የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/00 ገጽ 7
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የJW.ORG አድራሻ ካርድን በሚገባ እየተጠቀማችሁበት ነው?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 4/00 ገጽ 7

የጥያቄ ሣጥን

◼ በአውራጃ ስብሰባ ወቅት ደረት ላይ የሚለጠፈው ካርድ መሰጠት የሚኖርበት ለማን ነው?

በትልልቅ ስብሰባዎች ወቅት ደረት ላይ የሚለጠፉት ካርዶች ወንድሞቻችንን ለይተን እንድናውቃቸው ከማስቻላቸውም በላይ ስብሰባውን በማስተዋወቅ ረገድ በጣም ጠቃሚ ናቸው። ይሁን እንጂ እነዚህ ካርዶች እንዲሁ ለሁሉም ሰው መታደል አይኖርባቸውም። አንድ ሰው ይህን ካርድ ካደረገ በሌሎች ዘንድ የሚታየው ከይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤ ጋር እንደሚ​ተባበር ጥሩ አቋም ያለው ሰው ተደርጎ ነው።

ካርዱ የግለሰቡን ስምና የጉባኤውን ስም ለመጻፍ የሚያስችል ቦታ አለው። ስለሆነም ካርዱን የሚያደርገው ሰው በተወሰነ መጠንም ቢሆን ከተገለጸው ጉባኤ ጋር ሲተባበር የቆየ መሆን አለበት። ማህበሩ ለእያንዳንዱ ጉባኤ የተወሰነ መጠን ያለው ካርድ ይልካል። ስለዚህ እያንዳንዱ የተጠመቀና ያልተጠመቀ አስፋፊ ካርዱን ማግኘቱ ተገቢ ነው። ከዚህም በተጨማሪ አዘውትረው በስብሰባዎች ላይ የሚገኙና በመስክ አገልግሎት ለመካፈል በዝግጅት ላይ ያሉ ልጆች ወይም ሌሎች ሰዎች ካርዱን ማግኘት ይችላሉ። ሆኖም በአውራጃ ስብሰባ ወቅት ደረት ላይ የሚለጠፈውን ካርድ ለተወገደ ግለሰብ መስጠት ተገቢ አይሆንም።

ጉባኤው ካርዶቹ ሲደርሱት በመመሪያው መሠረት መሰራጨታቸውን ሽማግሌዎች ማረጋገጥ አለባቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ