መጽሐፍ ቅዱስ ያለውን ኃይል ተመልከቱ!
እንዴት? መጽሐፍ ቅዱስ—በአንተ ሕይወት ውስጥ ያለው ኃይል (እንግሊዝኛ) የተባለውን ቪዲዮ በመመልከት ነው። ይህ ቪዲዮ መጽሐፍ ቅዱስ—የእውነትና የትንቢት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) የሚል ርዕስ ካላቸው ተከታታይ የቪዲዮ ክሮች መካከል ሦስተኛው ክፍል ነው።
የተሳካ ትዳር ለመመሥረት ትፈልጋለህ? አስቸጋሪ የሆኑ ወቅቶችን ለመወጣት እርዳታ ያስፈልግሃል? ወጣቶች ኃላፊነት የሚሰማቸው ጎልማሶች ሆነው ማደግ የሚችሉት እንዴት ነው? ይህ ቪዲዮ እንደሚያቀርበው መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳን ይችላል። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ በሕይወታቸው ውስጥ ያሳደረባቸውን በጎ ተጽእኖ ሲናገሩ አዳምጡ። መሠረታዊ ሥርዓቶቹ ዘመናዊው ኑሮ የሚያስከትላቸውን ችግሮች እንዲወጡ እንዴት እንደረዳቸው ሲገልጹ አዳምጡ።
ይህ ቪዲዮ ፍላጎት ያሳዩ አዳዲስ ሰዎች የአምላክን ቃል በሕይወታቸው ውስጥ መመሪያ አድርገው መጠቀማቸው ምን ያህል ዋጋ እንዳለው እንዲገነዘቡ የሚረዳ ጠቃሚ መሣሪያ ነው። ማኅበሩ መጽሐፍ ቅዱስ—በአንተ ሕይወት ውስጥ ያለው ኃይል የተባለው ቪዲዮ አለው። በጉባኤው የጽሑፍ አገልጋይ በኩል አንድ ቅጂ እንዲላክላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ።