የጥያቄ ሣጥን
◼ ወደ ስብሰባዎች ስንሄድ ምን ምን ጽሑፎችን መያዝ ይኖርብናል?
በየሳምንቱ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ጠቃሚ የሆኑ መመሪያዎችና ማበረታቻዎች እናገኛለን። (ኢሳ. 48:17፤ ዕብ. 10:24, 25) ሆኖም ጥቅም ማግኘታችን በአብዛኛው የተመካው በዝግጅታችን ላይ ነው።
እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የራሱን የጥናት ጽሑፍና ለስብሰባው አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ነገሮች ይዞ መምጣቱ እጅግ አስፈላጊ ነው። ይህም መጽሐፍ ቅዱስ፣ የመዝሙር መጽሐፍ፣ እየተጠና ያለውን ጽሑፍ(ፎች)፣ የማስታወሻ ደብተር እና እስክሪብቶ ወይም እርሳስ ይዞ መሄድን ይጨ ምራል።
ለቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ስብሰባ የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራምና የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ አስፈላጊ ናቸው። እነዚህን ጽሑፎች መያዝ በተማሪዎች የሚቀርቡትን ንግግሮች ጭብጥ በአእምሯችን ለመያዝና የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ምክር በሚሰጥበት ጊዜ ለመከታተል እንድንችል ይረዱናል። የራሳችንን ንግግሮች እና የመስክ አገልግሎት አቀራረባችንን ለማሻሻል ከምክሩና ከሐሳቡ በግል ጥቅም ልናገኝ እንችላለን። ከጥር ጀምሮ አብዛኛዎቹ የመምሪያ ንግግሮች እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት ከተባለው መጽሐፍ ላይ የተወሰዱ ናቸው።
ለአገልግሎት ስብሰባ የወቅቱ የመንግሥት አገልግሎታችን እና ማመራመር የተባለውን መጽሐፍ ይዘን መሄድ ያስፈልገናል።
በስብሰባው ወቅት እንደሚያገለግሉ የተጠቀሱ ጽሑፎችን ለምሳሌ በትዕይንት ላይ የሚበረከቱ ጽሑፎችን ያዙ። ሽማግሌዎች አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት የተባለውን መጽሐፍ ቅጂ መያዝ ይኖርባ ቸዋል።
ወላጆች ልጆቻቸው በጉባኤ ስብሰባዎች በጸጥታ እንዲቀመጡና በጥንቃቄ እንዲያዳምጡ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ልጆች ማንበብ ባይችሉም እንኳ የመጠበቂያ ግንብ እና የሌሎች ጽሑፎች ቅጂዎች ቢኖሯቸው ለትምህርቱ ፍላጎት እንዲያድርባቸው ያበረታታቸዋል። ልጆች ቲኦክራሲያዊ ለሆኑ ጽሑፎች አክብሮት እንዲኖራቸውና በጥንቃቄ እንዲጠቀሙባቸው ስልጠና ከተሰጣቸው የዕድሜ ልክ ጥሩ መንፈሳዊ ልማድ ይኖራቸዋል።
ሙሉ ለሙሉ የታጠቅን ሆነን ወደ ጉባኤ ስብሰባዎች በምንሄድበት ጊዜ ከጉባኤ ስብሰባዎች የምናገኘው ደስታና እርካታ በይበልጥ ይጨምራል። (2 ጢሞ. 3:17) ‘የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንደሞላብን’ የሚያረጋግጠው ከሁሉ የተሻለው መንገድ ይህ ነው።— ቆላ. 1:9