የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/99 ገጽ 1
  • እንዲመጡ ጋብዟቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እንዲመጡ ጋብዟቸው
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በስብሰባዎች ላይ መገኘታችን ስለ እኛ ምን ይጠቁማል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ መገኘትህ የሚጠቅምህ እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • “ወደ ይሖዋ ቤት እንሂድ”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ‘መንፈሱና ሙሽራይቱ “ና!” እያሉ ነው’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 3/99 ገጽ 1

1 ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት የቀረበ አንድ ጥሪ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ በ233 አገሮች እያስተጋባ ነው:- “ኑ፣ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ . . . እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፣ በጎዳናውም እንሄዳለን።” (ኢሳ. 2:3) ሰዎች ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርጉ መርዳት ከምንችልባቸው ከሁሉ የተሻሉ መንገዶች አንዱ ወደ ይሖዋ ድርጅት እንዲመጡ መጋበዝ ነው።

2 አንዳንድ አስፋፊዎች ጥናቶቻቸው በቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አማካኝነት ጉልህ ለውጥ እስኪያደርጉ ድረስ ወደ መንግሥት አዳራሽ ለመጋበዝ ያመነቱ ይሆናል። ሆኖም አንዳንድ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከመጀመራቸውም በፊት በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘት ይጀምራሉ። ሰዎች ወደ ስብሰባዎች እንዲመጡ ሞቅ ያለ ግብዣ ለማቅረብና ለማበረታታት ዛሬ ነገ ማለት የለብንም።

3 ማድረግ ያለብን ነገር፦ በአካባቢያችሁ ስለሚደረጉት የጉባኤ ስብሰባዎች ለማሳወቅ በመጋበዣ ወረቀቶች በሚገባ ተጠቀሙ። ለስብሰባዎቹ ክፍያ እንደማይጠየቅና ሙዳየ ምጽዋትም ፈጽሞ እንደማይዞር ጥቀሱላቸው። ስብሰባዎቹ የሚካሄዱበትን መንገድ ግለጹላቸው። ስብሰባዎቹ በእርግጥም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚካሄድባቸው እንደሆኑና ሁሉም ለመከታተል እንዲችሉ የሚጠናውን ጽሑፍ እንደሚያገኙ ንገሯቸው። ስብሰባው ላይ የሚገኙ ሰዎች በአስተዳደግም ሆነ በኑሮ ደረጃቸው ተመሳሳይ አለመሆናቸውን ጥቀሱላቸው። ተሰብሳቢዎቹ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሆኑና በተለያየ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ልጆችም መምጣት እንደሚችሉ ንገሯቸው። የምናስጠናቸውን ሰዎች መጋበዝና ስብሰባ ላይ መገኘት እንዲችሉም ማንኛውንም ዓይነት ትብብር ለማድረግ ራሳችንን ማቅረብ አለብን።

4 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በመጨረሻ ተጠቅሰው ከምናገኛቸው ነገሮች መካከል ይሖዋ ለሕይወት ካደረጋቸው ዝግጅቶች እንድንካፈል የቀረበ ሞቅ ያለ ግብዣ ይገኝበታል። “መንፈሱና ሙሽራይቱም:- ና ይላሉ። . . . የተጠማም ይምጣ፣ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።” (ራእይ 22:17) ሰዎች ስብሰባዎቻችን ላይ እንዲገኙ መጋበዝን የመሰለ ነገር የለም።

5 ኢሳይያስ 60:8 ወደ አምላክ ሕዝቦች ጉባኤዎች በመምጣት ላይ ያሉትን በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ አወዳሾች እንደ ርግብ በመመሰል በትንቢታዊ መንገድ ሲገልጻቸው “ርግቦች ወደ ቤታቸው እንደሚበርሩ፣ እነዚህ እንደ ደመና የሚበርሩ” ናቸው ብሏል። ሁላችንም አዳዲስ ሰዎችን ወደ ስብሰባዎቻችን ልንጋብዛቸውና እንግድነት እንዳይሰማቸው ልናደርግ እንችላለን። እንዲህ በማድረግ ይሖዋ የመሰብሰቡን ሥራ ሲያፋጥነው ከእርሱ ጋር መተባበራችንን እናሳያለን።—ኢሳ. 60:22

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ