የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/00 ገጽ 3-4
  • ራሳችሁን እየጠቀማችሁ ነውን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ራሳችሁን እየጠቀማችሁ ነውን?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 11 በምታደርጓቸው የግል ምርጫዎች ረገድ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ምክር ያዘለ ንግግር ስትሰሙ ይሖዋ በቀጥታ ለእናንተ እየተናገራችሁ እንዳለ ሆኖ ይሰማችኋል? አንድ ወንድም ልክ እንደዚህ ተሰምቶታል። እንዲህ ሲል ተናግሯል:- “በቅርብ ጊዜ ባደረግነው አንድ ስብሰባ ላይ አንድ ወንድም ለክርስቲያኖች ተገቢ ስለሆነና ስላልሆነ የመዝናኛ ዓይነት ንግግር ሰጥቶ ነበር። የቦክስ ጨዋታ በቴሌቪዥን መመልከት እወድ ነበር። ሆኖም ከዚህ ስብሰባ በኋላ ይህ ጨዋታ ለክርስቲያኖች ተገቢ ካልሆኑት የመዝናኛ ዓይነቶች መካከል የሚመደብ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ በመድረሴ ጨዋታውን መመልከቴን አቆምኩ።” አዎን፣ ይህ ወንድም የዓመፅ ድርጊት ለሚፈጸምበት መዝናኛ ፍቅር አድሮበት የነበረ ቢሆንም ለይሖዋ መመሪያ በትህትና ምላሽ ሰጥቷል።​—⁠መዝ. 11:​5
  • 12 የሕዝብ ስብሰባ፣ የመጠበቂያ ግንብ ጥናትና የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት:- በየሳምንቱ የምንሰማቸው የሕዝብ ንግግሮች ልዩ ልዩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ርዕሰ ጉዳዮችን ይሸፍናሉ። ከእነዚህ ንግግሮች ምን ጥቅም እያገኛችሁ ነው? አንድ ክርስቲያን ባል ያገኛቸውን ጥቅሞች እንዲህ ሲል ገልጿል:- “በአንድ ወቅት በመንፈስ ፍሬዎች ላይ ያተኮረ የሕዝብ ንግግር የቀረበ ሲሆን ተናጋሪውም የራሱን ምሳሌ ጠቅሶ ነበር። እነዚህን የመንፈስ ፍሬዎች ለማዳበር ሲል አንዱን የመንፈስ ፍሬ ይመርጥና ለአንድ ሳምንት ያህል ይህንን ፍሬ ለማፍራት ጥረት ያደርጋል። ከዚያም በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በዕለታዊ እንቅስቃሴው ይህንን ፍሬ በማፍራት ረገድ ምን ያህል እንደተሳካለት ቆም ብሎ ያስባል። በቀጣዩ ሳምንት ደግሞ ሌላ የመንፈስ ፍሬ ለማፍራት እንዲሁ ጥረት ያደርጋል። ሐሳቡን ስለወደድኩት እኔም እንዲሁ ማድረግ ጀመርኩ።” የተማሩትን በሥራ ላይ በማዋል ረገድ እንዴት ያለ ግሩም ምሳሌ ነው!
  • 13 የመጠበቂያ ግንብ ጥናት የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች በተለያዩ የሕይወታችን ዘርፎች ተግባራዊ እንድናደርጋቸው ያስተምረናል። እንዲህ ማድረጋችን ደግሞ የኑሮ ጭንቀቶች ቢኖሩም እንኳ የተረጋጋ አእምሮና ልብ እንዲኖረን ይረዳናል። የመጠበቂያ ግንብ ጥናት በየጊዜው እየደመቀ ከሚሄደው የእውነት እውቀት ጋር እኩል እንድንራመድ ያስችለናል። ለምሳሌ፣ “ይህ ሊሆን ግድ ነውና፣” “አንባቢው ያስተውል፣” እንዲሁም “ንቁዎችና ትጉዎች ሁኑ!” ከሚሉት የግንቦት 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ የጥናት ርዕሶች ጥቅም አላገኘንምን? እነዚህ የጥናት ርዕሶች በግል የነኳችሁ እንዴት ነው? ኢየሱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ከልብ እንደተቀበላችሁት በተግባራችሁ ታሳያላችሁ? ‘የጥፋት ርኲሰት በተቀደሰው ስፍራ ቆሞ’ በምናይበት ወቅት ለሚገጥመን ፈተና ራሳችሁን በማዘጋጀት ላይ ናችሁ? (ማቴ. 24:​15-22) ከሁሉ ይበልጥ የሚያሳስባችሁ ቁሳዊ ነገሮችን መሰብሰብ ሳይሆን የይሖዋ ስም መቀደስ እንደሆነ ግቦቻችሁና አኗኗራችሁ በግልጽ ያሳያሉን? አሁንም እንኳ በመጠበቂያ ግንብ ጥናት አማካኝነት ራሳችንን እንዴት እንደምንጠቅም እየተማርን አይደለምን?
  • 14 በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ ደግሞ በየሳምንቱ ምን ያህል እንደምንማር አስቡ። በቅርቡ ታላቅ ሰው የተባለውን መጽሐፍ አጥንተን ጨርሰናል። ስለ ኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ማጥናታችን የኢየሱስን ምሳሌ በቅርብ እንድንከተልና ይሖዋን በይበልጥ እንድናውቀው አላስቻለንምን?
  • 15 ይሖዋ ተደስተን እንድንኖር ያስተምረናል:- የይሖዋን መመሪያዎች ትኩረት ሰጥተን ከተከታተልን ከብዙ ሐዘን ልንጠበቅ እንችላለን። በተጨማሪም አስደሳች ሕይወት ምን እንደሚመስል የማየት አጋጣሚ እናገኛለን። የይሖዋን አመራር የምንከተል ከሆነ ዳር ቆመን የምንታዘብ ከመሆን ይልቅ በሥራው ተካፋዮች እንሆናለን። የአምላክን ሥራ በመሥራት ላይ ያሉ ሰዎች ደግሞ ደስተኞች ናቸው።​—⁠1 ቆ⁠ሮ. 3:​9፤ ያዕ. 1:​25
  • 16 በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ የምትማሯቸውን ነገሮች እንዴት ተግባራዊ እንደምታደርጓቸው በንቃት አስቡ። (ዮሐ. 13:​17) አምላክን በሙሉ ልብና በጋለ ስሜት ካገለገላችሁ የተትረፈረፈ ደስታ ከማግኘታችሁም በላይ ሕይወታችሁ የበለጸገና ይበልጥ ትርጉም ያለው ይሆናል። አዎን፣ ራሳችሁን ትጠቅማላችሁ።
  • ‘ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች የሚያነቃቁ’ ስብሰባዎች
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
  • ለአምልኮ መሰብሰብ
    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
  • ስብሰባዎች ለወጣቶች ጠቃሚ ናቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ለፍቅርና ለመልካም ሥራ የሚያነቃቁ ስብሰባዎች
    እንደ አንድ አካል ሆነው በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 8/00 ገጽ 3-4

ራሳችሁን እየጠቀማችሁ ነውን?

1 ዛሬ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ያሉባቸውን ችግሮች በማሸነፍ ደስተኛ ሕይወት መምራት የሚችሉበትን መንገድ ለማወቅ ይፈልጋሉ። ሕይወታቸውን የተሻለ ለማድረግ የሚያስችል ምክር ለማግኘት ራስ አገዝ መጻሕፍትን በጉጉት ያነባሉ ወይም ደግሞ የተለያዩ ቡድኖችንና ድርጅቶችን ይጠይቃሉ። ምናልባት አንዳንዶች እንዲህ በማድረጋቸው ያገኙዋቸውን አንዳንድ ጥቅሞች መናገር ይችሉ ይሆናል። ይሁን እንጂ ዛሬ ያለውን ሕይወት ስንመለከት ጠቅላላው የሰው ዘር የሰዎችን መመሪያ ተከትሎ ሰላማዊና አርኪ ሕይወት መምራት ችሏልን? በፍጹም!​—⁠1 ቆ⁠ሮ. 3:​18-20

2 በሌላው በኩል ግን ፈጣሪያችን ለሚያዳምጡት ሁሉ በጣም ጠቃሚ የሆነ መመሪያ ያለ ክፍያ ይሰጣል። ይሖዋ እያንዳንዱ ሰው እርሱ ካዘጋጀው የትምህርት መርሃ ግብር ተጠቃሚ እንዲሆን ይፈልጋል። ይሖዋ የሰው ዘሮችን በጽድቅ ለመምራት ሲል በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ቃሉን በልግስና ከመስጠቱም በላይ የመንግሥቱ ምሥራች በመላው ምድር እንዲሰበክ አድርጓል። (መዝ. 19:​7, 8፤ ማቴ. 24:​14፤ 2 ጢ⁠ሞ. 3:​16) እውነተኛ ደስታ የሰፈነበት ሕይወት ለይሖዋ ትእዛዛት ትኩረት ከመስጠት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው።​—⁠ኢሳ. 48:​17, 18

3 የይሖዋ መመሪያ ዓለም በራስ አገዝ መጻሕፍትም ሆነ የራስን ሕይወት ያሻሽላሉ በሚባሉ ዘዴዎች አማካኝነት ከሚያቀርባቸው መመሪያዎች ሁሉ እጅግ የላቀ ነው። በቃሉ ውስጥ የተዘረዘሩትንና በድርጅቱ በኩል የምንማራቸውን የይሖዋ ዝግጅቶች ሙሉ በሙሉ ከተጠቀምንባቸው እውነተኛ እርዳታና ዘላቂ ጥቅም ማግኘት እንችላለን።​—⁠1 ጴ⁠ጥ. 3:​10-12

4 በጉባኤ ስብሰባዎች ራስን መጥቀም:- በዛሬው ጊዜ ይሖዋ ስለ መንገዶቹ እኛን ለማስተማር ልባዊ ፍላጎት ያለው ሲሆን እኛ ደግሞ ለትምህርቱ ትኩረት በመስጠት ጥቅም እናገኛለን። አምስቱ ሳምንታዊ የጉባኤ ስብሰባዎቻችን የይሖዋን ፍቅራዊ አሳቢነት የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ናቸው። በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ስንገኝ ስለ አምላክ ያለን እውቀት ይጨምራል። ወደ ይሖዋ በመቅረብ ራሳችንን መጥፎ ከሆነው ነገር መጠበቅ የምንችልበትን መንገድ ስለምንማር መንፈሳችን ይነቃቃል።

5 ሌላም የምናገኘው ጥቅም አለ። በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ስንገኝ “ተስፋፉ” የሚለውን ምክር ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን። (2 ቆ⁠ሮ. 6:​13) ይህም በጉባኤ ውስጥ ከሚገኙት ሌሎች ሰዎች ጋር መተዋወቅን ይጨምራል። ሐዋርያው ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ የገለጸውን የመሰለ ማበረታቻ ከሌሎች ጋር በመለዋወጥ ጥቅም እናገኛለን። (ሮሜ 1:​11, 12) ጳውሎስ ለዕብራውያን በጻፈ ጊዜ ከስብሰባዎች የመቅረት ልማድ በማዳበር ላይ ለነበሩት ክርስቲያኖች ጠንከር ያለ ምክር ሰጥቶአቸዋል።​—⁠ዕብ. 10:​24, 25

6 በሕይወት ውስጥ እርካታና ደስታ ማግኘት ለሌሎች ደህንነት ከማሰብ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። በስብሰባዎች ላይ ለሌሎች ደስታ አስተዋጽኦ ማድረግ የምንችልባቸውን መንገዶች እንድንፈልግ እንበረታታለን። በእርግጥም ክርስቲያናዊ ስብሰባዎች እኛንም ሆነ ከእኛ ጋር የሚሰበሰቡትን ሌሎች ሰዎች ይጠቅማሉ። ከእኛ የሚፈለገው ልባዊ ተሳትፎ ማድረግ ነው።

7 ሐዋርያው ጳውሎስ “እግዚአብሔርን ለመምሰል [“ለአምላክ ማደርን፣” NW ] ግን ራስህን አስለምድ” በማለት ጢሞቴዎስን በመከረው ጊዜ ተመሳሳይ ነጥብ ጠቅሷል። (1 ጢ⁠ሞ. 4:​7) እኛም ራሳችንን እንዲህ እያልን መጠየቅ እንችላለን:- ‘ራሴን እያሰለጠንኩ ነው? በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ከምሰማቸው ነገሮች ጥቅም ማግኘትን እየተማርኩ ነው?’ በስብሰባዎች ላይ የሚቀርቡትን ትምህርቶች ትኩረት ሰጥተን ከተከታተልንና የተማርነውን በተግባር ላይ ለማዋል ጥረት ካደረግን ለእነዚህ ጥያቄዎች የምንሰጠው መልስ አዎን የሚል ይሆናል። የእምነት ዓይናችንን በመጠቀም ትምህርቱን ከሚያቀርቡት ወንድሞች ባሻገር ማየትና ይሖዋ ታላቅ የሕዝቦቹ አስተማሪ መሆኑን መመልከት ይኖርብናል።​—⁠ኢሳ. 30:​20

8 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤትና የአገልግሎት ስብሰባ:- እነዚህ ሁለት ስብሰባዎች በክርስቲያናዊ አገልግሎታችን ውጤታማ እንድንሆን ታስበው የተዘጋጁ ናቸው። የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት የተዘጋጀው ለዚህ ዓላማ ሲሆን ተማሪዎች ዘወትር ትምህርትና ምክር ያገኙበታል። የሕዝብ ተናጋሪዎችና የአምላክ ቃል አስተማሪዎች በመሆን ረገድ ያደረጋችሁትን መሻሻል ማሳየት የምትችሉበት አጋጣሚ አላችሁ። ሆኖም ከትምህርት ቤቱ ሙሉ ጥቅም ለማግኘት መመዝገብ፣ በስብሰባው ላይ መገኘት፣ አዘውትሮ መሳተፍና የተሰጣችሁን ክፍል በደንብ አስባችሁበት መዘጋጀት ይኖርባችኋል። የሚሰጣችሁን ምክር መቀበላችሁና በተግባር ላይ ማዋላችሁ እድገት እንድታደርጉ ይረዳችኋል።

9 የአገልግሎት ስብሰባ ደግሞ የክርስቲያናዊ አገልግሎትን አስፈላጊነት ያስተምረናል። እንዲሁም ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ መካፈል የምንችልበትን መንገድ ያሳየናል። አንተና ቤተሰብህ በእነዚህ ሁለት ስብሰባዎች ላይ ከሚቀርቡት ትምህርቶች ሙሉ በሙሉ በመጠቀም ላይ ናችሁ? አንድ ክርስቲያን ባልና ሚስት “በአንድ የአገልግሎት ስብሰባ ላይ የዕለት ጥቅስን በቤተሰብ መልክ መመርመር እንደሚገባን ሲነገር ሰማን። በፊት እንዲህ አድርገን የማናውቅ ቢሆንም አሁን ግን የዕለቱን ጥቅስ በቤተሰብ መልክ አንድ ላይ እናነባለን” ሲሉ ተናግረዋል። እነዚህ ባልና ሚስት ራሳቸውን የጠቀሙት እንዴት ነው? እንዲህ ሲሉ ሳይሸሽጉ ተናግረዋል:- “ምግብ በምንመገብበት ወቅት የምናደርጋቸው ውይይቶች ይበልጥ አስደሳች ሆነውልናል። በእራት ሰዓት መከራከራችንንም አቁመናል።” ትንንሽ ልጆችስ ከስብሰባዎች ይጠቀሙ ይሆን? አዎን። እናትየዋ እንዲህ ስትል ተናግራለች:- “ልጆቻችን ስብሰባዎች ላይ በሚቀርቡት ትምህርቶች በጥልቅ እንደተነኩ ግልጽ ነው። በተለይ አንድ ወቅት ላይ የስድስት ዓመቱ ልጃችን ሲዋሽ አገኘነው። ሆኖም የዚያ ሳምንት የማስተማሪያ ንግግር ስለ ውሸት የሚናገር ነበር። ልጃችን ጥፋቱ እንደተሰማው በሚገልጽ ሁኔታ አባቱን ከተመለከተ በኋላ በኀፍረት አቀረቀረ። ነጥቡ ገብቶት ስለነበር ከዚያ በኋላ ምንም ችግር አልገጠመንም።”

10 አንዲት አቅኚ እህት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ አገልግሎታችንን ለማሻሻል የሚረዱ ሐሳቦች ስለሚቀርቡ አመስጋኝ መሆኗን ገልጻለች። ለምን? እንዲህ ስትል ታብራራለች:- “አንዳንዴ አሰልቺ ድግግሞሽ ይሆንብኛል። በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የቀረቡት ሐሳቦች እንደማይሠሩ ሆኖ የሚሰማኝ ጊዜ አለ። ሆኖም በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ሐሳቦቹን መሞከር እንዳለብን ስሰማ ሐሳቦቹን ተግባራዊ የማድረግ ጉጉት ያድርብኛል። ይህም አገልግሎቴን አስደሳች ያደርገዋል!” ሰዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ስታነጋግሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ሞክሩ የሚለውን ምክር ተግባራዊ ለማድረግ ለበርካታ ሳምንታት ጥረት ካደረገች በኋላ እርዳታ ለማግኘት ትጸልይ የነበረች አንዲት ሴት አገኘችና በመጀመሪያው ውይይታቸው ጥናት አስጀመረቻት።

11 በምታደርጓቸው የግል ምርጫዎች ረገድ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ምክር ያዘለ ንግግር ስትሰሙ ይሖዋ በቀጥታ ለእናንተ እየተናገራችሁ እንዳለ ሆኖ ይሰማችኋል? አንድ ወንድም ልክ እንደዚህ ተሰምቶታል። እንዲህ ሲል ተናግሯል:- “በቅርብ ጊዜ ባደረግነው አንድ ስብሰባ ላይ አንድ ወንድም ለክርስቲያኖች ተገቢ ስለሆነና ስላልሆነ የመዝናኛ ዓይነት ንግግር ሰጥቶ ነበር። የቦክስ ጨዋታ በቴሌቪዥን መመልከት እወድ ነበር። ሆኖም ከዚህ ስብሰባ በኋላ ይህ ጨዋታ ለክርስቲያኖች ተገቢ ካልሆኑት የመዝናኛ ዓይነቶች መካከል የሚመደብ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ በመድረሴ ጨዋታውን መመልከቴን አቆምኩ።” አዎን፣ ይህ ወንድም የዓመፅ ድርጊት ለሚፈጸምበት መዝናኛ ፍቅር አድሮበት የነበረ ቢሆንም ለይሖዋ መመሪያ በትህትና ምላሽ ሰጥቷል።​—⁠መዝ. 11:​5

12 የሕዝብ ስብሰባ፣ የመጠበቂያ ግንብ ጥናትና የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት:- በየሳምንቱ የምንሰማቸው የሕዝብ ንግግሮች ልዩ ልዩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ርዕሰ ጉዳዮችን ይሸፍናሉ። ከእነዚህ ንግግሮች ምን ጥቅም እያገኛችሁ ነው? አንድ ክርስቲያን ባል ያገኛቸውን ጥቅሞች እንዲህ ሲል ገልጿል:- “በአንድ ወቅት በመንፈስ ፍሬዎች ላይ ያተኮረ የሕዝብ ንግግር የቀረበ ሲሆን ተናጋሪውም የራሱን ምሳሌ ጠቅሶ ነበር። እነዚህን የመንፈስ ፍሬዎች ለማዳበር ሲል አንዱን የመንፈስ ፍሬ ይመርጥና ለአንድ ሳምንት ያህል ይህንን ፍሬ ለማፍራት ጥረት ያደርጋል። ከዚያም በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በዕለታዊ እንቅስቃሴው ይህንን ፍሬ በማፍራት ረገድ ምን ያህል እንደተሳካለት ቆም ብሎ ያስባል። በቀጣዩ ሳምንት ደግሞ ሌላ የመንፈስ ፍሬ ለማፍራት እንዲሁ ጥረት ያደርጋል። ሐሳቡን ስለወደድኩት እኔም እንዲሁ ማድረግ ጀመርኩ።” የተማሩትን በሥራ ላይ በማዋል ረገድ እንዴት ያለ ግሩም ምሳሌ ነው!

13 የመጠበቂያ ግንብ ጥናት የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች በተለያዩ የሕይወታችን ዘርፎች ተግባራዊ እንድናደርጋቸው ያስተምረናል። እንዲህ ማድረጋችን ደግሞ የኑሮ ጭንቀቶች ቢኖሩም እንኳ የተረጋጋ አእምሮና ልብ እንዲኖረን ይረዳናል። የመጠበቂያ ግንብ ጥናት በየጊዜው እየደመቀ ከሚሄደው የእውነት እውቀት ጋር እኩል እንድንራመድ ያስችለናል። ለምሳሌ፣ “ይህ ሊሆን ግድ ነውና፣” “አንባቢው ያስተውል፣” እንዲሁም “ንቁዎችና ትጉዎች ሁኑ!” ከሚሉት የግንቦት 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ የጥናት ርዕሶች ጥቅም አላገኘንምን? እነዚህ የጥናት ርዕሶች በግል የነኳችሁ እንዴት ነው? ኢየሱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ከልብ እንደተቀበላችሁት በተግባራችሁ ታሳያላችሁ? ‘የጥፋት ርኲሰት በተቀደሰው ስፍራ ቆሞ’ በምናይበት ወቅት ለሚገጥመን ፈተና ራሳችሁን በማዘጋጀት ላይ ናችሁ? (ማቴ. 24:​15-22) ከሁሉ ይበልጥ የሚያሳስባችሁ ቁሳዊ ነገሮችን መሰብሰብ ሳይሆን የይሖዋ ስም መቀደስ እንደሆነ ግቦቻችሁና አኗኗራችሁ በግልጽ ያሳያሉን? አሁንም እንኳ በመጠበቂያ ግንብ ጥናት አማካኝነት ራሳችንን እንዴት እንደምንጠቅም እየተማርን አይደለምን?

14 በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ ደግሞ በየሳምንቱ ምን ያህል እንደምንማር አስቡ። በቅርቡ ታላቅ ሰው የተባለውን መጽሐፍ አጥንተን ጨርሰናል። ስለ ኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ማጥናታችን የኢየሱስን ምሳሌ በቅርብ እንድንከተልና ይሖዋን በይበልጥ እንድናውቀው አላስቻለንምን?

15 ይሖዋ ተደስተን እንድንኖር ያስተምረናል:- የይሖዋን መመሪያዎች ትኩረት ሰጥተን ከተከታተልን ከብዙ ሐዘን ልንጠበቅ እንችላለን። በተጨማሪም አስደሳች ሕይወት ምን እንደሚመስል የማየት አጋጣሚ እናገኛለን። የይሖዋን አመራር የምንከተል ከሆነ ዳር ቆመን የምንታዘብ ከመሆን ይልቅ በሥራው ተካፋዮች እንሆናለን። የአምላክን ሥራ በመሥራት ላይ ያሉ ሰዎች ደግሞ ደስተኞች ናቸው።​—⁠1 ቆ⁠ሮ. 3:​9፤ ያዕ. 1:​25

16 በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ የምትማሯቸውን ነገሮች እንዴት ተግባራዊ እንደምታደርጓቸው በንቃት አስቡ። (ዮሐ. 13:​17) አምላክን በሙሉ ልብና በጋለ ስሜት ካገለገላችሁ የተትረፈረፈ ደስታ ከማግኘታችሁም በላይ ሕይወታችሁ የበለጸገና ይበልጥ ትርጉም ያለው ይሆናል። አዎን፣ ራሳችሁን ትጠቅማላችሁ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ