የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች
በዚህ ዓመት የመታሰቢያው በዓል ሐሙስ መጋቢት 28 ይከበራል። ሽማግሌዎች ለሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረት መስጠት ይገባቸዋል:-
◼ ስብሰባው የሚደረግበትን ሰዓት ስትወስኑ ቂጣውና ወይኑ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር እንደሌለባቸው አስታውሱ።
◼ ተናጋሪውን ጨምሮ ሁሉም ተሰብሳቢዎች በዓሉ የሚከበርበት ትክክለኛ ጊዜና ቦታ ሊነገራቸው ይገባል።
◼ ተገቢው ዓይነት ቂጣና ወይን ተዘጋጅቶ መቀመጥ አለበት።—መጠበቂያ ግንብ 2-106 ገጽ 17ን ተመልከቱ።
◼ ሳህኖች፣ ብርጭቆዎች እንዲሁም ተስማሚ የሆነ ጠረጴዛና የጠረጴዛ ልብስ ቀደም ብለው ወደ ስብሰባው አዳራሽ መጥተው በየቦታቸው መቀመጥ ይኖርባቸዋል።
◼ የመንግሥት አዳራሹም ሆነ ሌላ የመሰብሰቢያ ቦታ ቀደም ብሎ በሚገባ መጽዳት አለበት።
◼ አስተናጋጆች እንዲሁም ቂጣውንና ወይኑን የሚያዞሩ ወንድሞች ቀደም ተብሎ ሊመረጡና የሥራ ድርሻቸው፣ ተገቢ የሆነው የአሠራር ሥርዓት እንዲሁም አግባብ ያለው አለባበስና አበጣጠር አስፈላጊ መሆኑ ሊነገራቸው ይገባል።
◼ አቅመ ደካማ የሆኑ እንዲሁም በበዓሉ ላይ መገኘት የማይችሉ ቅቡዓን ከቂጣውና ከወይኑ መካፈል የሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸት ይኖርበታል።
◼ ከአንድ በላይ የሆኑ ጉባኤዎች በአንድ የመንግሥት አዳራሽ የሚጠቀሙ ከሆነ መግቢያው ላይ እንዲሁም በመኪና ማቆሚያው አካባቢና ከመንግሥት አዳራሹ ውጪ ባለው ጎዳና ላይ አላስፈላጊ ጭንቅንቅ እንዳይፈጠር በጉባኤዎቹ መካከል ጥሩ ቅንጅት ሊኖር ይገባል።