እንዴት እንደምታዳምጡ ተጠበቁ
በጉባኤ፣ በአውራጃ እንዲሁም በልዩና በወረዳ ስብሰባዎች ላይ በትኩረት ማዳመጥ በጣም አስፈላጊ ነው። (ሉቃስ 8:18 NW ) የማዳመጥ ችሎታህን እንዴት ማሻሻል ትችላለህ?
◼ ከስብሰባ በፊት ከባድ ምግብ ከመብላት ተቆጠብ።
◼ አእምሮህ እንዲባዝን አትፍቀድ።
◼ ዋና ዋና ነጥቦችን በአጭሩ በማስታወሻህ ላይ ጻፍ።
◼ ጥቅስ ሲነበብ እያወጣህ ተከታተል።
◼ አጋጣሚው ሲገኝ ተሳትፎ አድርግ።
◼ እየቀረበ ባለው ትምህርት ላይ አሰላስል።
◼ የሰማኸውን ሥራ ላይ ስለምታውልበት መንገድ አስብ።
◼ በመጨረሻም የተማርከውን ለሌሎች ተናገር።
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ጥናት 5ን ተመልከት።