የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/00 ገጽ 8
  • ‘ብቁ መሆናቸው ይፈተን’—እንዴት?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ብቁ መሆናቸው ይፈተን’—እንዴት?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የጉባኤ አገልጋዮች ጠቃሚ ሥራ ያከናውናሉ
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
  • ወንድሞች—የጉባኤ አገልጋይ ለመሆን እየተጣጣራችሁ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • በሽማግሌዎችና በዲያቆናት መካከል ያለውን ስምምነት መጠበቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ሽማግሌዎች—ኃላፊነት እንዲሸከሙ ሌሎችን አሠልጥኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 5/00 ገጽ 8

‘ብቁ መሆናቸው ይፈተን’​—⁠እንዴት?

1 የይሖዋ ድርጅት የሚያደርገው ቀጣይ እድገት የጉባኤ አገልጋይ የሚሆኑ ብቃት ያላቸው ወንድሞች ከሥር ከሥር እንዲገኙ የሚጠይቅ ነው። በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙትን ጨምሮ ይህንን መብት ያላገኙ ብዙ ወንድሞች በጉባኤ ውስጥ የማገልገል ፍላጎት አላቸው። ተጨማሪ ሥራ እንዲሠሩ ሲመደቡ ጠቃሚ እንደሆኑና አንድ ነገር እንዳከናወኑ ይሰማቸዋል። ሆኖም ተጨማሪ ዕድገት ማድረጋቸው የተመካው ‘ተፈትነው ብቁ በመሆናቸው’ ላይ ነው። (1 ጢ⁠ሞ. 3:​10 NW ) ብቁ መሆናቸው የሚፈተነው እንዴት ነው?

2 የሽማግሌዎች ድርሻ:- ሽማግሌዎች በ1 ጢሞቴዎስ 3:​8-13 ላይ ለጉባኤ አገልጋዮች የወጣውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ብቃት ተንተርሰው የአንድን ወንድም ብቃት ሲመዝኑ ኃላፊነት ለመሸከም ያለውን ብቃት ይመረምራሉ። ምናልባትም መጽሔቶች​ንና ጽሑፎችን ከማከፋፈል፣ የድምፅ ማጉያ መሣሪያዎችን ከማስተካከል፣ አዳራሹን ከመጠገንና ከመሳሰሉት ጋር በተያያዘ ጠቃሚ አገልግሎት እንዲሰጥ ይመድቡት ይሆናል። ሽማግሌዎች ይህ ወንድም ሥራ ሲሰጠው የሚያሳየውን ምላሽና ኃላፊነቱን እንዴት እንደሚወጣ ይከታተላሉ። እምነት የሚጣልበት፣ ሰዓት አክባሪ፣ ትጉህ፣ ልከኛ፣ የፈቃደኝነት መንፈስ የሚያሳይ እንዲሁም ከሌሎች ጋር ተስማምቶ የመሥራት ችሎታ ያለው መሆኑን ይመለከታሉ። (ፊልጵ. 2:​20) በአለባበሱና በሰውነት አያያዙ ምሳሌ የሚሆን ነው? የኃላፊነት ስሜት ይሰማዋል? ‘በመልካም አንዋዋሩ ሥራውን በጥበብ የዋህነት ሲያሳይ’ መመልከት ይፈልጋሉ። (ያዕ. 3:​13) ጉባኤውን በአንዳንድ ነገር ለማገዝ ከልቡ ይጣጣራል? በመስክ አገልግሎት በቅንዓት በመካፈል ኢየሱስ ‘ደቀ መዛሙርት አድርጉ’ በማለት የሰጠውን ትእዛዝ እየፈጸመ ነው?​—⁠ማቴ. 28:​19፤ መጠበቂያ ግንብ 17-111 ገጽ 18-28ን ተመልከት።

3 በጉባኤ አገልጋይነት ለመሾም መነሻ የሆነ የተወሰነ የዕድሜ ገደብ ባይኖርም መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ወንድሞች “የሚያገለግሉ ወንዶች [NW ]” በማለት ይጠራቸዋል። ስለዚህ በአሥራዎቹ ዕድሜ መጀመሪያ ወይም አጋማሽ ላይ ይሆናሉ ብለን አንጠብቅም። ምክንያቱም ሚስትና ልጆች ሊኖራቸው የሚችልበት አጋጣሚ እንዳለ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሷል። (1 ጢሞ. 3:​12, 13) እነዚህ ወንድሞች ‘ለጎልማሳነት ምኞት የሚሸነፉ’ መሆን የለባቸውም። ከዚህ ይልቅ ቁም ነገረኞች እንዲሁም በአምላክና በሰው ፊት መልካም ምግባር ያላቸውና ንጹህ ሕሊና ያተረፉ ሊሆኑ ይገባል።​—⁠2 ጢ⁠ሞ. 2:​22

4 የአንድ ሰው ተፈጥሮአዊ ችሎታ ጠቃሚ ቢሆንም ዋናው ነገር ዝንባሌውና ውስጣዊ ግፊቱ ነው። በትህትና ራሱን ዝቅ አድርጎ ለአምላክ ክብር ለማምጣትና ወንድሞቹን ለማገልገል ይፈልጋል? እንዲህ ከሆነ በጉባኤ ውስጥ ለማደግ የሚያደርገውን ጥረት ይሖዋ ይባርክለታል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ