‘በትክክለኛ እውቀት እያደጋችሁ መሄዳችሁን ቀጥሉ’
አምላክ የሚሰጠውን ትክክለኛ እውቀት ማግኘት የዘላለም ሕይወት ያስገኛል። (ዮሐ. 17:3) ስለ ይሖዋ ያገኘነውን ትክክለኛ እውቀት ለማሳደግ የምንችለውን ያህል መጣር አለብን። (ቆላ. 1:9, 10 አዓት) ከሚያዝያ 29 ጀምሮ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለውን መጽሐፍ በጉባኤ መጽሐፍ ጥናት ላይ እናጠናለን። መጽሐፉን በማጥናታችን ራሳችን የአምላክን ቃል በተሻለ ሁኔታ ከመረዳታችንም በላይ በመጽሐፉ ተጠቅመን ሌሎችን ለማስጠናት ይበልጥ ብቁ እንሆናለን። አንተና ቤተሰብህ አስቀድማችሁ ከተዘጋጃችሁ፣ በየሳምንቱ መጽሐፍ ጥናት ላይ ተገኝታችሁ የምትሳተፉ ከሆነና ትምህርቱን በመስክ አገልግሎት ከሠራችሁበት ትባረካላችሁ።