ልታደርጉት ትችላላችሁን?
1 ‘ምኑን?’ ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል። ምሳሌ 3:27 “ለተቸገረው ሰው በጎ ነገርን ማድረግ አትከልክል፣ ልታደርግለት የሚቻልህ ሲሆን” በማለት መልሱን ይሰጠናል። የአገልግሎት እንቅስቃሴያችሁን ማስፋትና በረዳት አቅኚነት ወይም በዘወትር አቅኚነት አገልግሎት መካፈል ‘ልታደርጉት የምትችሉት ነገር ነውን?’ ይህን ልታደርጉ ትችላላችሁን?
2 በ1993 የዓመት መጽሐፍ ላይ በምሥራቅ አፍሪካ 3,504 ረዳት አቅኚዎችና የዘወትር አቅኚዎች እንደነበሩ ማንበብ እንዴት የሚያበረታታ ነው። ይህም ከ5 አስፋፊዎች ውስጥ አንዱ አቅኚ ነበር ማለት ነው። አዎ፣ 652 አስፋፊዎች ወደ አቅኚነት አገልግሎት የገቡት ባለፈው ዓመት ነው። ይህም ሁኔታዎቻቸውን የመረመሩና በአገልግሎቱ ይበልጥ መሥራት እንደሚችሉ ያረጋገጡ በየቀኑ ሁለት አስፋፊዎች ነበሩ ማለት ነው።
3 ረዳት አቅኚ መሆን ለሌሎች መልካም የምናደርግበት አንዱ መንገድ ነው። ባለፈው ዓመት 3,430 የደረሰ ከፍተኛ የረዳት አቅኚዎች ቁጥር ነበር። ይህ በጣም ግሩም ነው። ብዙ አስፋፊዎች በዓመቱ ውስጥ በተደጋጋሚ ረዳት አቅኚዎች ሆነው የሚያገለግሉበትን መንገድ ሲፈልጉ ነበር።
4 ‘ልታደርገው የምትችል’ መሆንህንና አለመሆንህን ለመወሰን አስቀድመህ ልባዊ ፍላጎትህን መመርመር ያስፈልግሃል። (ማቴ. 22:37–39) ሥራ 20:35 “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው” ይላል። ከልብ በመነጨ ልግስና መንፈሳዊ እርዳታ የሚሰጡ ሰዎች ትክክለኛው ፍላጎት እንዳላቸው አያጠራጥርም። የተሳካለት አስፋፊ ወይም አቅኚ ለመሆን ይህ ፍላጎት መኖሩ በጣም ጠቃሚ ነው።
5 ሁለተኛ አሁን ያለህባቸውን ሁኔታዎች መርምር። በሙሉ ጊዜ ለማገልገል በዕለታዊ ጉዳዮችህ ላይ ማስተካከያዎችን ለማድረግ ትችላለህን? ይህን ማድረግ የሚችለው ሁሉም ሰው አይደለም። ነገር ግን ራሳቸውን በጸሎት ከመረመሩ በኋላ በየዓመቱ በሺህ የሚቆጠሩ ይህን ‘ለማድረግ’ ችለዋል። (ቆላ. 4:5፤ የእንግሊዝኛ መግ 77 ገጽ 701) ለምሳሌ ያህል አንዳንድ ቤተሰቦች አንዳንዶቹ ወይም ጠቅላላ የቤተሰቡ አባላት ረዳት አቅኚ እንዲሆኑ የተወሰኑ ወሮችን ይመርጣሉ። ሌሎች ቤተሰቦች ደግሞ አንዱ የቤተሰባቸው አባል የዘወትር አቅኚ እንዲሆን ሲሉ በሚያስፈልገው ሁሉ ይረዱታል። ቤተሰባችሁ እነዚህን ሁሉ አማራጭ መንገዶች አስቦባቸዋልን? — ምሳሌ 11:25 ተመልከት።
6 አስፋፊም ሆናችሁ አቅኚ ሌሎች እውነትን እንዲያውቁ መርዳት እውነተኛ እርካታ ያመጣላችኋል። እውነተኛ ደስታ የሚገኘው ለሌሎች መልካም ከማድረግ እንደሆነ እናውቃለን፤ በተለይ ‘ልናደርገው የሚቻለን ሲሆን።’