የጥያቄ ሣጥን
◼ አንድ የዘወትር አቅኚ ከአንድ ጉባኤ ተቀይሮ ቢመጣ ጸሐፊው ምን ማድረግ ይኖርበታል?
ጸሐፊው በጉባኤ ሪፖርት መመለሻ ቅጽ (S-1) ጀርባ ባለው ቦታ ላይ ስለ ጉዳዩ በመግለጽ ለማኅበሩ ማስታወቅ ይኖርበታል። ምንም ጊዜ ሳያባክንም አቅኚው በፊት ከነበረበት ጉባኤ ጸሐፊ ጋር ተጻጽፎ የአቅኚውን የአስፋፊ ሪፖርት መመዝገቢያ (S-21) ካርዶች በሙሉ እንዲልክለትና የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ አቅኚውን ለማስተዋወቅ የሚረዳ ደብዳቤ እንዲጽፍለት መጠየቅ አለበት።
አንድ አቅኚ ከነበረበት ቦታ ፈጽሞ አዲስ ወደ ሆነ አካባቢ ከተዛወረ ብዙውን ጊዜ እስኪረጋጋና ጥሩ የአገልግሎት ፕሮግራም እስኪያወጣ ድረስ አንዳንድ ችግሮች ያጋጥሙታል። አቅኚው ወደ አዲስ ጉባኤ ያደረገው ዝውውር በተቻለ መጠን ቀላል እንዲሆንለት ሽማግሌዎች እርዳታ ቢያደርጉለት በርዳታቸው በጣም ይደሰታል።
ማሳሰቢያ፦ ጸሐፊው የአቅኚነት አገልግሎት መታወቂያ ካርድ (S-202) የሚሰጠው በዚያው አገር ውስጥ ከአንዱ ጉባኤ ወደ ሌላ ጉባኤ ለተዛወሩ አቅኚዎች ብቻ ነው። ካርዳቸው የጠፋባቸው፣ በጋብቻ ወይም በፍቺ ምክንያት ስማቸውን የቀየሩ ወይም በሌላ ቅርንጫፍ ቢሮ ሥር ካሉ አገሮች የመጡ ከሆኑ (በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ደግሞ ከአንዱ አገር ወደ ሌላው የተዛወሩ ሁሉ) አዲስ ካርድ ማግኘት የሚችሉት ከጸሐፊው ሳይሆን ከማኅበሩ ነው። በዚህ ጊዜ ጸሐፊው ወይም አቅኚው ለማኅበሩ ጽፈው ስለ ሁኔታው በመግለጽ አዲስ ካርድ እንዲላክ ጥያቄ ማቅረብ ይገባቸዋል።