የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች
በዚህ ዓመት የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ሐሙስ፣ ሚያዝያ 1 ነው። ሽማግሌዎች ለሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረት ሊሰጡ ይገባል:-
◼ ስብሰባው የሚደረግበትን ሰዓት ስትወስኑ ቂጣውና ወይኑ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር እንደሌለባቸው አስታውሱ። ኃላፊነት ያለባቸው ወንድሞች የስብሰባውን ሰዓት እንዲሁም ቂጣና ወይን ማዞርን በሚመለከት የሚያዝያ 27, 1998 ደብዳቤን መከለስ አለባቸው።
◼ ተናጋሪውን ጨምሮ ሁሉም ተሰብሳቢዎች በዓሉ የሚከበርበት ትክክለኛ ሰዓትና ቦታ ሊነገራቸው ይገባል።
◼ ተገቢው ዓይነት ቂጣና ወይን ተዘጋጅቶ መቀመጥ አለበት።—መጠበቂያ ግንብ 2-106 ገጽ 17ን ተመልከቱ።
◼ ሳህኖች፣ ብርጭቆዎች እንዲሁም ተስማሚ የሆነ ጠረጴዛና የጠረጴዛ ጨርቅ ወደ መንግሥት አዳራሹ መጥተው ቀደም ብሎ በየቦታቸው መቀመጥ ይኖርባቸዋል።
◼ የመንግሥት አዳራሹም ሆነ ሌላ የመሰብሰቢያ ቦታ ቀደም ብሎ በሚገባ መጽዳት አለበት።
◼ አስተናጋጆች እንዲሁም ቂጣውንና ወይኑን የሚያዞሩ ወንድሞች ቀደም ብሎ ሊመረጡና ተገቢ ስለሆነው አሠራርና ስለተሰጣቸው የሥራ ድርሻ መመሪያ ሊሰጣቸው ይገባል።
◼ የአካል ጉዳተኞችንና በቦታው መገኘት የማይችሉትን ቅቡዓን ለማስተናገድ ዝግጅት መደረግ ይኖርበታል።
◼ የበዓሉ ሥነ ሥርዓት በአንድ የመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲደረግ ፕሮግራም ተይዞ ከሆነ በመተላለፊያዎች ላይና በግቢው ውስጥ ጭንቅንቅ እንዳይፈጠር በጉባኤዎቹ መካከል ጥሩ ቅንጅት ሊኖር ይገባል።