የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/96 ገጽ 1
  • ምሥራቹን ያለማሰለስ ማወጅ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ምሥራቹን ያለማሰለስ ማወጅ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እንዴት ይሰማሉ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • ያለማሰለስ ከቤት ወደ ቤት መሄድ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ያለማሰለስ ስበኩ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • መስበክና ማስተማር—ደቀ መዛሙርት ለማድረግ የሚረዱ ወሳኝ ነገሮች
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 8/96 ገጽ 1

ምሥራቹን ያለማሰለስ ማወጅ

1 የጥንት ክርስቲያኖች አገልግሎታቸውን ከፍ አድርገው ይመለከቱት ነበር። “ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር” በማለት ሉቃስ ዘግቧል። (ሥራ 5:42) ምንም ነገር፣ ስደትም እንኳን ቢሆን ከመስበክ ወደ ኋላ እንዲሉ አላደረጋቸውም ነበር! (ሥራ 8:4) በየቀኑ እውነትን ለሌሎች ሰዎች ይናገሩ ነበር።

2 እኛስ እንዴት ነን? እንዲህ እያልህ ራስህን ጠይቅ:- ‘የጊዜው አጣዳፊነት ይሰማኛልን? ምሥራቹን ያለማሰለስ ማወጄን የመቀጠል ዝንባሌ አለኝ?’

3 ያለማሰለስ በመስበክ ረገድ በዘመናችን ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎች፦ የፖሊዮ በሽታ ለአካል ጉዳት የዳረጋት አንዲት እህት ሰው ሠራሽ በሆነ የመተንፈሻ መሣሪያ ውስጥ ትኖር ነበር። ወደ መንግሥት አዳራሽ መሄድ ወይም ደግሞ ትልልቅ ስብሰባዎች ላይ መገኘት አትችልም ነበር። ይሁን እንጂ ምሥራቹን በማወጁ ተግባር ተግታ ትሠራ ነበር። በሰው ሠራሽ የመተንፈሻ መሣሪያ ውስጥ በነበረችባቸው 37 ዓመታት 17 ሰዎች እውነትን እንዲያውቁ ለመርዳት ችላ ነበር! ይህንን እንዴት ልታከናውን ቻለች? ምንም እንኳ ከቤት ወደ ቤት መሄድ ባትችልም በየቀኑ ሊጠይቋት ለሚመጡ ሰዎች መደበኛ ባልሆነ መንገድ የመመሥከር አጋጣሚዎች ታገኝ ነበር።

4 በቦስኒያ የሚኖሩ ወንድሞቻችን ጦርነትና እጦት ያስከተለባቸውን ችግር መቋቋም አስፈልጓቸዋል። ይሁን እንጂ ለሌሎች አዘውትረው መስበካቸውን ቀጥለዋል። በሳራዬቮ ያሉ አስፋፊዎች ምሥራቹን ለሌሎች በመናገር በየወሩ በአማካይ 20 ሰዓት ያሳልፋሉ። እያንዳንዳቸውም በአማካይ ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ይመራሉ። ምንም እንኳ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ቢሆንም ያለማሰለስ መስበካቸውንም ሆነ ማስተማራቸውን ቀጥለዋል።

5 ትንንሽ ልጆችም ለምሥክርነቱ ሥራ ከፍተኛ ቅንዓት ያሳያሉ። ወታደሮች በሩዋንዳ ውስጥ የሚኖሩ የአንድ ቤተሰብ አባላትን አንድ ክፍል ውስጥ አድርገው ሊገድሏቸው ተዘጋጁ። ቤተሰቡም ከመገደላቸው በፊት እንዲጸልዩ ፈቃድ ጠየቁ፤ ተፈቀደላቸውም። ዲቦራ የተባለችው ትንሽ ልጅ “ይሖዋ፣ በዚህ ሳምንት እኔና አባባ አምስት መጽሔቶች አበርክተናል። ታዲያ እንደገና ተመልሰን ሄደን እነዚህን ሰዎች እውነትን የምናስተምራቸውና ሕይወት እንዲያገኙ የምንረዳቸው እንዴት ነው?” በማለት ጮክ ብላ ጸለየች። በጠንካራ እምነቷና ለአገልግሎት በነበራት ፍቅር ምክንያት ጠቅላላው ቤተሰብ ከሞት ተረፈ።

6 በአሁኑ ጊዜ ለሌሎች ለመመሥከር ለሚያስችሉ አጋጣሚዎች ንቁ መሆን እንዲሁም “ለዘላለም ሕይወት ትክክለኛ ዝንባሌ ያላቸውን” ሰዎች መፈለግ አስፈላጊ ነው። (ሥራ 13:48 አዓት) የጉባኤ ሽማግሌዎች ከአካባቢው ሁኔታ ጋር በሚስማማ መንገድ ጠዋት፣ ከሰዓት በኋላ ወይም ምሽት ላይ የቡድን ምሥክርነት እንዲደረግ ዝግጅት ያደርጋሉ። በአገልግሎት ስብሰባዎች የሚጠኑ በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚወጡ ርዕሶች እንዲሁም በወረዳና በአውራጃ ስብሰባዎች ላይ የሚቀርቡት ክፍሎች ብዙዉን ጊዜ በመንግሥቱ ምሥክርነት በልዩ ልዩ አቅጣጫዎች መካፈል የሚያስችሉ ወቅታዊ ሐሳቦችንና ማበረታቻዎችን ያካተቱ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ የወረዳና የአውራጃ የበላይ ተመልካቾች ከቤት ወደ ቤትና በመንገድ ላይ በሚሰጠው ምሥክርነት አስፋፊዎችን ያሰለጥናሉ፤ የንግድ እንቅስቃሴ በሚደረግባቸው ቦታዎች እንዴት መሥራት እንደሚቻል ከማሳየታቸውም በላይ ሰዎች ሊገኙ በሚችሉበት በማንኛውም ቦታ ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችሉ የተለያዩ መንገዶችን ይጠቁሟቸዋል። ይህ ሁሉ ምሥራቹን ያለማሰለስ የማወጁን አስፈላጊነት ያጎላል!

7 የኢየሱስ ሐዋርያት “እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም” በማለት በድፍረት ተናግረዋል። እነዚህ ሁሉ እንቅፋቶች እያሉ መጽናት የቻሉት እንዴት ነበር? ይሖዋ እንዲረዳቸው ሲጠይቁት ስለረዳቸው “ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፣ የእግዚአብሔርንም ቃል ያለፍርሃት በድፍረት ተናገሩ።” (ሥራ 4:20, 29, 31 የ1980 ትርጉም) ሁሉም በሚያከናውኑት አገልግሎት ልዩ የሆነ ተሞክሮ ያገኛሉ ማለት አይደለም። ይሁን እንጂ ያለማሰለስ ምሥራቹን ለማወጅ ልባዊ ፍላጎት ካለንና በየቀኑ እንዲህ ለማድረግ ከጣርን ይሖዋ ይረዳናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ