የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/95 ገጽ 1
  • ስላሉን ነገሮች አመስጋኝ መሆን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ስላሉን ነገሮች አመስጋኝ መሆን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “የምታመሰግኑ ሁኑ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • 1,000 ረዳት አቅኚዎች ይፈለጋሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • አመስጋኝ መሆናችሁን አሳዩ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ‘የምታመሰግኑ ሁኑ’
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 4/95 ገጽ 1

ስላሉን ነገሮች አመስጋኝ መሆን

1 “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።” (ሮሜ 5:8) ሁላችንም ይሖዋ አምላክና ልጁ ለእኛ ሲሉ ለከፈሉልን ታላቅ መሥዋዕት ምንኛ አመስጋኞች መሆን ይገባናል! በፈሰሰው የክርስቶስ ደም አማካኝነት ማንኛውም ሰው ሊሰጠን የማይችለውን ለዘላለም በሕይወት የመኖር አጋጣሚ አግኝተናል።

2 አድናቆታችንን እንዴት ማሳየት እንችላለን? ከአምላክ ቅዱስ ቃል ውስጥ ብቻ የሚገኘውን እውነተኛ እውቀት የተጠሙ በጣም ብዙ ሰዎች አሉ። ይሖዋ እነዚህ ሰዎች የእውነትን እውቀት ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ይፈልጋል። (1 ጢሞ. 2:4) ለእውነት ያለንን አድናቆት ‘የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥራች በመስበክ’ እናሳያለን። (ሉቃስ 4:43) በዚህ ሥራ በሙሉ ልብ መሳተፍ ክርስቶስ ለእኛ ሲል መሞቱን እንደምናደንቅ አንዲሁም ሌሎችን ደቀ መዛሙርት እንድናደርግ የሰጠንን ትእዛዝ በታማኝነት በመፈጸም እርሱን ለመምሰል እንደምንፈልግ የሚያሳይ ነው።—ማቴ. 28:19, 20

3 የተከፈቱልን አንዳንድ የስብከት በሮች ምንድን ናቸው? አልፎ አልፎ ረዳት አቅኚ ለመሆን እንችላለንን? አንዳንዶች አስቀድመው ወጪያቸውን ካሰሉ በኋላ ወደ ዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ሊገቡ ይችላሉ። እነዚህ የመንግሥቱን ምሥራች በማዳረስ የምናሳልፈውን ሰዓት ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ ግሩም አጋጣሚዎች ናቸው። ምናልባት ባለፉት ጊዜያት በአቅኚነት አገልግሎት ለመመዝገብ አስባችሁ ነገር ግን እንቅፋቶች በዝተውባችሁ ትታችሁት ይሆናል። ምናልባት እነዚያ ሁኔታዎቻችሁ አሁን ተለውጠው ይሆናል። ከሆነ፣ ወደ ዘወትር አቅኚነት አገልግሎት በመግባት ወይም ረዳት አቅኚ ሆኖ በማገልገል አገልግሎታችሁን ከፍ ለማድረግ በጥሞና አስባችሁበታልን?

4 በዙሪያችን ምን እየተከናወነ እንዳለ ስንመለከት አመስጋኝነታችን የበለጠ ጥልቀት እያገኘ ይሄዳል። በዓለም ዙሪያ ዓመፅ፣ ጥላቻና ብጥብጥ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው። ጳውሎስ ጊዜያችንን “የሚያስጨንቅ ዘመን” በማለት በትክክል ገልጾታል። (2 ጢሞ. 3:1) እንዲህ ባሉት አስጨናቂ ሁኔታዎች ውስጥ ለሌሎች የምናካፍለው የተትረፈረፈ ምሥራች አለን። በዚህ ወር በተናጠልም ሆነ ኮንትራት በማስገባት የምናበረክታቸው መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! የተባሉ ግሩም መጽሔቶች አሉን። በተጨማሪም በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ብሮሹሮች አሉን። እነዚህ ጽሑፎች ለሚያነቧቸው ሁሉ እውነተኛ እፎይታ ሊያመጡላቸው ይችላሉ። ስላሉን ነገሮች ያለን አመስጋኝነት እነሱን ለሌሎች በማካፈል ረገድ ለጋሶች እንድንሆን ሊያንቀሳቅሰን ይገባል።— ዕብ. 13:16

5 ከጥቂት ጊዜ በፊት ለራሳችንም ሆነ ለሌሎች ለማበርከት እነዚህ ውብ ባለ ሙሉ ቀለም መጽሔቶች፣ ብሮሹሮች፣ መጻሕፍትና ትራክቶች አልነበሩንም፤ አሁን እነዚህን ማግኘታችን አመስጋኞች እንድንሆን የሚያደርገን ሌላው ምክንያት ነው። ጥራት ባለው አቀራረባቸውና በያዙት መልእክት በመስካችን እነሱን የሚወዳደር የለም። ስለዚህ እነዚህን በዋጋ ሊተመኑ የማይችሉ መሣሪያዎች ሁልጊዜ በሚገባ በመታጠቅ በቅንዓት ለማበርከት ዝግጁ እንሁን።— ቆላ. 3:15፤ 1 ተሰ. 5:18, 19

6 ስላሉን ነገሮች አመስጋኝ የምንሆንባቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ፤ በእውነትም በጣም ብዙ መልካም ነገሮች አሉን። ለይሖዋ ምስጋናችንን የምንገልጽበት ከሁሉ የተሻለ መንገድ ስሙንና ዓላማዎቹን ለሌሎች ማሳወቅ ነው።— ኢሳ. 12:4, 5

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ