኢየሱስ ወጣት በነበረበት ጊዜ በአምላክና በሰው ፊት ሞገስን በማግኘት በኩል ምሳሌ ትቷል። (ሉቃስ 2:52) በዛሬው ጊዜ ያሉ ወጣቶችም እንዲሁ ለማድረግ መጣር ይኖርባቸዋል። አንድ ወጣት በጥበብ እየተራመደ መሆኑ በሚከታተላቸው ነገሮች በግልጽ ሊታይ ይገባል። ኢየሱስ በ12 ዓመቱ ለሌሎች ስለ ይሖዋ ለመናገር በነበረው ፍላጎቱ የታወቀ ነበር። (ሉቃስ 2:46, 47) በዛሬው ጊዜ ያሉ ወጣቶችም እምነታቸውን ለሌሎች ለማስረዳት በመጣር ከዚህ ጋር የሚመሳሰል ፍላጎት አሳይተዋል። — መግ 13–111 ገጽ 29–30፤ የእንግሊዝኛ መግ 87 12/1 ገጽ 21

3 ወጣቶች ሆይ፣ በአሁኑ ጊዜ በተለይም በእረፍት ወራት ‘ይሖዋን በሀብታችሁ’ ለማክበር ምን ልታደርጉ ትችላላችሁ? (ምሳሌ 3:9) የምሥራቹን በመስበክና በማስተማር የምታሳልፉበትን ሰዓት ከሌላው ጊዜ የበለጠ ለምን ከፍ አታደርጉትም? ምናልባት ረዳት አቅኚ መሆን ትችላላችሁን? በአገልግሎቱ ይበልጥ በምትሳተፉበት ጊዜ የምታገኙት ከፍተኛ ደስታና ሌሎች ጥቅሞች ከምታስቡት በላይ ይሆንና ትደነቁ ይሆናል። በተጨማሪም በአገልግሎቱ ያላችሁን ተሳትፎ ከፍ ማድረጋችሁ ከብዙ የተለያዩ አስፋፊዎች ጋር በመስክ አገልግሎት የመሥራት አጋጣሚ ይሰጣችኋል። በፊታችን ባሉት ቅዳሜና እሁድ አብረዋችሁ እንዲያገለግሉ ልምድ ያላቸውን አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች በመጋበዝ አገልግሎታችሁን ከፍ ማድረጉን አሁንኑ ልትጀምሩ ትችሉ ይሆናል።

4 ወላጆችም ልጆቻቸውን ይዘው ወደ አገልግሎት ከመሄድ በተጨማሪ የልምምድ ፕሮግራሞችን በማድረግ ለልጆቻቸው ከፍተኛ ማበረታቻና ድጋፍ ሊሰጧቸው ይችላሉ። በጉባኤ ውስጥ ያሉ ሌሎች የጎለመሱ ወንድሞችም ወጣቶች ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎትና በተመላልሶ መጠየቅ እንዲሁም በቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ አብረዋቸው እንዲገኙ በመጋበዝ ረገድ እስኪጠየቁ ድረስ ሳይጠብቁ ራሳቸው ተነሳስተው ሊጠይቁ ይችላሉ። በመንፈሳዊ ጠንካሮች ከሆኑ እንዲህ ካሉ አስፋፊዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት ማድረግ ወጣቶችን ይገነባቸዋል፤ እንዲሁም “ወደ ጉልምስና” ለመድረስ ወደፊት እንዲጓዙ ይረዳቸዋል። — ዕብ. 6:1 አዓት

5 እያንዳንዱ ክርስቲያን የማስተማር ችሎታውን ማሻሻል ያስፈልገዋል። ወጣቶችም እንዲሁ እንዲያደርጉ ያስፈልጋቸዋል። እናንተ ወጣቶች በቲኦክራቲካዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ንግግር የመስጠት መብት ስታገኙ ክፍላችሁን በደንብ ትዘጋጁበታላችሁን? ለማንበብና የግል ጥናት ለማድረግ እንዲሁም ለማሰላሰል ቋሚ ፕሮግራም አውጥታችኋልን? ያነበባችሁት ትምህርት እናንተን እንዴት እንደሚመለከት ቶሎ ይታያችኋልን? ትምህርቱን ሙሉ በሙሉ እስክትረዱትና ሐሳብ ለመስጠት ዝግጁዎች ለመሆን እስከምትችሉበት ደረጃ ድረስ ለስብሰባዎች በደንብ ትዘጋጃላችሁን? በስብሰባዎች ላይ የሚሰጡትን ጠቃሚ ነጥቦች ልብ ብላችሁ ትከታተላላችሁን? በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚወጡትን የማሻሻያ ሐሳቦች ለመጠቀምስ ትሞክራላችሁን?

6 የመንግሥት አዳራሹን የማጽዳትና በዕድሜ የገፉትን ወይም አቅመ ደካማ የሆኑትን ወንድሞችንና እህቶችን በቤት ውስጥ ሥራ ወይም በሌሎች ተግባራዊ መንገዶች ለመርዳት የሚያስችሉ አጋጣሚዎች አይለፏችሁ። የመንግሥት አዳራሹን ወጪዎች ለመሸፈንና የማኅበሩን ዓለም አቀፋዊ ሥራ ለማገዝ አዘውትራችሁ በግላችሁ የእርዳታ መዋጮ ማድረጋችሁን አትዘንጉት።

7 ‘የይሖዋን ቃል ብንጠብቅና’ እርሱ እርምጃችንን እንዲያቀናልን ብንፈቅድለት ደስታና ተጨማሪ የአገልግሎት መብቶች እንድናገኝ ያስችለናል። — መዝሙር 119:9

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ