የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/95 ገጽ 1
  • ይሖዋን በየዕለቱ አወድሱት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይሖዋን በየዕለቱ አወድሱት
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እናንት ወጣቶች፣ ይሖዋን አመስግኑ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • በየቀኑ ይሖዋን አወድሱ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • መደበኛ ባልሆነ መንገድ መመሥከር ትችላላችሁ!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
  • የአውራጃ ስብሰባው ቀስቃሽ ጥሪ አቅርቧል!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 12/95 ገጽ 1

ይሖዋን በየዕለቱ አወድሱት

1 አምላካችን ይሖዋ ድንቅ የሆነ አፍቃሪ አምላክ ከመሆኑም በላይ የሕይወትና የደስታ ምንጭ ነው። ታላቅ አምላክ በመሆኑ ሁሉም ፍጥረታቱ ውዳሴ ሊያቀርቡለት ይገባዋል። እኛም በግለሰብ ደረጃ መዝሙራዊው “በምስጋናህም ሁሉ ላይ እጨምራለሁ። . . . አፌ ጽድቅህን ሁልጊዜም ማዳንህን ይናገራል” በማለት እንደተናገረው ለማለት እንፈልጋለን። (መዝ. 71:14, 15) ይህን ለማድረግ በየዕለቱ ይሖዋን ለማወደስ የሚያስችሉ መንገዶችን መፈለግና ስለ ጥሩነቱ፣ ስለ ጽድቁና የመዳን ዝግጅቱ ለመናገር መገፋፋት አለብን።

2 የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ይሖዋን በማወደስ ረገድ ጥሩ ምሳሌ ትተውልናል። ሥራ 2:46, 47 በጰንጠቆስጤ ዕለት ስለተጠመቁት 3,000 ሰዎች ሲናገር እንዲህ ብሏል:- “በየቀኑም በአንድ ልብ ሆነው በመቅደስ እየተጉ . . . እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በሕዝብ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው። ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።” ስለ ይሖዋና ስለ መሲሑ አስደናቂ እውነቶች ይማሩ ነበር። እነርሱም በተራቸው ሌሎችን እንዲያዳምጡና እንዲማሩ እንዲሁም ይሖዋን እንዲያወድሱ በማበረታታት እንደ እነርሱ ደስተኛ እንዲሆኑ አድርገው ነበር።

3 በየዕለቱ ለማወደስ የሚያስችሉ አጋጣሚዎች አሉ፦ በዛሬው ጊዜ ብዙዎች መደበኛ ባልሆነ መንገድ በመመሥከር ይሖዋን በየዕለቱ ማወደስ እንደሚችሉ ተገንዝበዋል። ቀደም ብለው መዘጋጀታቸው ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ረድቷቸዋል። መደበኛ ባልሆነ ምስክርነት ለመካፈል ወስና የነበረች አንዲት እህት መኪናዋን ሌባ ሰበረባት። መኪናዋ እንዲጠገንላት ወደ ጋራዥ ደወለችና ሊጠግንላት ለሚመጣው መካኒክ ለመመስከር ወሰነች። የይሖዋን መመሪያ እንድታገኝ በመጸለይ ጥሩ ቅድመ ዝግጅት አደረገች። ለሠራተኛው አንድ ሰዓት ሙሉ መሰከረችለትና ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ አበረከተችለት።

4 አንዲት ሌላ እህት በእግሯ ስትጓዝ ከአንዲት ጎረቤቷ ጋር ሁልጊዜ ትገናኝ ነበር። አንድ ቀን ሲገናኙ በኑሮ ውስጥ ስለሚያጋጥሙ ችግሮች ጠለቅ ያለ ውይይት አደረጉ፤ ይህም ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ በር ከፋች ሆነ። በመጨረሻም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ተጀመረ። ይህች ሴት በፊት በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በአምላክ ላይ እምነት ስላልነበራት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቷ መጥተው ቢያነጋግሯት ኖሮ አልፈልግም ትላቸው እንደነበር ከጊዜ በኋላ ተናግራለች።

5 አንዳንድ አስፋፊዎች የተለያዩ ነገሮችን ለመሸጥ ወይም ለሌላ ጉዳይ ወደ ቤታቸው ለሚመጡ ሰዎች ምስክርነት መስጠት የሚቻል ሆኖ አግኝተውታል። በአየርላንድ የሕይወት ኢንሹራንስ የሚሸጥ አንድ ሰው አንዲትን እህት ቤቷ መጥቶ አነጋገራት። እህት የዘላለም ሕይወት ተስፋ እንዳለ ነገረችው። ከልጅነቱ ጀምሮ የሮማ ካቶሊክ ተከታይ የነበረው ይህ ሰው የነገረችው ነገር ጨርሶ እንግዳ ሆነበት። ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ወሰደ፤ በተከታዩ ሳምንት ስብሰባ ላይ ተገኘ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጀመረ። ይህ ሰው በአሁኑ ጊዜ ተጠምቆ ወንድም ሆኗል።

6 ይሖዋን በየዕለቱ ለማወደስ የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን ለመጠቀም ሁላችንም ንቁዎች መሆን ይገባናል። ጥቂት መጽሔቶችን ወይም ትራክቶችን ሰው ሊያያቸውና ወደቤታችን ለሚመጡ ሰዎች በቀላሉ ለማበርከት በሚያስችሉ ቦታዎች ማስቀመጡ ጥሩ ነው። በአንዳንድ ቦታዎች በመናፈሻ ወንበሮች ላይ ለትንሽ ጊዜ ቁጭ ብትል ጥቂት ደቂቃዎች አረፍ ብለው ለሚሄዱ ሰዎች ምስክርነት ለመስጠት የሚያስችሉ ብዙ አጋጣሚዎች ይከፍትልሃል። የይሖዋ ምሥክር የሆኑ አንዳንድ ተማሪዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን ዴስካቸው ላይ በማስቀመጥ ጽሑፉን ተመልክቶ ጥያቄ ከሚጠይቃቸው ሰው ጋር ውይይት ለመጀመር ይጠቀሙበታል። ሰዎችን ስታነጋግር የምትጠቀምባቸው አንድ ወይም ሁለት ጥቅሶች በአእምሮህ ያዝ። ይሖዋ እንዲረዳህ ጠይቀው። እንዲህ በማድረግህ ትባረካለህ።— 1 ዮሐ. 5:14

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ