የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/95 ገጽ 2
  • እድገትህ በግልጽ እንዲታይ አድርግ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እድገትህ በግልጽ እንዲታይ አድርግ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ማደግህ በግልጥ ይታይ
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • እድገት አድርግ
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ወጣቶች—እድገታችሁ በግልጽ እንዲታይ አድርጉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • እድገትህ በግልጽ እንዲታይ አድርግ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 12/95 ገጽ 2

እድገትህ በግልጽ እንዲታይ አድርግ

1 መጀመሪያ የመንግሥቱን መልእክት የሰማህበትን ጊዜ አስታውስ። ቀላል የሆኑ እውነቶች እውቀትና ማስተዋል ለማግኘት ያለህን ፍላጎት ቀስቅሰውታል። መንገዶችህ ከይሖዋ መንገዶች የራቁ ስለነበሩ አኗኗርህን የማስተካከሉን አስፈላጊነት ብዙም ሳይቆይ ተገንዝበህ ነበር። (ኢሳ. 55:8, 9) እድገት አደረግህና ራስህን ለአምላክ ወስነህ ተጠመቅህ።

2 አንዳንድ መንፈሳዊ እድገቶች ካደረግክ በኋላ እንኳ መወገድ የነበረባቸው ድክመቶች ነበሩ። (ሮሜ 12:2) ምናልባትም በመስክ አገልግሎት ለመካፈል ፈራ ተባ እንድትል ያደረገህ የሰው ፍርሃት አድሮብህ ይሆናል። ወይም የአምላክን መንፈስ ፍሬዎች ማሳየት አስቸጋሪ ሆኖብህ ይሆናል። ያላንዳች ማመንታት ለራስህ ቲኦክራሲያዊ ግቦችን በማውጣት እድገት ለማድረግ ወስነህ ነበር።

3 አሁን ራስህን ከወሰንክ ብዙ ዓመታት አልፈው ሊሆን ይችላል። መለስ ብለህ ስትመለከት ምን እድገት አድርገሃል? አንዳንዶቹ ግቦችህ ላይ ደርሰሃልን? “መጀመሪያ” የነበረህ ዓይነት ቅንዓት አለህን? (ዕብ. 3:14) ጳውሎስ ጢሞቴዎስን “ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አስብ፣ ይህንም አዘውትር” በማለት ሲመክረው ጢሞቴዎስ የብዙ ዓመታት ተሞክሮ የነበረው የጎለመሰ ክርስቲያን ነበር።— 1 ጢሞ. 4:15

4 ራስን በራስ መመርመር አስፈላጊ ነው፦ የቀድሞ አኗኗራችንን መለስ ብለን ስንመረምር ጥናት ስንጀምር የነበሩብንን አንዳንድ ድካሞች አሁንም እንዳሉ ናቸውን? አንዳንድ ያወጣናቸው ግቦች ላይ መድረስ ተስኖናልን? ከሆነ ምክንያቱ ምንድን ነው? ጥሩ ዕቅዶች ቢኖሩንም እንኳ ዛሬ ነገ እንል ይሆናል። ምናልባት የኑሮ ጭንቀቶች ወይም የዚህ ሥርዓት ተጽዕኖዎች የምናደርገውን እድገት እንዲጎትቱብን ፈቅደንላቸው ሊሆን ይችላል።— ሉቃስ 17:28-30

5 ላለፈው ጊዜ ምንም ማድረግ ባንችልም ለወደፊቱ ግን ማድረግ የምንችለው ነገር ይኖራል። ራሳችንን በሃቀኝነት ጠለቅ ብለን በመመርመር ድክመታችን ምን እንደሆነ ማወቅና ለማሻሻል በሙሉ ኃይላችን ጥረት ማድረግ እንችላለን። ራስን መግዛት፣ የዋህነት ወይም ትዕግሥት የመሳሰሉ የመንፈስ ፍሬዎችን በማፍራት ረገድ ይበልጥ ጥረት ማድረግ ያስፈልገን ይሆናል። (ገላ. 5:22, 23) ከሌሎች ጋር ተስማምቶ መኖር ወይም ከሽማግሌዎች ጋር ተባብሮ መሥራት ካስቸገረን የዋህነትና ትሕትና ማዳበር ያስፈልገናል።— ፊልጵ. 2:2, 3

6 አንዳንድ የአገልግሎት መብቶች ላይ ለመድረስ በመጣጣር እድገታችንን በግልጽ ማሳየት እንችላለንን? ወንድሞች ተጨማሪ ጥረት በማድረግ ዲያቆን ወይም ሽማግሌ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዶቻችን የዘወትር አቅኚ መሆን እንችላለን። ብዙዎች ረዳት አቅኚነት ሊደረስበት የሚችል ግብ ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ የግል ጥናት ልማዳቸውን ለማሻሻል፣ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ይበልጥ ንቁ ተሳታፊ ለመሆን ወይም ይበልጥ ፍሬያማ የጉባኤ አስፋፊዎች ለመሆን ጥረት ሊያደርጉ ይችላሉ።

7 እርግጥ ነው፣ በምን ረገድ እድገት ማድረግ እንዳለብን የምንወስነው ራሳችን ነን። “ወደ ጉልምስና ለመድረስ” የምናደርገው ልባዊ ጥረት ደስታችንን እንደሚጨምርልንና ፍሬያማ የጉባኤው አባላት እንደሚያደርገን እርግጠኞች መሆን እንችላለን።— ዕብ. 6:1 አዓት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ