የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/96 ገጽ 7
  • ሥራ በጣም ይበዛብሃልን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሥራ በጣም ይበዛብሃልን?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ሸክምን ሁሉ እናስወግድ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ዘመኑን መዋጀት የሚቻለው እንዴት ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ሁልጊዜ ሥራ ይብዛላችሁ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ብዙ ሥራ እያለብህ ደስተኛ ልትሆን ትችላለህን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 5/96 ገጽ 7

ሥራ በጣም ይበዛብሃልን?

1 ጳውሎስ ‘የጌታ ሥራ ሁልጊዜ የበዛልን’ እንድንሆን አጥብቆ መክሮናል። (1 ቆሮ. 15:58) በየዕለቱ የግል ጥናት እንድናደርግ፣ ዘወትር እንድናገለግል፣ በስብሰባዎች ላይ ሳናሰልስ እንድንገኝና በጉባኤ ውስጥ ያሉብንን ሥራዎች በትጋት እንድንወጣ ማሳሰቢያዎች ይሰጡናል። በዚህ ላይ እገዛችን የሚያስፈልጋቸውን ወንድሞች መርዳት አለብን። ብዙ ሥራ ሲደራረብብን አንዳንድ ጊዜ ከአቅማችን በላይ እንደሆነ ሊሰማንና ያለብንን የሥራ ጫና የምናቃልልበት መንገድ መፈለግ እንዳለብን እናስብ ይሆናል።

2 አንዳንድ ሥራዎችን መተው ወይም መጠናቸውን መቀነስ አስተዋይነትና ምክንያታዊነት የሚሆንባቸው ጊዜያት አሉ። አንዳንዶች ሰው የጠየቃቸውን ሁሉ ማድረግ ያለባቸው መስሎ ይሰማቸዋል። በዚህ ረገድ ሚዛንን መሳት ጭራሹኑ ሊጥለን የሚችል ጭንቀትና ውጥረት ይፈጥርብናል።

3 ሚዛናዊ ሁኑ፦ ጳውሎስ “ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ፈትኑ” በማለት የሰጠውን ምክር በሥራ ላይ ማዋል ሚዛናዊ ለመሆን ቁልፍ ነው። (ፊልጵ. 1:10 አዓት) ይህም በጣም አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ ማተኮርና ጊዜና ሁኔታዎች ሲፈቅዱልን ብዙም አስፈላጊ ያልሆኑ ነገሮችን ማከናወን ማለት ነው። የቤተሰብ ኃላፊነት እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች መካከል ግንባር ቀደም ነው። አንዳንድ ሰብዓዊ ሥራዎችን ወደ ኋላ ልናደርጋቸው አንችልም። ሆኖም በሕይወታችን ቅድሚያ የምንሰጠው ነገር የአምላክን መንግሥት አስቀድሙ በሚለው መሠረታዊ ሥርዓት ላይ የተዋቀረ መሆን እንዳለበት ኢየሱስ አስተምሯል። ከሁሉ በፊት ራሳችንን ለይሖዋ ስንወስን የገባነውን ቃል ለመፈጸም የሚያስችሉንን ነገሮች መሥራት አለብን።— ማቴ. 5:3፤ 6:33

4 ይህንን በአእምሯችን ከያዝን ውጥረት ከተሞላበት ፕሮግራማችን ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የግል ጉዳዮችን፣ ከልክ ያለፉ መዝናኛዎችንና ሳያስፈልግ እንዲህ አደርጋለሁ ብሎ ለሌሎች ቃል መግባትን እናስወግዳለን። ለእያንዳንዱ ሳምንት እንቅስቃሴያችን ፕሮግራም ስናወጣ በቂ የግል ጥናት ለማድረግ፣ በአገልግሎት ተገቢ በሆነ መጠን ለመካፈል፣ በስብሰባዎች ላይ ለመገኘትና ከአምልኳችን ጋር በቅርብ የተቆራኙ ሌሎች ነገሮችን ለማከናወን ጊዜ እንመድባለን። የተረፈው ጊዜ መንግሥቱን የሚያስቀድሙ ሚዛናዊ ክርስቲያኖች ለመሆን ያወጣነው ግብ ላይ ለመድረስ በሚያበረክቱት አስተዋጽኦ መጠን ለሌሎች ጉዳዮች ሊከፋፈል ይችላል።

5 እነዚህን ሁሉ ካደረግንም በኋላ ከባድ ሸክም እንደተጫነብን ይሰማን ይሆናል። እንደዚህ የሚሰማን ከሆነ ኢየሱስ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፣ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ” በማለት ላቀረበው ግብዣ ምላሽ መስጠት ያስፈልገናል። (ማቴ. 11:28) በተጨማሪም ‘ሸክማችንን በየቀኑ ወደሚያቀልልን’ እና ለደከሙት ኃይልን ወደሚሰጠው ወደ ይሖዋ ዞር በል። ጻድቁ ሲናወጥ ይሖዋ ዝም ብሎ እንደማይመለከት ቃል ገብቷል። (መዝ. 55:22፤ 68:19 የ1980 ትርጉም፤ ኢሳ. 40:29) ጸሎታችን መልስ እንደሚያገኝና በቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴ ንቁ ተሳትፎ እያደረግን ለመቀጠል እንደሚረዳን ትምክህት መጣል እንችላለን።

6 ጊዜና ጉልበት ቢጠፋላቸው በማያስቆጩት የመንግሥቱ ሥራዎች ስንጠመድ ድካማችን በጌታ ከንቱ እንደማይሆን በማወቃችን ደስተኞች መሆን እንችላለን።— 1 ቆሮ. 15:58

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ