ለመታሰቢያው በዓል የሚያስፈልጉትን ነገሮች አዘጋጁ
ተናጋሪውን ጨምሮ ሁሉም በዓሉ የሚከበርበት ትክክለኛው ሰዓትና ቦታ ተነግሯቸዋልን? ተናጋሪው ፕሮግራሙ ከ45 ደቂቃ መብለጥ እንደሌለበት ያውቃልን?
ምሳሌያዊውን ቂጣና ወይን ጠጅ የሚያዘጋጅ ሰው ተመድቧልን? (መግ 4–111 ገጽ 14–16 ተመልከት።) ጠረጴዛውን ንጹሕ የጠረጴዛ ልብስ ለማልበስና በቂ ብርጭቆና ሳህን ለማቅረብ ዝግጅት ተደርጓልን?
ከበዓሉ በፊትና በኋላ የመንግሥት አዳራሹን ለማጽዳት ዝግጅት ተደርጓል? አስተናጋጆች እንዲሁም ቂጣውንና ወይኑን የሚያዞሩ ወንድሞች ተመድበዋል? ከስብሰባው በፊት በመታሰቢያው በዓል ላይ ስላላችሁ ኃላፊነት ለመወያየት የምትሰበሰቡበትን ፕሮግራም አውጥታችኋልን? ቂጣውና ወይኑ በሁሉም ፊት በሚገባ እንዲዞር ለማድረግ ምን መመሪያ እንከተላለን?
አረጋውያንና የአካል ጉዳተኞች የሆኑ ወንድሞችና እህቶች በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ለመርዳት ምን ዝግጅት ተደርጓል? ከቅቡዓን መካከል የሆኑ በቤት የዋሉና በበዓሉ ላይ መገኘት የማይችሉ ካሉ ከቂጣውና ከወይኑ እንዲካፈሉ የሚያስችላቸው ዝግጅት ተደርጓል?