የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች
የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው እሁድ መጋቢት 23 ቀን ነው። ሽማግሌዎች ለሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረት ሊሰጧቸው ይገባል:-
◼ የስብሰባውን ሰዓት ስትወስኑ ቂጣና ወይኑ መዞር ያለበት ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ መሆኑን አትዘንጉ።
◼ ተናጋሪውን ጨምሮ ሁሉም ተሰብሳቢዎች በዓሉ የሚከበርበት ትክክለኛ ሰዓትና ቦታ ሊነገራቸው ይገባል።
◼ ተገቢው ዓይነት ቂጣና ወይን መዘጋጀት ይገባዋል።— መጠበቂያ ግንብ ገጽ 2-106 ገጽ 17 ተመልከት።
◼ ሳህኖች፣ ብርጭቆዎች እንዲሁም አመቺ የሆነ ጠረጴዛና የጠረጴዛው ልብስ ወደ መንግሥት አዳራሹ መጥተው ቀደም ብሎ በየቦታቸው መቀመጥ ይኖርባቸዋል።
◼ የመንግሥት አዳራሹም ሆነ ሌላ የመሰብሰቢያ ቦታ ቀደም ብሎ በሚገባ መጽዳት ይኖርበታል።
◼ አስተናጋጆች እንዲሁም ቂጣውንና ወይኑን የሚያዞሩት ወንድሞች ቀደም ብሎ ሊመረጡና ተገቢ ስለሆነው አሠራርና ስለተሰጣቸው የሥራ ድርሻ መመሪያ ሊሰጣቸው ይገባል።
◼ የአካል ችግር ያለባቸውንና በቦታው መገኘት የማይችሉትን ቅቡዓን ለማስተናገድ ዝግጅት መደረግ ይኖርበታል።
◼ የበዓሉ ሥርዓት በአንድ የመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲደረግ ታቅዶ ከሆነ በኮሪደሩ፣ በመግቢያው፣ በሕዝብ መተላለፊያዎችና በመኪና ማቆሚያዎች ላይ ጭንቅንቅ እንዳይፈጠር በጉባኤዎቹ መካከል ጥሩ ቅንጅት ሊኖር ይገባል።