የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/96 ገጽ 1
  • ዘመኑን መዋጀት የሚቻለው እንዴት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዘመኑን መዋጀት የሚቻለው እንዴት ነው?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለማንበብና ለማጥናት ጊዜ መዋጀት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • በጊዜ አጠቃቀማችሁ ረገድ ጠንቃቆች ሁኑ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ጊዜያችሁን በጥበብ ተጠቀሙበት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • ሕይወታችሁን በይሖዋ አገልግሎት ዙሪያ ገንቡ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 10/96 ገጽ 1

ዘመኑን መዋጀት የሚቻለው እንዴት ነው?

1 በይሖዋ አገልግሎት ሥራ የበዛልን መሆናችን በሥራ የተጠመድን እንድንሆን ያደርጋል። (1 ቆሮ. 15:58) በግልም ሆነ በቤተሰብ መልክ ማጥናት፣ መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ማንበብ፣ ለጉባኤ ስብሰባዎች መዘጋጀትና በዚያ መገኘት እንዲሁም ዘወትር በመስክ አገልግሎት መካፈል ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንገነዘባለን። የበላይ ተመልካቾች የእረኝነት ኃላፊነቶችን የተሸከሙ ከመሆናቸውም በላይ ሌሎች የጉባኤ ሥራዎችን ይሠራሉ። አንዳንዶች ከባድ የቤተሰብ ኃላፊነቶች ወይም ደግሞ ሌሎች ግዴታዎች ይኖሩባቸው ይሆናል። ማናቸውንም ነገር በሥርዓት ለማከናወን ሚዛናዊና የተደራጀን መሆን ያስፈልገናል።

2 ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባውን ነገር አስቀድሙ፦ ‘ዘመኑን በመዋጀት’ በኩል የተሳካልን መሆናችን የተመካው ባለን የማስተዋልና ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ ላይ ነው። (ኤፌ. 5:15, 16) ‘ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች’ ለይተን ማወቅና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ነገሮች ዝርዝር ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ ማስቀመጥ ይኖርብናል። (ፊልጵ. 1:10) አንድ ባልና ሚስት ቲኦክራሲያዊ ስለሆነው ቤተሰባቸው ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ:- “ሕይወታችን በእውነት እንዲሞላ አድርገናል . . . እውነት የሕይወታችን ክፍል ብቻ ሳይሆን ሕይወታችን ነው። የተቀረው ነገር ሁሉ ከዚህ በኋላ የሚመጣ ነው።” በሕይወታችን ውስጥ የይሖዋን አምልኮና አገልግሎት ማስቀደማችን የግድ አስፈላጊ ነው።

3 ጊዜ የሚያባክኑ ነገሮችን ለይታችሁ እወቁ፦ በአንድ ሳምንት ውስጥ 168 ሰዓታት አሉ፤ እንግዲያውስ ያለንን ጊዜ በጥበብ መጠቀም ይኖርብናል። ለቲኦክራሲያዊ ሥራዎች በቂ ጊዜ እንድናገኝ ጊዜ የሚያባክኑ ነገሮችን ለይተን ማወቅና መቀነስ ያስፈልገናል። አንዳንድ ሰዎች ቴሌቪዥን በመመልከት በሳምንት ከ30 ሰዓት በላይ ያጠፋሉ! ሌሎች ደግሞ ብዙ ጊዜ የሚያጠፉት ዓለማዊ ጽሑፎችን በማንበብ ነው። አንዳንዶች ደግሞ ለማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች፣ ለትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች፣ ለመዝናናት ወይም ለአንዳንድ የኮምፒዩተር ጨዋታዎች ሰፊ ጊዜ እንደሚመድቡ ይገነዘቡ ይሆናል። ጊዜያችንን በተሻለ መንገድ መጠቀም እንድንችል በየዕለቱ የምንሠራቸውን ነገሮች መለስ ብለን መመርመር ሊያስፈልገን ይችላል። በጣም አስፈላጊ ላልሆኑ ነገሮች ለምናጠፋው ጊዜ ገደብ ለማበጀት ጥበብ ያስፈልገናል።

4 ጥሩ የሥራ ፕሮግራም ይኑራችሁ፦ የግል ሁኔታችን ምንም ይሁን ምን ሁላችንም ለመንፈሳዊ ነገሮች ጊዜ መዋጀት እንችላለን። አንዳንዶች ጠዋት ቀደም ብለው ሥራቸውን መጀመራቸው ብዙ ነገሮችን ለማከናወን የሚያስችላቸው ሆኖ አግኝተውታል። ወደ ሥራ ስንሄድና ስንመጣ ወይም ሌሎችን በመጠበቅ ብዙ ሰዓት የምናሳልፍ ከሆነ ጥቂቱን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ፣ ለስብሰባ ለመዘጋጀት ወይም ማኅበሩ በካሴት ያዘጋጃቸውን ትምህርቶች ለማዳመጥ ልንጠቀምበት እንችላለን። ቤተሰቦች አንድ ላይ ለማጥናት የተወሰነ ቋሚ ጊዜ ቢመድቡ ይጠቀማሉ። እያንዳንዱ የቤተሰቡ አባል ሰዓቱን አክብሮ ለቤተሰብ ጥናቱ የሚገኝ ከሆነ ጊዜያቸው አይባክንም።

5 እያንዳንዱ ዕለት ባለፈ ቁጥር ‘የቀረው ዘመን አጭር እንደሆነ’ ይበልጥ መገንዘብ ይኖርብናል። (1 ቆሮ. 7:29) ሕይወታችን የተመካው የቀረውን ውድ ጊዜ በምንጠቀምበት መንገድ ነው። የመንግሥቱን ፍላጎቶች ለማስቀደም ዘመኑን የምንዋጅ ከሆነ እንባረካለን!— ማቴ. 6:33

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ