የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/93 ገጽ 3-4
  • “ወደ ይሖዋ ቤት እንሂድ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ወደ ይሖዋ ቤት እንሂድ”
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 12 አንዳንዶች ወደ ኋላ የሚሉበት ምክንያት፦ ብዙውን ጊዜ ምንም ያህል ጥረት ብታደርግላቸውም አንዳንዶች ወደ ድርጅቱ ለመቅረብ አይፈልጉም። ጥረትህን በቶሎ አታቋርጥ። ራስህን በእነርሱ ቦታ ለማስቀመጥ ሞክር። በአንዳንድ በዓላት ካልሆነ በስተቀር በሃይማኖታዊ ስነ ሥርዓቶች ላይ የመገኘት አስፈላጊነት እስከዚህ ጊዜ ድረስ ተሰምቷቸው አያውቅ ይሆናል። የቤተሰቡ አባላት ወይም የቅርብ ወዳጆቻቸው ግፊት እያሳደሩባቸው ይሆናል። ጎረቤቶቻቸው እኛን በተመለከተ በጥላቻ ስለሚናገሩ አስፈራርተዋቸው ይሆናል። እንዲሁም እንዲባክኑ በሚያደርጓቸው የተለያዩ የማኅበራዊና የመዝናኛ ጉዳዮች ተጠላልፈው ይሆናል። እነዚህንም ሁኔታዎች ሊወጧቸው እንደማይችሏቸው መሰናክሎች አድርገው ይመለከቷቸዋል። ነገሮችን በትክክለኛው አቅጣጫ በመመልከት ‘የተሻለውን ነገር መርምረው እንዲያውቁ’ መርዳት ያስፈልግሃል። — ፊል. 1:10
  • 13 መጽናት እንደሚያስፈልግ የሚናገሩትን ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክንያቶች ጥቀስላቸው። ሁላችንም ማበረታቻና በመንፈሳዊ የሚገነቡ ነገሮችን በአፋጣኝ ማግኘት እንደሚያስፈልገን አጥብቀህ ግለጽላቸው። እነዚህንም የምናገኘው አንድ ላይ በምንሰበሰብበት ጊዜ ነው። (ሮሜ 1:11, 12) የቤተሰብ ተቃውሞ ወደ ኋላ እንድናፈገፍግ የሚያደርገን ተገቢ ምክንያት እንዳልሆነ ኢየሱስ ግልጽ አድርጎታል። (ማቴ. 10:34–39) ጳውሎስ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መሆናችንን በሕዝብ ፊት ለመግለጽ ማፈር እንደሌለብን አሳስቦናል። (2 ጢሞ. 1:8, 12–14) የግል ግቦችና ትኩረትን የሚስቡ ጉዳዮች ቁጥጥር ሊደረግባቸው ይገባል፤ አለበለዚያ ወጥመድ ይሆናሉ። (ሉቃስ 21:34–36) የይሖዋን በረከት ለማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች በሙሉ ነፍሳቸው የሚሠሩ መሆን አለባቸው እንጂ ፈጽሞ የተከፈለ ልብ ሊኖራቸው አይገባም። (ቆላ. 3:23, 24) እንዲህ ላሉት የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች አድናቆት ማሳደራቸው በመንፈሳዊ እንዲያድጉ መንገድ ሊከፍትላቸው ይችላል።
  • 14 በሩ ክፍት ነው፦ እውነተኛው አምልኮ የሚቀርብበት የይሖዋ ቤት ከሁሉም በላይ ከፍ ከፍ ብሏል። “ኑ፣ ወደ እግዚአብሔር [ይሖዋ አዓት] ተራራ፣ . . . እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፣ በጎዳናውም እንሄዳለን” የሚለው ግብዣ በዓለም ዙሪያ በ229 አገሮች ውስጥ እየተስተጋባ ነው። (ኢሳ. 2:3) አዲሶች የሚሰጡት አዎንታዊ ምላሽ ሕይወታቸውን ሊያድንላቸው ይችላል። ትኩረታቸውን ወደ ይሖዋ ድርጅት እንዲያዞሩ ማድረግ እነርሱን ልንረዳ ከምንችልባቸው በጣም ጥሩ መንገዶች አንዱ ነው።
  • ተማሪዎችን ከስማችን በስተጀርባ ወዳለው ድርጅት መምራት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ሌሎች ሰዎች በስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ እርዷቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • የሚታየው የአምላክ ድርጅት
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 4/93 ገጽ 3-4

“ወደ ይሖዋ ቤት እንሂድ”

1 ዳዊት “ወደ ይሖዋ ቤት እንሂድ” ለሚለው ጥሪ በጉጉት ምላሽ ሰጥቷል። (መዝ. 122:1 አዓት) በቤተ መቅደሱ የተወከለው የይሖዋ “ቤት” እውነተኛውን አምላክ ለማምለክ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች የሚሰበሰቡበት ቦታ ነበር። የጸጥታና የሰላም መቅደስ ነበር። በዛሬው ጊዜ ያለው “የእውነት ዓምድና መሠረት” የሆነው የአምላክ “ቤት” ዓለም አቀፉ የክርስቲያን ጉባኤ ነው። (1 ጢሞ. 3:15) ለመዳን የሚደረጉ ዝግጅቶች ሁሉ የሚመጡት በዚህ የመገናኛ መሥመር አማካኝነት ነው። በዚህም ምክንያት በአምላክ በሚተዳደረው መንግሥት ሥር እንደሚመጡ ቃል በተገቡልን በረከቶች ለመደሰት የሚፈልጉ “አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ።” — ኢሳ. 2:2

2 ይህ “ቤት” በ229 አገሮች ውስጥ የሚገኙትን ከ69,000 የሚበልጡ ጉባኤዎችን የያዘ ነው። ከአራት ሚልዮን የሚበልጡ ቀናተኛ ሠራተኞች “ና! . . . የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ” በማለት የሚያሰሙትን ግብዣ ተቀብለው ለሚመጡ ሁሉ በዓለም ዙሪያ የሚገኙት የመንግሥት አዳራሾች በሮች ክፍት ናቸው። (ራእይ 22:17) ብዙዎች ይህንን መልእክት ሰምተው በአድናቆት አዎንታዊ ምላሽ ሰጥተዋል። ሌሎችም በመልእክቱ ተነክተዋል፤ ሆኖም ከክርስቲያን ጉባኤ ጋር በመተባበር ወደ ይሖዋ ቤት ገና አልመጡም። እንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች ‘የሚያስፈልጓቸው መንፈሳዊ ነገሮች’ አሉ። እነዚህም ነገሮች ሊሟሉላቸው የሚችሉት በጉባኤ ውስጥ ባሉት ዝግጅቶች ብቻ ነው። (ማቴ. 5:3 አዓት) የምንኖረው የዚህ ሥርዓት መጨረሻ በፍጥነት እየተቃረበ ባለበት አሳሳቢ ጊዜ ውስጥ ነው። የግድ የለሽነት ወይም የእንቢተኝነት አመለካከቶች እርምጃ ከመውሰድ አደገኛ በሆነ ሁኔታ ሊያዘገዩን ይችላሉ። ሰዎች ወደ ድርጅቱ ይበልጥ በመጠጋት ወደ ‘አምላክ ለመቅረብ’ መጣራቸው በጣም አጣዳፊ ነው። (ያዕ. 4:8) ይህን እንዲያደርጉ እንዴት ልንረዳቸው እንችላለን?

3 በድርጅቱ ላይ እንዲያተኩሩ አድርግ፦ ፍላጎት ካሳዩ ሰዎች ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ከተገናኘንበት ጊዜ አንስተን ትኩረታቸውን ወደ ድርጅቱ ማዞር ይኖርብናል። ጥቅሶችን የማውጣትና መሠረታዊ የሆኑ ትምህርቶችን የማብራራት ችሎታ ሊኖረን ቢችልም የዚያ እውቀት ምንጮች አይደለንም። የተማርናቸው ነገሮች ሁሉ ‘በተገቢው ጊዜ ምግብን’ ከሚያቀርብልን ከባሪያው ክፍል ጋር ከተያያዘው ድርጅት የመጡ ናቸው። (ማቴ. 24:45–47) አዲሶች ንጹሕ አምልኮ ማለት ከእኛ ወይም ከጉባኤያችን የበለጠ ነገርን የሚያጠቃልል እንደሆነ ከመጀመሪያ ጀምረው መገንዘብ ያስፈልጋቸዋል። በይሖዋ አመራር ሥር የሚሠራ ቲኦክራቲካዊ የሆነ የተደራጀ ዓለም አቀፋዊ ማኅበር አለ።

4 እየተቀበልን ያለነው መመሪያ እኛን ለመምራትና ለማስተማር ቃል ከገባልን ከይሖዋ የሚመነጭ ነው። (መዝ. 32:8፤ ኢሳ. 54:13) ይህ መመሪያ በይበልጥ የሚሠራጨው በጽሑፎቻችን በኩል ነው። ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ጽሑፎቻችን የሕይወት አድን ትምህርቶች ምንጭ መሆናቸውን በማስገንዘብ ከፍ አድርገው እንዲመለከቷቸው ልንረዳቸው ከቻልን ጽሑፎቹን በቶሎ ከመጣል ይልቅ ይበልጥ ለማንበብና በሥራ ላይ ለማዋል ይችላሉ። ሁልጊዜ ጽሑፎቹን አክብሮት በሚያመጣ መንገድ እንጠቀምባቸው። ይህም አዲሶች ድርጅቱን እንዲያደንቁና በዝግጅቶቹ ላይ እንዲመኩ ያስተምራቸዋል።

5 ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ዘወትር ትምህርት የሚሰጥበት ማዕከላዊ የመሰብሰቢያ ቦታ በአካባቢያቸው መኖሩን እንዲያውቁ አድርግ። የመንግሥት አዳራሹን አድራሻና ስብሰባ የሚደረግበትን ሰዓት ንገራቸው። እኛ በምናደርጋቸው ስብሰባዎችና ባለፉት ጊዜያት ሲካፈሉባቸው በነበሩት ሃይማኖታዊ ስብሰባዎች መካከል ያለውን ልዩነት ግለጽላቸው ማንም ሰው ወደ ስብሰባዎቻችን ሊመጣ ይችላል፤ ሙዳየ ምጽዋት አይዞርም ወይም በግለሰብ ደረጃ ገንዘብ እንዲያዋጡ አይጠየቁም። የተሾሙ አገልጋዮች ፕሮግራሙን በሚመሩበት ጊዜ እያንዳንዱ ሰው ሐሳብ በመስጠትና በፕሮግራሙ ክፍሎች በመካፈል በስብሰባዎች የመሳተፍ አጋጣሚ ይኖረዋል። ቤተሰቦች ወደ ስብሰባው ሊመጡ ይችላሉ፤ ልጆችም በመጽሐፍ ቅዱስ ውይይቶች ውስጥ መካፈል ይችላሉ። የጉባኤ አገልጋዮቻችን የተለዩ ካባዎችና ልብሶች አይለብሱም። የመንግሥት አዳራሹ በጥሩ ሁኔታ የተጌጠ ሲሆን ሻማዎች፣ ሐውልቶች ወይም ስዕሎች የሉበትም። በስብሰባው የሚገኙት በአብዛኛው በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ናቸው።

6 ቀስ በቀስ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፍላጎት እንዲኖራቸው አድርግ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዋነኛ ዓላማ የአምላክን ቃል እውነት ማስተማር ነው። በተጨማሪም ተማሪው ለይሖዋ ድርጅት ያለውን አድናቆት ሊገነባለትና የድርጅቱ አካል የመሆንን ከፍተኛ አስፈላጊነት እንዲገነዘብ ሊያደርገው ይገባል። በመጀመሪያው መቶ ዘመን በኢየሱስና በደቀ መዛሙርቱ ይሠራ የነበረው ታላቅ ሥራ ቅን ልብ ያላቸውን ሰዎች ስቧቸዋል፤ ማዕከላዊ በሆነ የአስተዳደር አካል ሥር በመሆንም በሥራው እንዲተባበሩ አድርጓቸዋል። ጥሩ ምላሽ በተገኘባቸው መንደሮች ውስጥ ጉባኤዎች ይቋቋሙ ነበር። በእነዚያም ጉባኤዎች አማካኝነት የማያቋርጥ ሥልጠናና ትምህርት ይሰጥ ነበር። ከጉባኤው ጋር የሚተባበሩት በመንፈሳዊ እንዲጠነክሩ ይደረግ ነበር። ይህም በመከራ ጊዜ እንዲጸኑ ይረዳቸዋል። (ዕብ. 10:24, 25፤ 1 ጴጥ. 5:8–10) በዘመናችንም የይሖዋ ዓላማ “ሁሉንም በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።” (ኤፌ. 1:9, 10) በውጤቱም ዓለም አቀፍ ‘የወንድማማች ማኅበር’ ሊኖረን ችሏል። — 1 ጴጥ. 2:17

7 ሣምንታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ተማሪዎቹ ድርጅቱን እንዲያደንቁና ለመዳን ይችሉ ዘንድ ከዝግጅቶቹ ጥቅም እንዲያገኙ የሚረዳቸውን ትምህርት የሚጨምር መሆን ይኖርበታል። በየሣምንቱ ጥቂት ደቂቃዎችን በመውሰድ ስለ ድርጅቱና ስለ አሠራሩ አንዳንድ ነገሮችን ንገራቸው ወይም ግለጽላቸው። በ11–105 መጠበቂያ ግንብ ላይ ጠቃሚ የመነጋገሪያ ነጥቦችን ልታገኝ ትችላለህ። በሀያኛው መቶ ዘመን ያሉ የይሖዋ ምስክሮች የተባለውና እንደ አንድ አካል በመሆን የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምስክሮች የተባሉት ብሮሹሮች የድርጅቱን ዋና ዋና ገጽታዎችና እነርሱም እንዴት ሊጠቅሙን እንደሚችሉ ይገልጻሉ። ተማሪዎቹ የይሖዋ ምስክሮችና ከስሙ በስተጀርባ ያለው ድርጅት የተባለውን የቪድዮ ፊልም እንዲመለከቱ ዝግጅት ማድረግ እየተከናወነ ያለው ሥራ ምን እንደሆነ ራሳቸው እንዲያዩት ያስችላቸዋል። ከዓመት መጽሐፉ ላይ የተመረጡ ሪፖርቶችና ተሞክሮዎች ሥራው በኛ አገር ብቻ ሳይሆን በሌሎች አገሮችና ባሕሎች ውስጥም ምን ያህል ስኬታማ እንደሆነ ሊያሳዩ ይችላሉ። በሌሎች ጽሑፎችም ልትጠቀም ትችላለህ። ከቤት ወደ ቤት ለምን እንደምንሄድ፣ የስብሰባዎቻችንን ዓላማ፣ ሥራችን የገንዘብ ድጋፍ እንዴት እንደሚያገኝ እንዲሁም ሥራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ስፋት የመሳሰሉ ነገሮችን ከጊዜ ወደ ጊዜ በየደረጃው ግለጽላቸው።

8 አዲሶችን ከሌሎች ምስክሮች ጋር ማስተዋወቅ ስለ ጉባኤ ያላቸውን አመለካከት ስለሚያሰፋላቸው የሚያነቃቃ ውጤት ሊኖረው ይችላል። በየጊዜው ሌሎች አስፋፊዎች በጥናቱ እንዲካፈሉ ለመጋበዝ ትችላለህ። ከጥናትህ ጋር ተመሳሳይ አስተዳደግ ወይም ተመሳሳይ ፍላጎት ያለው በጉባኤ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሰው በጥናቱ ላይ እንዲገኝ መጋበዝ ለተማሪህ አመለካከት ስፋት ይጨምርለታል። ምናልባትም አንድ ሽማግሌ ከጥናቶችህ ጋር ለመተዋወቅ እንዲችል አብሮህ ይሄድ ይሆናል። ከክልል የበላይ ተመልካቹ ወይም ከሚስቱ ጋር አብረህ በመሄድ ጥናትህን ለመጎብኘት ዝግጅት ማድረግ ትልቅ በረከት ሆኖ ሊገኝ ይችላል። በአቅራቢያቸው የሚኖሩ ምስክሮች ካሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችህ ጋር ማስተዋወቁ ተማሪው በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ እንዲገኝ የሚረዳው ተጨማሪ ማበረታቻ ሊሆንለት ይችላል።

9 አዲሶች ወደ ስብሰባ እንዲመጡ አበረታታ፦ አዳዲስ ሰዎች በስብሰባ ላይ መገኘታቸው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋቸዋል። ፍላጎታቸውን ለማነሳሳት ሞክር። በመጠበቂያ ግንብ ጥናት ላይ የሚሸፈኑትን ርዕሰ ትምህርቶች አሳየው። በቅርቡ የሚሰጠውን የሕዝብ ንግግር ርዕስ ንገረው። ቲኦክራቲካዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የሚቀርብባቸውን ጽሑፎችና በጉባኤ መጽሐፍ ጥናት የሚሸፈኑትን ጽሑፎች ዋና ዋና ነጥቦች ንገረው። በእነዚህ ስብሰባዎች ምን እንደምትማርና በስብሰባዎቹ ላይ መገኘት ለምን አስፈላጊ ሆኖ እንደሚሰማህ የራስህን ስሜት ግለጽለት። የምትችል ከሆነ ወደ ስብሰባው ልትወስደው እንደምትችል ንገረው። ከስብሰባው በፊት ስልክ ብትደውልለት በስብሰባው ላይ ለመገኘት ተጨማሪ ማበረታቻ ሊሆንለት ይችላል።

10 የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪው ወደ ስብሰባ ሲመጣ እንግድነት እንዳይሰማው አድርግ። ሽማግሌውን ጨምሮ ሌሎች ሰዎችንም አስተዋውቀው። የሕዝብ ንግግር የሚካፈል ከሆነ ተናጋሪውን ወንድም አስተዋውቀው። የመንግሥት አዳራሹን አስጎብኘው። በጠረጴዛ ላይ የተደረደሩ ጽሑፎችና መጽሔቶች፣ የመዋጮ ሣጥን፣ የመጻሕፍት ቤቱና የዓመቱ ጥቅስ ዓላማ ምን እንደሆነ አብራራለት። አዳራሹ የአምልኮ ቦታ ብቻ ሳይሆን በአካባቢው የሚደረገው የስብከት ሥራ የሚደራጅበት ማዕከልም መሆኑን እንዲያውቅ አድርግ።

11 ስብሰባዎቻችን እንዴት እንደሚመሩ አብራራለት። የምንጠቀምባቸውን ጽሑፎች ለተማሪው አሳየው። መሠረታዊው የመማሪያ መጽሐፋችን መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን አስገንዝበው። ልጆችን ጨምሮ እያንዳንዱ ሰው በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ ይችላል። በመዝሙር መጽሐፋችን ላይ ያሉት ሙዚቃዎችና ግጥሞች ለአምልኮ እንድንጠቀምባቸው ታስቦ በይሖዋ ምስክሮች የተደረሱ መሆናቸውን ግለጽለት። ተሰብሳቢዎቹ የተለያየ የአስተዳደግ፣ የትምህርትና የኑሮ ደረጃ ያላቸው መሆኑን እንዲመለከት አድርግ። የወዳጅነትንና የእንግዳ ተቀባይነትን መንፈስ በተመለከተ ገንቢ ሐሳቦችን አቅርብለት። ይህ ደግነትና ልባዊ አሳቢነት ተማሪው ሌላ ጊዜም እንዲመጣ ከሚያደርጉት ጠንካራ ምክንያቶች አንዱ ሊሆን ይችላል።

12 አንዳንዶች ወደ ኋላ የሚሉበት ምክንያት፦ ብዙውን ጊዜ ምንም ያህል ጥረት ብታደርግላቸውም አንዳንዶች ወደ ድርጅቱ ለመቅረብ አይፈልጉም። ጥረትህን በቶሎ አታቋርጥ። ራስህን በእነርሱ ቦታ ለማስቀመጥ ሞክር። በአንዳንድ በዓላት ካልሆነ በስተቀር በሃይማኖታዊ ስነ ሥርዓቶች ላይ የመገኘት አስፈላጊነት እስከዚህ ጊዜ ድረስ ተሰምቷቸው አያውቅ ይሆናል። የቤተሰቡ አባላት ወይም የቅርብ ወዳጆቻቸው ግፊት እያሳደሩባቸው ይሆናል። ጎረቤቶቻቸው እኛን በተመለከተ በጥላቻ ስለሚናገሩ አስፈራርተዋቸው ይሆናል። እንዲሁም እንዲባክኑ በሚያደርጓቸው የተለያዩ የማኅበራዊና የመዝናኛ ጉዳዮች ተጠላልፈው ይሆናል። እነዚህንም ሁኔታዎች ሊወጧቸው እንደማይችሏቸው መሰናክሎች አድርገው ይመለከቷቸዋል። ነገሮችን በትክክለኛው አቅጣጫ በመመልከት ‘የተሻለውን ነገር መርምረው እንዲያውቁ’ መርዳት ያስፈልግሃል። — ፊል. 1:10

13 መጽናት እንደሚያስፈልግ የሚናገሩትን ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክንያቶች ጥቀስላቸው። ሁላችንም ማበረታቻና በመንፈሳዊ የሚገነቡ ነገሮችን በአፋጣኝ ማግኘት እንደሚያስፈልገን አጥብቀህ ግለጽላቸው። እነዚህንም የምናገኘው አንድ ላይ በምንሰበሰብበት ጊዜ ነው። (ሮሜ 1:11, 12) የቤተሰብ ተቃውሞ ወደ ኋላ እንድናፈገፍግ የሚያደርገን ተገቢ ምክንያት እንዳልሆነ ኢየሱስ ግልጽ አድርጎታል። (ማቴ. 10:34–39) ጳውሎስ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መሆናችንን በሕዝብ ፊት ለመግለጽ ማፈር እንደሌለብን አሳስቦናል። (2 ጢሞ. 1:8, 12–14) የግል ግቦችና ትኩረትን የሚስቡ ጉዳዮች ቁጥጥር ሊደረግባቸው ይገባል፤ አለበለዚያ ወጥመድ ይሆናሉ። (ሉቃስ 21:34–36) የይሖዋን በረከት ለማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች በሙሉ ነፍሳቸው የሚሠሩ መሆን አለባቸው እንጂ ፈጽሞ የተከፈለ ልብ ሊኖራቸው አይገባም። (ቆላ. 3:23, 24) እንዲህ ላሉት የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች አድናቆት ማሳደራቸው በመንፈሳዊ እንዲያድጉ መንገድ ሊከፍትላቸው ይችላል።

14 በሩ ክፍት ነው፦ እውነተኛው አምልኮ የሚቀርብበት የይሖዋ ቤት ከሁሉም በላይ ከፍ ከፍ ብሏል። “ኑ፣ ወደ እግዚአብሔር [ይሖዋ አዓት] ተራራ፣ . . . እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፣ በጎዳናውም እንሄዳለን” የሚለው ግብዣ በዓለም ዙሪያ በ229 አገሮች ውስጥ እየተስተጋባ ነው። (ኢሳ. 2:3) አዲሶች የሚሰጡት አዎንታዊ ምላሽ ሕይወታቸውን ሊያድንላቸው ይችላል። ትኩረታቸውን ወደ ይሖዋ ድርጅት እንዲያዞሩ ማድረግ እነርሱን ልንረዳ ከምንችልባቸው በጣም ጥሩ መንገዶች አንዱ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ