የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/94 ገጽ 1
  • ወንድሞቻችሁን በደንብ እወቋቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወንድሞቻችሁን በደንብ እወቋቸው
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ”
    እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት
  • “እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ”
    እውነተኛውን አንድ አምላክ አምልክ
  • የወንድማማችነት ፍቅራችሁ እያደገ ይሂድ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ከወንድሞቻችሁ ጋር በደንብ ተዋወቁ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 8/94 ገጽ 1

ወንድሞቻችሁን በደንብ እወቋቸው

1 አብረውን ይሖዋን ከሚያመልኩ ሰዎች ጋር የሚኖረን ግንኙነት በመንግሥት አዳራሽ ውስጥ አብሮ ከመሰብሰብ የበለጠ ነገርንም ይጨምራል። የአምላክን ፈቃድ የምናደርግ መሆናችን ከኢየሱስ ጋር በመንፈሳዊ ያዛምደናል። (ማር. 3:34, 35) ይህም ደግሞ እንድንወዳቸው ከታዘዝነው በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ከሚገኙት መንፈሳዊ ወንድሞችና እህቶች ጋር በመንፈሳዊ የቤተሰብ ዝምድና እንድንታቀፍ ያደርገናል። (ዮሐ. 13:35) እንግዲያውስ ወደ ‘አምላክ ቤተሰብ’ የተቀላቀሉ ሁሉ እርስ በእርሳቸው በደንብ ለመተዋወቅ መጣር አለባቸው። — ኤፌ. 2:19 አዓት

2 ወንድሞችህን በስም እወቅ፦ በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ቡድንህ ውስጥ ያሉትን የሁሉንም ወንድሞችና እህቶች ስም ታውቃለህን? ብዙውን ጊዜ በቡድኑ ውስጥ ያሉት ተሳታፊዎች ቁጥር ትንሽ ስለሚሆን የተሰብሳቢዎቹን በሙሉ፣ አለዚያም የአብዛኛዎቹን ስም ለማወቅ ቀላል ነው። ስማቸውን እንኳን የማታውቅ ከሆነ በደንብ አውቃቸዋለሁ ብለህ መናገር ትችላለህን?

3 በመንግሥት አዳራሽ በሚደረጉ ስብሰባዎቸ ላይ ከሚገኙ ሌሎች ሰዎች ጋር (ከልጆችም ጋር) ስለመተዋወቅስ ምን ማለት ይቻላል? ምናልባት ትንሽ ቁጥር ካላቸው ጓደኞቻችን ጋር ብቻ መጫወት ይቀናን ይሆናል። አዘውትረን ከተወሰኑ ሰዎች ጋር በመሆን መደሰታችን ስህተት ባይሆንም ሞቅ ያለ ሰላምታችንና የሚያንጽ ውይይታችን ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ እንዲገደብ አንፈልግም። ሁሉንም ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በደንብ ለማወቅ በመጣር ‘መስፋፋት’ ይኖርብናል። (2 ቆሮ. 6:11–13) ይህ ከእነሱ ጋር በስም መተዋወቅን እንደሚጨምር ግልጽ ነው።

4 የጉባኤ ስብሰባዎችን የሚመሩ ወንድሞች በዚያ የሚገኙትን የሁሉንም ሰዎች ስም ለማወቅ መጣር ይኖርባቸዋል። ከመድረክ ላይ እያንዳንዳቸውን በየስማቸው መጥራቱ የሰጡት ሐሳብ ተቀባይነት እንዳገኘ እንዲሰማቸው ሲያደርግ እግረ መንገዱንም ሌሎች የእነርሱን ስም እንዲያውቁ ይረዳል። እርግጥ ነው በአድማጮች መካከል አዲሶች ወይም እንግዶች ምን ጊዜም ስለሚኖሩ ለማንኛውም ሰው ቢሆን የእያንዳንዱን ሰው ስም ማወቅ ሊያስቸግረው ይችላል። የሆነው ሆኖ የማያቋርጥ ልባዊ ጥረት ማድረጋችን ሌሎችን የሚያበረታታና በግለሰብ ደረጃ እንደምናብላቸው የሚያንጸባርቅ ይሆናል። — ሮሜ 1:11, 12

5 ሌሎችን በደንብ ለማወቅ ራስህ ቀዳሚ ሁን፦ ብዙውን ጊዜ ተጓዥ የበላይ ተመልካቾች ከብዙ ወንድሞችና እህቶች ጋር በደንብ ለመተዋወቅ ይችላሉ። ይህን የሚያደርጉት እንዴት ነው? በሦስት ዋና ዋና መንገዶች ነው:- (1) ዘወትር ከእነርሱ ጋር በመስክ አገልግሎት ይሠራሉ፤ (2) ቤታቸው መጥተው እንዲጎበኟቸው የሚቀርብላቸውን ግብዣ ሁኔታቸው በፈቀደላቸው መጠን ይቀበላሉ፤ እንዲሁም (3) በስብሰባዎች ላይ ከአዋቂዎችም ሆነ ከልጆች ጋር ሰላምታ ለመለዋወጥ ቀዳሚዎች ናቸው።

6 እናንተስ ቅርርባችሁን ለማስፋትና ከወንድሞቻችሁ ጋር ይበልጥ ለመተዋወቅ የምትችሉባቸው መንገዶች ይኖራሉን? ሌሎች ከእኛ ጋር አብረውን ወደ መስክ አገልግሎት እንዲሄዱ ልንጋብዛቸው እንችላለን። ከቤት ወደ ቤት መሄድ፣ ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች መምራት ወይም መጽሔቶችን በመጠቀም ከመንገድ ወደ መንገድ መመሥከር እርስ በእርስ ለመተዋወቅ የሚያስችሉ ግሩም አጋጣሚዎች ናቸው። አልፎ አልፎ ሌሎች ወደ ቤታችሁ እንዲመጡ መጋበዝና ከተቻለ ምግብ ወይም ቀለል ያለ ነገር በማዘጋጀት አብሮ መካፈልም ጥሩ ነው። አዳዲሶችን ወይም ዓይን አፋር የሆኑትን ቀረብ ብሎ ለማናገር ቀዳሚ መሆን እነርሱ በመንፈሳዊ እንዲታነጹ ከማድረጉም በላይ አብዝቶ የሚክስ ነው። — ሥራ 20:35፤ 1 ተሰ. 5:11

7 ጳውሎስ ወንድሞቹን በደንብ ያውቃቸው ነበር። በደብዳቤዎቹ ብዙዎቹን በየስማቸው መጥቀሱ ለእነሱ ያለውን ከራስ ወዳድነት የራቀ ስሜትና እውነተኛ ፍቅር የሚያረጋግጥ ነው። (1 ተሰ. 2:17፤ 2 ጢሞ. 4:19, 20) ወንድሞቻችንን በደንብ ለማወቅ የምናደርገው ጥረት ለሁላችንም በረከቶችን ያመጣልናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ