የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/94 ገጽ 1
  • ያለማሰለስ ከቤት ወደ ቤት መሄድ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ያለማሰለስ ከቤት ወደ ቤት መሄድ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከቤት ወደ ቤት የሚከናወነው አገልግሎት በአሁኑ ጊዜ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ መመሥከር
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • በአደባባይና ከቤት ወደ ቤት አስተምሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ምሥራቹን ያለማሰለስ ማወጅ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 7/94 ገጽ 1

ያለማሰለስ ከቤት ወደ ቤት መሄድ

1 በጥንቷ እስራኤል በየዕለቱ መሥዋዕቶች ይቀርቡ ነበር። (ዘጸ. 29:38-42) በመሠዊያው ላይ ሁልጊዜ እሳት እንዲነድድ ይደረግ ነበር። ወደ ላይ የሚወጣው ጭስም ይሖዋ አምላክን የሚያስደስት “ጣፋጭ ሽቱ” ነበር። (ዘጸ. 29:18)በዛሬው ጊዜ እኛ “ለእግዚአብሔር የምሥጋናን መሥዋዕት፣ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ” እንድናቀርብ በጥብቅ ተነግሮናል። (ዕብ. 13:15) እኛ ይሖዋ አምላክን የምናመልከው በሕጉ የታዘዙትን መሥዋዕቶች በማቅረብ ሳይሆን ያለማቋረጥ እርሱን የሚያወድሱ ቃላት በመናገር ነው።​—ኢሳ. 43:21፤ ሥራ 5:42

2 እስከዛሬ ድረስ በዚህች ምድር ላይ ከኖሩት ምሥክሮች ሁሉ የሚበልጠው ታላቁ ምሥክር ኢየሱስ ክርስቶስ የምስጋናን መሥዋዕት በማቅረብ ንጹሕ አምልኮ ልናካሂድ የምንችለው እንዴት እንደሆነ አስተምሮናል። የሚሰብኩት መልእክት አጣዳፊ መሆኑን ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሯቸዋል። ምሥራቹን ለሰዎች ለማዳረስ የሚያስችለው ከሁሉ የተሻለ ውጤታማ ዘዴ እቤታቸው ድረስ ሄዶ በግል ማነጋገር መሆኑን ያውቅ ነበር። (ማቴ. 10:7, 12) ሐዋርያቱም እርሱ የሰጣቸውን መለኮታዊ መመሪያ በመከተል ከቤት ወደ ቤት ሄደው ሰብከዋል።​—ሥራ 20:20

3 ዛሬም ሁኔታው አልተለወጠም። እውነተኛ ክርስቲያኖች የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ስለሆኑ ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ ምሥራቹን በመስበክ የእርሱን አርዓያ ይከተላሉ። እንዲህ በማድረጋችን ምክንያት ብንወገዝና ብንሰደድም በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እውነትን ማወቃቸውና በየዓመቱ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አዳዲስ ደቀ መዛሙርት ደግሞ የሚፈለግባቸውን ብቃት እያሟሉ ከእጅግ ብዙ ሰዎች ጋር መተባበራቸው ይሖዋ ፈቃዱን ለመፈጸም የሚጠቀምበት መንገድ ይህ ለመሆኑ ማስረጃ ይሆናል። በአገልግሎታችን ያለመሰልቸት የምንቀጥለው በዚህ ምክንያት ነው።

4 ከቤት ወደ ቤት መመስከር ያለው ጥቅም፦ “እግዚአብሔር ለሰው ፊት [አያደላም] . . . እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ” ነው። (ሥራ 10:34, 35) በአገልግሎት ክልላችን ውስጥ ወደሚገኘው ወደያንዳንዱ ቤት መሄዳችን፣ እያንዳንዱ ሰው የመንግሥቱን መልእክት አዘውትሮ ለመስማት የሚያስችል አጋጣሚ የሚሰጥ ስለሆነ የማናዳላ መሆናችንን በግልጽ ያሳያል። መልእክቱን የተቀበሉ ደግሞ በግለሰብ ደረጃ በሚያስፈልጋቸው መንገድ እርዳታ ያገኛሉ።

5 ሁሉም አስፋፊዎች ወጣቶች፣ በዕድሜ የገፉና አዲሶችም ጭምር ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው ሥራ ሊካፈሉ ይችላሉ። በዚህ መንገድ እያንዳንዱ ሰው ‘በሕዝብ ፊት በመመስከር ሊድን’ ይችላል። (ሮሜ 10:10) ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት ከሌሎች ጋር መሳተፋችን በፍቅርና በአንድነት ማሰሪያ እርስ በርስ ያቀራርበናል። በዚያ ላይ ደግሞ ግድ የለሽ የሆኑ ሰዎች ወይም ተቃዋሚዎች በሚያጋጥሙን ጊዜ ጽናታችንን ለማሳየት አጋጣሚ እናገኛለን። እምነታችንን ለሕዝብ ስንገልጽ “በቲያትር መድረክ ላይ እንዳሉ ተዋንያን” እንሆናለን። ይህም ቅን የሆኑ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን የምናስተምርበት የተደራጀ ዝግጅት ያለን መሆኑን እንዲገነዘቡና በዚህ ዝግጅት እንዲጠቀሙ ሊረዳቸው ይችላል። (1 ቆሮ. 4:9 አዓት) ከቤት ወደ ቤት የሚደረገው ሥራ የይሖዋ በረከት እንዳለበትና እጅግ ብዙ ሰዎችን እውነተኛው አምልኮ ወደሚካሄድበት ‘ቤቱ’ ለመሰብሰብ ይሖዋ እየተጠቀመበት እንዳለ ሁሉም ነገር በግልጽ ያሳያል።​—ኢሳ. 2:2-4

6 ሰዎች በታሪክ ውስጥ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ የመንግሥቱን መልእክት መስማት የሚያስፈልጋቸው አሁን ነው። ይሖዋ ይበቃል እስከሚለን ድረስ ያለማሰለስ ከቤት ወደ ቤት እየሄድን መስበካችንን እንቀጥል። (ኢሳ. 6:11) እንዲህ ካደረግን በዚህ በመጨረሻው ዘመን ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው ዐቢይና ጠቃሚ በሆነ አገልግሎት ከመካፈል የሚመጣውን ደስታ በማግኘት የድካማችንን ዋጋ እናገኛለን።​—1 ቆሮ. 15:58

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ