የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/02 ገጽ 3-6
  • ‘የአምላክን ቃል በተሟላ ሁኔታ ስበኩ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘የአምላክን ቃል በተሟላ ሁኔታ ስበኩ’
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 11 በጉባኤው ውስጥ ያሉት ሁሉ ‘የአምላክን ቃል በተሟላ ሁኔታ እንዲሰብኩ’ ለመርዳት ሽማግሌዎች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ? በስብሰባ ክፍሎችና በግል በምታደርጓቸው ጭውውቶች ቅንዓታቸውን ለመቀስቀስ ጣሩ። የመጽሐፍ ጥናት ቡድን መሪዎችና ረዳቶቻቸው ቅድሚያውን ወስደው በቡድናቸው ውስጥ የሚገኘውን እያንዳንዱን አስፋፊ ሊያነጋግሩና በግል ሊያበረታቱት ይችላሉ። ደግነት የተሞላባቸው ጥቂት የማበረታቻ ቃላት ወይም ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ የተወሰኑ ሐሳቦች ብቻ በቂ ሊሆኑ ይችላሉ። (ምሳሌ 25:11) ብዙዎች በፕሮግራማቸው ላይ መጠነኛ ማስተካከያ በማድረግ በረዳት አቅኚነት የማገልገል መብት ማግኘት እንደሚችሉ ይረዳሉ። በበርካታ ጉባኤዎች ውስጥ ያሉ ሽማግሌዎችና የጉባኤ አገልጋዮች እንዲሁም ሚስቶቻቸው፣ ሁሉም ለማለት ይቻላል በመታሰቢያው በዓል ወራት አብረው በረዳት አቅኚነት በማገልገል ግሩም ምሳሌ ሆነዋል። ይህም ብዙ አስፋፊዎችን እንደ እነሱ ረዳት አቅኚ እንዲሆኑ አበረታቷቸዋል። በአንዳንድ አካላዊ የአቅም ገደቦች ወይም በሌሎች ሁኔታዎች የተነሳ አንዳንድ አስፋፊዎች አቅኚ ሆነው ማገልገል አይችሉ ይሆናል፤ ቢሆንም ከሌሎች የጉባኤው አባላት ጋር አብረው ሆነው አቅማቸው የፈቀደውን ያህል በአገልግሎቱ በመካፈል አድናቆታቸውን እንዲያሳዩ ማበረታታት ይቻላል።
  • 12 ሽማግሌዎች በሚገባ የታሰበበት እቅድ ካወጡ ጥሩ ውጤት ሊገኝ ይችላል። የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ በሳምንቱ ውስጥ ተስማሚ በሆኑ ሰዓቶች እንዲደረግ ፕሮግራም ሊወጣለት ይገባል። የሚቻል ከሆነ የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ሁሉንም የአገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች የሚመሩ ብቃት ያላቸው ወንድሞችን አስቀድሞ ይመድባል። እነዚህ ስብሰባዎች በቡድን መመደብን፣ የአገልግሎት ክልል መስጠትንና ጸሎትን ጨምሮ ከ10 እስከ 15 ደቂቃዎች እንዳይበልጡ ጥሩ ዝግጅት ያስፈልጋል። (በመስከረም 2001 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚገኘውን የጥያቄ ሣጥን ተመልከት።) የወሩ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ለጉባኤው በግልጽ መነገር እንዲሁም በማስታወቂያ ሰሌዳው ላይ መለጠፍ አለበት።
  • 13 በቂ የአገልግሎት ክልል ሊኖር ይገባል። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ከክልል አገልጋዩ ጋር በመነጋገር በተደጋጋሚ ያልተሸፈኑ ክልሎችን ለመሸፈን ዝግጅቶችን ማድረግ አለበት። በቤታቸው የማይገኙ ሰዎችን ለማግኘት፣ ከመንገድ ወደ መንገድ እና ከሱቅ ወደ ሱቅ ለመመሥከር እንዲሁም በምሽት ምሥክርነት ለመካፈል ልዩ ጥረት ሊደረግ ይገባል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ አንዳንድ አስፋፊዎች በስልክ እንዲመሰክሩ ማበረታቻ መስጠት ይቻላል።
  • 14 በድጋሚ በአገልግሎት መካፈል እንዲጀምሩ እርዷቸው:- በጉባኤያችሁ ክልል ውስጥ ምስራቹን በመስበኩ ሥራ መሳተፍ ያቆሙ አሉ? እንዲህ ዓይነቶቹ አሁንም የጉባኤው ክፍል ስለሆኑ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። (መዝ. 119:176) የዚህ አሮጌ ዓለም መጨረሻ በጣም ስለቀረበና በአዲሱ ዓለም ደፍ ላይ ስለምንገኝ አገልግሎት ያቆሙትን ለመርዳት የምንችለውን ሁሉ ጥረት ማድረጋችን የተገባ ነው። (ሮሜ 13:11, 12) በየዓመቱ ብዙዎች ለተደረገላቸው እርዳታ ምላሽ በመስጠት አገልግሎት ይጀምራሉ። ሌሎች ተጨማሪ አስፋፊዎች ቀደም ሲል ለአገልግሎቱ የነበራቸውን ፍቅርና ድፍረት መልሰው እንዲያቀጣጥሉ ለመርዳት ምን ማድረግ እንችላለን?​—⁠ዕብ. 3:12-14
  • 15 የሽማግሌዎች አካል ባለፉት ጥቂት ዓመታት አገልግሎት አቁመው የነበሩትን እንዴት መርዳት እንደሚችል መወያየት ይፈልግ ይሆናል። (ማቴ. 18:12-14) የጉባኤው ጸሐፊ የጉባኤውን የአስፋፊዎች ካርድ በመመርመር አገልግሎት ያቆሙትን ሁሉ በማስታወሻ መመዝገብ አለበት። የእረኝነት ጉብኝት በማድረግ እነዚህን አስፋፊዎች ለመርዳት ልዩ ጥረት መደረግ አለበት። አንድ ሽማግሌ አገልግሎት ካቆመው ግለሰብ ጋር ጓደኝነት ወይም ቅርርብ የነበረው አንድ አስፋፊ ይህን ሰው እንዲረዳው ሊያደርግ ይችላል፤ ወይም ሌሎች አስፋፊዎች እንዲረዱት ሊጠይቅ ይችላል። ምናልባት አገልግሎት ያቆመውን አስፋፊ ያስጠኑት እነሱ ከሆኑ እርዳታ በሚፈልግበት በዚህ ወቅት የቅርብ እርዳታ ሊያደርጉለት መቻላቸው ያስደስታቸው ይሆናል። አገልግሎት ካቆሙት አስፋፊዎች ውስጥ ብዙዎቹ በድጋሚ የአምላክን ቃል መስበክ ለመጀመር እንደሚነሳሱ ተስፋ እናደርጋለን። ብቃቱን የሚያሟሉ ከሆኑ አገልግሎት ለመጀመር ከመታሰቢያው በዓል ወራት የተሻለ ጊዜ የለም!​—⁠ለተጨማሪ ማብራሪያ በኅዳር 2000 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ያለውን የጥያቄ ሣጥን ተመልከት።
  • 16 ለአስፋፊነት ሊበቁ የሚችሉ ሌሎች ይኖሩ ይሆን? ይሖዋ ‘በአሕዛብ ሁሉ የተመረጡትን ዕቃዎች’ በማምጣት ሕዝቡን መባረኩን ቀጥሏል። (ሐጌ 2:7) በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ለመሆን ብቃቱን ያሟላሉ። እነዚህ እነማን ናቸው? የይሖዋ ምሥክሮች ልጆችና እድገት የሚያደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ናቸው። የምሥራቹ አስፋፊዎች ለመሆን ብቁ እንደሆኑና እንዳልሆኑ እንዴት ማወቅ እንችላለን?
  • 17 የይሖዋ ምሥክሮች ልጆች:- ብዙ ልጆች ያልተጠመቁ አስፋፊ ባይሆኑም ለብዙ ዓመታት ከወላጆቻቸው ጋር ሆነው ከቤት ወደ ቤት ሲሄዱ ቆይተዋል። ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ለመሆን መጋቢት ጥሩ ጊዜ ሊሆንላቸው ይችላል። ልጅህ ብቁ እንደሆነና እንዳልሆነ እንዴት ታውቃለህ? አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት የተባለው መጽሐፍ በገጽ 100 ላይ “አንድ ልጅ በጠባዩ ጥሩ ምሳሌ ከሆነና ስለ ምሥራቹ ለሌሎች በመናገር እምነቱን ከራሱ በመነጨ ሐሳብ ለመግለጽ ከቻለ እንዲሁም ይህንን ከልቡ ተነሳስቶ ካደረገ” ብቁ እንደሆነ ይናገራል። ልጅህ ብቁ እንደሆነ ከተሰማህ የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ አባል የሆነ አንድ ሽማግሌ አነጋግር።
  • 18 ለአስፋፊነት የሚበቁ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች:- አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እውቀት ካገኘና ለተወሰነ ጊዜ በስብሰባዎች ላይ ከተገኘ በኋላ የመንግሥቱ አስፋፊ መሆን ይፈልግ ይሆናል። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪህ ይህን ዓይነት ፍላጎት ካሳየ እነዚህን ጥያቄዎች አስብባቸው:- ከዕድሜውና ከችሎታው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ እድገት እያደረገ ነው? መደበኛ ባልሆነ መንገድ እምነቱን ለሌሎች ማካፈል ጀምሯል? “አዲሱን ሰው” እየለበሰ ነው? (ቆላ. 3:10) በአገልግሎታችን መጽሐፍ ገጽ 97-99 ላይ የተዘረዘሩትን ያልተጠመቀ አስፋፊ ለመሆን የሚያስፈልጉ ብቃቶች ያሟላል? የሚያሟላ ከሆነ ሁለት ሽማግሌዎች አንተ ባለህበት እንዲያነጋግሩት ዝግጅት ማድረግ ይቻል ዘንድ ለጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ ማሳወቅ አለብህ። ብቁ ከሆነ ሁለቱ ሽማግሌዎች በሕዝባዊ አገልግሎት መካፈል መጀመር እንደሚችል ይነግሩታል።
  • 19 በሚያዝያና በግንቦትስ:- እነዚህም በመስክ አገልግሎት ከፍተኛ እንቅስቃሴ የምናደርግባቸው ልዩ ወራት ይሆናሉ። በመጋቢት በረዳት አቅኚነት ያገለገሉ ብዙዎች በሚያዝያና በግንቦት ወይም ከሁለቱ ወራት በአንዱ አቅኚ ሆነው መቀጠል ይችሉ ይሆናል። በሚያዝያና በግንቦት በአገልግሎት ላይ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ቅድሚያ እንሰጣለን። እነዚህ መጽሔቶች በሚያነቧቸው ሰዎች ሕይወት ላይ እንዴት ያለ መልካም ውጤት አምጥተዋል! በመላው ዓለም አስደናቂ ጭማሪ እንዲገኝ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። በሚያዝያና በግንቦት መጽሔቶችን የቻልነውን ያህል ለብዙ ሰው ለማበርከት ልዩ ጥረት ይደረጋል። ሙሉ ተሳትፎ ለማድረግ አሁኑኑ እቅድ አውጡ።
  • 21 ብዙዎች በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ “መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ለማለት ይቻላል” በሚል ርዕስ የሚወጡትን አቀራረቦች ጠቃሚ ሆነው እንዳገኟቸው ገልጸዋል። ለናሙና የቀረቡትን መጽሔት ለማበርከት የሚረዱ አቀራረቦች በመለማመድ በዚህ ዝግጅት እየተጠቀማችሁ ነው? በየሳምንቱ ከቤተሰብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችሁ ላይ ጥቂት ጊዜ ወስዳችሁ ለምን እነዚህን አቀራረቦች አትለማመዱም?
  • 22 ይህን የመታሰቢያው በዓል ወቅት በሚገባ ተጠቀሙበት:- በዚህ ዓመት ለሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ወራት እንዲደረጉ በታቀዱት መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ሙሉ ተሳትፎ በማድረግ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ እኛም ‘የማይነገር ስጦታውን’ ምን ያህል እንደምናደንቅ ለይሖዋ እናሳይ። እነዚህም እንቅስቃሴዎች (1) ሐሙስ መጋቢት 28, 2002 በሚከበረው የዓመቱ ልዩ በዓል በሆነው የጌታ እራት ላይ መገኘትን፤ (2) አገልግሎት ያቆሙት ‘የቀደመውን ፍቅራቸው’ መልሰው እንዲያቀጣጥሉ እገዛ ማድረግን (ራእይ 2:4፤ ሮሜ 12:11)፤ (3) ልጆቻችንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ያልተጠመቁ አስፋፊ እንዲሆኑ መርዳትንና (4) በወንጌል ሰባኪነቱ ሥራ በተቻለ መጠን ሙሉ ተሳትፎ ማድረግን አልፎ ተርፎም በመጋቢትና በቀጣዮቹ ወራት ረዳት አቅኚ መሆንን ይጨምራሉ።​—⁠2 ጢ⁠ሞ. 4:​5
  • 23 በዚህ የመታሰቢያው በዓል ወራት ሁላችንም የመንግሥቱን ምሥራች በመስበኩ ሥራ ሙሉ ተሳትፎ በማድረግ ይሖዋ ላደረገልን ሁሉ ያለንን ጥልቅ አመስጋኝነት እንድናሳይ ልባዊ ጸሎታችን ነው።
  • ‘ምሥራቹን በሚገባ መሥክሩ’
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ዘንድሮም ጥሪውን ትቀበላላችሁን?—ለረዳት አቅኚነት በድጋሚ የቀረበ ጥሪ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ስለ ይሖዋ ድንቅ ሥራዎች መናገራችሁን ቀጥሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • 1,000 ረዳት አቅኚዎች ይፈለጋሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 2/02 ገጽ 3-6

‘የአምላክን ቃል በተሟላ ሁኔታ ስበኩ’

1 መልካም ነገር ሲደረግልህ ከልብህ የምታደንቅ ከሆነ አድናቆትህን በሁኔታህና በድርጊትህ አታሳይም? እንደምታሳይ ግልጽ ነው! ይሖዋ ለሰው ዘር ያሳየውን ጥሩነትና ፍቅራዊ ደግነት በተመለከተ ሐዋርያው ጳውሎስ ምን እንዳለ ልብ በል። “በቃላት ሊገለጽ ስለማይቻል ነፃ ስጦታው አምላክ ይመስገን” በማለት ተናግሯል። ይህ ‘ነፃ ስጦታ’ ምንን ይጨምራል? የተደረገልንን ‘ይገባናል የማንለውን የላቀ የአምላክ ደግነት’ በሙሉ የሚጨምር ሲሆን ይህ ደግነት በዋነኛነት የተገለጸው ለኃጢያታችን ቤዛ አድርጎ በሰጠን በልጁ ስጦታ በኩል ነው።​—⁠2 ቆ⁠ሮ. 9:14, 15 NW ፤ ዮሐ. 3:16

2 ጳውሎስ አመስጋኝነቱን የገለጸው እንዲያው በቃላት ብቻ ነበርን? በፍጹም! ጥልቅ አድናቆቱን በብዙ መንገዶች አሳይቷል። ስለ ክርስቲያን ባልደረቦቹ መንፈሳዊ ደህንነት ከልብ ያስብ የነበረ ከመሆኑም በላይ ከአምላክ ፍቅራዊ ደግነት ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለመርዳት የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ይፈልግ ነበር። ጳውሎስ ስለ እነዚህ ባልደረባዎቹ ሲናገር “እንዲሁም እያፈቀርናችሁ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለማካፈል ብቻ ሳይሆን የገዛ ነፍሳችንን ደግሞ እናካፍላችሁ ዘንድ በጎ ፈቃዳችን ነበረ፣ ለእኛ የተወደዳችሁ ሆናችሁ ነበርና” ብሏል። (1 ተ⁠ሰ. 2:8) ጳውሎስ የጉባኤው አባላት የሆኑት መዳናቸውን እንዲያጸኑ ከመርዳቱም በተጨማሪ ‘ለዘላለም ሕይወት የተዘጋጁ’ ሰዎችን ለማግኘት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በየብስም ሆነ በባህር ላይ በሺህ የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ ምሥራቹን ሰብኳል። (ሥራ 13:48) ጳውሎስ ይሖዋ ላደረገለት ሁሉ የነበረው ከልብ የመነጨ የአመስጋኝነት ስሜት ‘የአምላክን ቃል በተሟላ ሁኔታ እንዲሰብክ’ ገፋፍቶታል።​—⁠ቆላ. 1:25 NW 

3 ይሖዋ ላደረገልን ሁሉ ያለን አድናቆት በጉባኤያችን ውስጥ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው መንፈሳዊ እገዛ እንድናደርግላቸው አያነሳሳንም? (ገላ. 6:10) እንዲሁም በአገልግሎት ክልላችን ውስጥ የመንግሥቱን ምሥራች ከዳር እስከ ዳር በመስበኩ ሥራ በተቻለ መጠን ሙሉ ተሳትፎ ለማድረግ አንነሳሳም?​—⁠ማቴ. 24:14

4 አድናቆታችንን የምናሳይበት አጋጣሚ:- በየዓመቱ የሚከበረው የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ይሖዋና ኢየሱስ ላደረጉልን ነገር አመስጋኝነታችንን የምናሳይበት ልዩ አጋጣሚ ይከፍትልናል። ይህ እንዲያው የተለመደ ስብሰባ ወይም የአንድ ክንውን መታሰቢያ ብቻ አይደለም። ኢየሱስ “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” ብሏል። (ሉቃስ 22:19፣ በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።) የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ስለ ኢየሱስ ስብዕና የምናሰላስልበት ወቅት ነው። ለተከተለው የታማኝነት ጎዳናና ለከፈለው መሥዋዕትነት በአሁኑ ጊዜ ክብርና ንግሥና ተጎናጽፎ ሕያው ሆኖ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ የምናስታውስበት ወቅት ነው። እንዲሁም ይህ በዓል ክርስቶስ የክርስቲያን ጉባኤን ጉዳዮችና እንቅስቃሴዎች በበላይነት የሚቆጣጠር እንደመሆኑ መጠን ለራስነት ስልጣኑ እንደምንገዛ የምናሳይበት አጋጣሚ ነው። (ቆላ. 1:17-20) የአምላክ ሕዝቦች በሙሉ በክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ በአክብሮት መገኘት አለባቸው። በዚህ ዓመት በዓሉ ሐሙስ መጋቢት 28, 2002 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይከበራል።

5 ባለፈው ዓመት የመታሰቢያው በዓል ከመከበሩ አስቀድሞ ትጋት የተሞላበት ጥረት በመደረጉ በኢትዮጵያ 17,728 የደረሰ ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር ልናገኝ ችለናል። በዚህ ዓመት የተሰብሳቢው ቁጥር ምን ያህል ይሆን? ይህ የተመካው የተቻለንን ያህል ብዙ ሰዎች በበዓሉ እንዲገኙ ለመርዳት ‘በመጣራችን እና በመድከማችን’ ላይ ነው።​—⁠1 ጢ⁠ሞ. 4:10 አ.መ.ት

6 በጌታ እራት ላይ ከመገኘታችንም በተጨማሪ የመስክ አገልግሎት እንቅስቃሴያችንንም ከፍ ማድረግ እንችል ይሆናል። ብዙ ወንድሞችና እህቶች ለአንድ ወይም ከዚያ ለሚበልጡ ወራት በረዳት አቅኚነት እንደሚያገለግሉ ጥርጥር የለውም። ባለፈው ዓመት በመታሰቢያው በዓል ወቅት ማለትም ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት 2,611 ረዳት አቅኚዎች ነበሩን። በዚህ ዓመት በረዳት አቅኚነት የማገልገል መብት ለማግኘት ሁኔታዎችህን ማመቻቸት ትችላለህ? የአምላክ ፍቅራዊ ዝግጅት ለሆነው የክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት ያለህን ልባዊ አድናቆት የምታሳይበት ጥሩ አጋጣሚ ይሆንልሃል። የሚከተለው ተሞክሮ እንደሚያሳየው የይሖዋን በረከት እንደምታገኝ እርግጠኛ ልትሆን ትችላለህ።

7 የሙሉ ቀን ሰብዓዊ ሥራ የምትሠራ አንዲት እህት ባለፈው የመጋቢት ወር በረዳት አቅኚነት ስታገለግል ያጋጠማትን የሚከተለውን ተሞክሮ ጽፋልን ነበር:- “የየካቲት 2001 የመንግሥት አገልግሎታችን ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው ሁሉ በመታሰቢያው በዓል ወራት በረዳት አቅኚነት እንዲያገለግሉ አበረታቶ ነበር። መጋቢት አምስት ቅዳሜዎች ስለ ነበሩት ከፕሮግራሜ ጋር የሚስማማ ነበር። ስለዚህ ማመልከቻዬን ለማስገባት ወሰንኩ።” ወሩን ስትጀምር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ግብ አወጣች። ተሳክቶላት ይሆን? እንዴታ፤ 52 ሰዓት ካገለገለች በኋላ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አገኘች! ምን ብላ ደመደመች? “ተጨማሪ ጥረት ካደረግን አስደሳች የሆኑ በረከቶችን እናገኛለን።”

8 ቤተሰብ አንድ ላይ በአቅኚነት መካፈሉ ምን ጥቅሞችን ያስገኛል? አራት አባላት ባሉት አንድ ቤተሰብ ውስጥ ሁሉም በአቅኚነት በመካፈላቸው ያለፈውን የሚያዝያ ወር መቼም የማይረሳ ሆኖ አግኝተውታል። እናትየው እንዲህ ብላለች:- “አገልግሎቱ አንድ አድርጎን ስለነበር በእያንዳንዱ ቀን ደስተኞች ነበርን! ስለ ዕለታዊ የአገልግሎት እንቅስቃሴያችን የምናደርገው ጭውውት የእራት ሰዓታችን በጣም አስደሳች እንዲሆን አድርጎልናል።” ወንዱ ልጅ እንዲህ ብሏል:- “በሰብዓዊ ሥራው ምክንያት አባባ ሌላ ጊዜ በማይገኝባቸው የሳምንቱ ቀናት በመስክ አገልግሎት አብሬው መካፈል በመቻሌ በጣም ተደስቻለሁ።” አባትየውም እንዲህ ሲል አክሎ ተናግሯል:- “የቤተሰቡ ራስ እንደመሆኔ መጠን በጊዜያችን ከምንም ነገር ይበልጥ አጣዳፊ በሆነው እንቅስቃሴ በጋራ እየሠራን እንዳለን በማወቄ እርካታ አግኝቻለሁ።” ቤተሰባችሁ በአንድነት በአቅኚነት መካፈል ይችላል? ሁላችሁም በዚህ የመታሰቢያ በዓል ወራት በረዳት አቅኚነት መካፈል ትችሉ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ ለምን በቤተሰብ አትወያዩበትም?

9 በመጋቢት ከምንጊዜውም የበለጠ እንቅስቃሴ ማድረግ እንችል ይሆን? በ2000 መጀመሪያ ላይ የመንግሥት አገልግሎታችን “በሚያዝያ 2000 ከምንጊዜውም የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ እንችል ይሆን?” የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ምን ምላሽ ተገኘ? ብዙ አዳዲስ ከፍተኛ ቁጥሮች ተገኝተው ነበር። 1,495 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የረዳት አቅኚዎች ቁጥር ነበረ። በዚያ ልዩ ወር በታየው ከፍተኛ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ምክንያት በጉባኤያችሁ ውስጥ ተቀጣጥሎ የነበረውን የቅንዓት መንፈስ ታስታውሳላችሁ? በዚህ ዓመት ከዚህ ጋር የሚስተካከል ምናልባትም የበለጠ ሥራ ማከናወን እንችል ይሆን? ሁላችንም ከልብ ጥረት ካደረግን መጋቢት 2002 “ከምንጊዜውም የበለጠ እንቅስቃሴ የምናደርግበት” ወር ሊሆንልን ይችላል። ግን ለምን መጋቢት ተመረጠ?

10 መጋቢት ልዩ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ወር መሆን ያለበት በሁለት ምክንያቶች የተነሳ ነው። በመጀመሪያ፣ የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው በመጋቢት መጨረሻ አካባቢ ስለሆነ በወሩ መጀመሪያ ላይ በተቻለ መጠን ብዙ ሰው እንድንጋብዝ ሰፊ አጋጣሚ ይሰጠናል። ሁለተኛ በዚህ ዓመት የመጋቢት ወር አምስት ሙሉ ቅዳሜና እሁዶች ስላሉት ሰብዓዊ ሥራ የሚሠሩ ወይም ተማሪዎች የሆኑ ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል ቀላል ይሆንላቸዋል። ለምን በዚህ አባሪ ላይ የቀረበውን የቀን መቁጠሪያ በመጠቀም ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ፕሮግራም አታወጣም? ረዳት አቅኚነት አንተ ከምታስበው በላይ ቀላል ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ። ለምሳሌ ያህል፣ በአምስቱም ቅዳሜና እሁዶች በእያንዳንዳቸው 8 ሰዓት በመስክ አገልግሎት ለማሳለፍ ፕሮግራም ብታወጣ የሚፈለግብህን 50 ሰዓት ለማሟላት በቀሪዎቹ ቀናት ውስጥ ማገልገል የሚያስፈልግህ 10 ተጨማሪ ሰዓት ብቻ ይሆናል።

11 በጉባኤው ውስጥ ያሉት ሁሉ ‘የአምላክን ቃል በተሟላ ሁኔታ እንዲሰብኩ’ ለመርዳት ሽማግሌዎች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ? በስብሰባ ክፍሎችና በግል በምታደርጓቸው ጭውውቶች ቅንዓታቸውን ለመቀስቀስ ጣሩ። የመጽሐፍ ጥናት ቡድን መሪዎችና ረዳቶቻቸው ቅድሚያውን ወስደው በቡድናቸው ውስጥ የሚገኘውን እያንዳንዱን አስፋፊ ሊያነጋግሩና በግል ሊያበረታቱት ይችላሉ። ደግነት የተሞላባቸው ጥቂት የማበረታቻ ቃላት ወይም ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ የተወሰኑ ሐሳቦች ብቻ በቂ ሊሆኑ ይችላሉ። (ምሳሌ 25:11) ብዙዎች በፕሮግራማቸው ላይ መጠነኛ ማስተካከያ በማድረግ በረዳት አቅኚነት የማገልገል መብት ማግኘት እንደሚችሉ ይረዳሉ። በበርካታ ጉባኤዎች ውስጥ ያሉ ሽማግሌዎችና የጉባኤ አገልጋዮች እንዲሁም ሚስቶቻቸው፣ ሁሉም ለማለት ይቻላል በመታሰቢያው በዓል ወራት አብረው በረዳት አቅኚነት በማገልገል ግሩም ምሳሌ ሆነዋል። ይህም ብዙ አስፋፊዎችን እንደ እነሱ ረዳት አቅኚ እንዲሆኑ አበረታቷቸዋል። በአንዳንድ አካላዊ የአቅም ገደቦች ወይም በሌሎች ሁኔታዎች የተነሳ አንዳንድ አስፋፊዎች አቅኚ ሆነው ማገልገል አይችሉ ይሆናል፤ ቢሆንም ከሌሎች የጉባኤው አባላት ጋር አብረው ሆነው አቅማቸው የፈቀደውን ያህል በአገልግሎቱ በመካፈል አድናቆታቸውን እንዲያሳዩ ማበረታታት ይቻላል።

12 ሽማግሌዎች በሚገባ የታሰበበት እቅድ ካወጡ ጥሩ ውጤት ሊገኝ ይችላል። የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ በሳምንቱ ውስጥ ተስማሚ በሆኑ ሰዓቶች እንዲደረግ ፕሮግራም ሊወጣለት ይገባል። የሚቻል ከሆነ የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ሁሉንም የአገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች የሚመሩ ብቃት ያላቸው ወንድሞችን አስቀድሞ ይመድባል። እነዚህ ስብሰባዎች በቡድን መመደብን፣ የአገልግሎት ክልል መስጠትንና ጸሎትን ጨምሮ ከ10 እስከ 15 ደቂቃዎች እንዳይበልጡ ጥሩ ዝግጅት ያስፈልጋል። (በመስከረም 2001 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚገኘውን የጥያቄ ሣጥን ተመልከት።) የወሩ የአገልግሎት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ለጉባኤው በግልጽ መነገር እንዲሁም በማስታወቂያ ሰሌዳው ላይ መለጠፍ አለበት።

13 በቂ የአገልግሎት ክልል ሊኖር ይገባል። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ከክልል አገልጋዩ ጋር በመነጋገር በተደጋጋሚ ያልተሸፈኑ ክልሎችን ለመሸፈን ዝግጅቶችን ማድረግ አለበት። በቤታቸው የማይገኙ ሰዎችን ለማግኘት፣ ከመንገድ ወደ መንገድ እና ከሱቅ ወደ ሱቅ ለመመሥከር እንዲሁም በምሽት ምሥክርነት ለመካፈል ልዩ ጥረት ሊደረግ ይገባል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ አንዳንድ አስፋፊዎች በስልክ እንዲመሰክሩ ማበረታቻ መስጠት ይቻላል።

14 በድጋሚ በአገልግሎት መካፈል እንዲጀምሩ እርዷቸው:- በጉባኤያችሁ ክልል ውስጥ ምስራቹን በመስበኩ ሥራ መሳተፍ ያቆሙ አሉ? እንዲህ ዓይነቶቹ አሁንም የጉባኤው ክፍል ስለሆኑ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። (መዝ. 119:176) የዚህ አሮጌ ዓለም መጨረሻ በጣም ስለቀረበና በአዲሱ ዓለም ደፍ ላይ ስለምንገኝ አገልግሎት ያቆሙትን ለመርዳት የምንችለውን ሁሉ ጥረት ማድረጋችን የተገባ ነው። (ሮሜ 13:11, 12) በየዓመቱ ብዙዎች ለተደረገላቸው እርዳታ ምላሽ በመስጠት አገልግሎት ይጀምራሉ። ሌሎች ተጨማሪ አስፋፊዎች ቀደም ሲል ለአገልግሎቱ የነበራቸውን ፍቅርና ድፍረት መልሰው እንዲያቀጣጥሉ ለመርዳት ምን ማድረግ እንችላለን?​—⁠ዕብ. 3:12-14

15 የሽማግሌዎች አካል ባለፉት ጥቂት ዓመታት አገልግሎት አቁመው የነበሩትን እንዴት መርዳት እንደሚችል መወያየት ይፈልግ ይሆናል። (ማቴ. 18:12-14) የጉባኤው ጸሐፊ የጉባኤውን የአስፋፊዎች ካርድ በመመርመር አገልግሎት ያቆሙትን ሁሉ በማስታወሻ መመዝገብ አለበት። የእረኝነት ጉብኝት በማድረግ እነዚህን አስፋፊዎች ለመርዳት ልዩ ጥረት መደረግ አለበት። አንድ ሽማግሌ አገልግሎት ካቆመው ግለሰብ ጋር ጓደኝነት ወይም ቅርርብ የነበረው አንድ አስፋፊ ይህን ሰው እንዲረዳው ሊያደርግ ይችላል፤ ወይም ሌሎች አስፋፊዎች እንዲረዱት ሊጠይቅ ይችላል። ምናልባት አገልግሎት ያቆመውን አስፋፊ ያስጠኑት እነሱ ከሆኑ እርዳታ በሚፈልግበት በዚህ ወቅት የቅርብ እርዳታ ሊያደርጉለት መቻላቸው ያስደስታቸው ይሆናል። አገልግሎት ካቆሙት አስፋፊዎች ውስጥ ብዙዎቹ በድጋሚ የአምላክን ቃል መስበክ ለመጀመር እንደሚነሳሱ ተስፋ እናደርጋለን። ብቃቱን የሚያሟሉ ከሆኑ አገልግሎት ለመጀመር ከመታሰቢያው በዓል ወራት የተሻለ ጊዜ የለም!​—⁠ለተጨማሪ ማብራሪያ በኅዳር 2000 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ያለውን የጥያቄ ሣጥን ተመልከት።

16 ለአስፋፊነት ሊበቁ የሚችሉ ሌሎች ይኖሩ ይሆን? ይሖዋ ‘በአሕዛብ ሁሉ የተመረጡትን ዕቃዎች’ በማምጣት ሕዝቡን መባረኩን ቀጥሏል። (ሐጌ 2:7) በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ለመሆን ብቃቱን ያሟላሉ። እነዚህ እነማን ናቸው? የይሖዋ ምሥክሮች ልጆችና እድገት የሚያደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ናቸው። የምሥራቹ አስፋፊዎች ለመሆን ብቁ እንደሆኑና እንዳልሆኑ እንዴት ማወቅ እንችላለን?

17 የይሖዋ ምሥክሮች ልጆች:- ብዙ ልጆች ያልተጠመቁ አስፋፊ ባይሆኑም ለብዙ ዓመታት ከወላጆቻቸው ጋር ሆነው ከቤት ወደ ቤት ሲሄዱ ቆይተዋል። ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ለመሆን መጋቢት ጥሩ ጊዜ ሊሆንላቸው ይችላል። ልጅህ ብቁ እንደሆነና እንዳልሆነ እንዴት ታውቃለህ? አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት የተባለው መጽሐፍ በገጽ 100 ላይ “አንድ ልጅ በጠባዩ ጥሩ ምሳሌ ከሆነና ስለ ምሥራቹ ለሌሎች በመናገር እምነቱን ከራሱ በመነጨ ሐሳብ ለመግለጽ ከቻለ እንዲሁም ይህንን ከልቡ ተነሳስቶ ካደረገ” ብቁ እንደሆነ ይናገራል። ልጅህ ብቁ እንደሆነ ከተሰማህ የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ አባል የሆነ አንድ ሽማግሌ አነጋግር።

18 ለአስፋፊነት የሚበቁ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች:- አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እውቀት ካገኘና ለተወሰነ ጊዜ በስብሰባዎች ላይ ከተገኘ በኋላ የመንግሥቱ አስፋፊ መሆን ይፈልግ ይሆናል። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪህ ይህን ዓይነት ፍላጎት ካሳየ እነዚህን ጥያቄዎች አስብባቸው:- ከዕድሜውና ከችሎታው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ እድገት እያደረገ ነው? መደበኛ ባልሆነ መንገድ እምነቱን ለሌሎች ማካፈል ጀምሯል? “አዲሱን ሰው” እየለበሰ ነው? (ቆላ. 3:10) በአገልግሎታችን መጽሐፍ ገጽ 97-99 ላይ የተዘረዘሩትን ያልተጠመቀ አስፋፊ ለመሆን የሚያስፈልጉ ብቃቶች ያሟላል? የሚያሟላ ከሆነ ሁለት ሽማግሌዎች አንተ ባለህበት እንዲያነጋግሩት ዝግጅት ማድረግ ይቻል ዘንድ ለጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ ማሳወቅ አለብህ። ብቁ ከሆነ ሁለቱ ሽማግሌዎች በሕዝባዊ አገልግሎት መካፈል መጀመር እንደሚችል ይነግሩታል።

19 በሚያዝያና በግንቦትስ:- እነዚህም በመስክ አገልግሎት ከፍተኛ እንቅስቃሴ የምናደርግባቸው ልዩ ወራት ይሆናሉ። በመጋቢት በረዳት አቅኚነት ያገለገሉ ብዙዎች በሚያዝያና በግንቦት ወይም ከሁለቱ ወራት በአንዱ አቅኚ ሆነው መቀጠል ይችሉ ይሆናል። በሚያዝያና በግንቦት በአገልግሎት ላይ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ቅድሚያ እንሰጣለን። እነዚህ መጽሔቶች በሚያነቧቸው ሰዎች ሕይወት ላይ እንዴት ያለ መልካም ውጤት አምጥተዋል! በመላው ዓለም አስደናቂ ጭማሪ እንዲገኝ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። በሚያዝያና በግንቦት መጽሔቶችን የቻልነውን ያህል ለብዙ ሰው ለማበርከት ልዩ ጥረት ይደረጋል። ሙሉ ተሳትፎ ለማድረግ አሁኑኑ እቅድ አውጡ።

20 የስብከት እንቅስቃሴያችሁን ከፍ ለማድረግ እቅድ ካወጣችሁ በጉባኤው በኩል የምታገኟቸውን መጽሔቶች ቁጥር መጨመር ያስፈልጋችሁ ይሆን? የአገልግሎት ዓመቱን በሙሉ የመጽሔት ቀናችን በሆነው በቅዳሜ ቀን መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን እናበረክታለን። ይሁን እንጂ በዚህ ወቅት በረዳት አቅኚነት የሚካፈሉት ብዙ ስለሆኑና ሁላችንም ለሁለት ወር የምናበረክተው መጽሔቶችን ስለሆነ ከጉባኤው የምትወስዱትን የመጽሔት ቁጥር መጨመር ያስፈልጋችሁ ይሆናል። የሚያስፈልጋችሁ ከሆነ አሁኑኑ ለጉባኤያችሁ የመጽሔት አገልጋይ ንገሩት። በዚሁ ጊዜ የጉባኤው የጽሑፍ አገልጋይም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ለማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለው ትራክት በበቂ መጠን መኖሩን ማረጋገጥ አለበት።

21 ብዙዎች በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ “መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ለማለት ይቻላል” በሚል ርዕስ የሚወጡትን አቀራረቦች ጠቃሚ ሆነው እንዳገኟቸው ገልጸዋል። ለናሙና የቀረቡትን መጽሔት ለማበርከት የሚረዱ አቀራረቦች በመለማመድ በዚህ ዝግጅት እየተጠቀማችሁ ነው? በየሳምንቱ ከቤተሰብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችሁ ላይ ጥቂት ጊዜ ወስዳችሁ ለምን እነዚህን አቀራረቦች አትለማመዱም?

22 ይህን የመታሰቢያው በዓል ወቅት በሚገባ ተጠቀሙበት:- በዚህ ዓመት ለሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ወራት እንዲደረጉ በታቀዱት መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ሙሉ ተሳትፎ በማድረግ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ እኛም ‘የማይነገር ስጦታውን’ ምን ያህል እንደምናደንቅ ለይሖዋ እናሳይ። እነዚህም እንቅስቃሴዎች (1) ሐሙስ መጋቢት 28, 2002 በሚከበረው የዓመቱ ልዩ በዓል በሆነው የጌታ እራት ላይ መገኘትን፤ (2) አገልግሎት ያቆሙት ‘የቀደመውን ፍቅራቸው’ መልሰው እንዲያቀጣጥሉ እገዛ ማድረግን (ራእይ 2:4፤ ሮሜ 12:11)፤ (3) ልጆቻችንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ያልተጠመቁ አስፋፊ እንዲሆኑ መርዳትንና (4) በወንጌል ሰባኪነቱ ሥራ በተቻለ መጠን ሙሉ ተሳትፎ ማድረግን አልፎ ተርፎም በመጋቢትና በቀጣዮቹ ወራት ረዳት አቅኚ መሆንን ይጨምራሉ።​—⁠2 ጢ⁠ሞ. 4:​5

23 በዚህ የመታሰቢያው በዓል ወራት ሁላችንም የመንግሥቱን ምሥራች በመስበኩ ሥራ ሙሉ ተሳትፎ በማድረግ ይሖዋ ላደረገልን ሁሉ ያለንን ጥልቅ አመስጋኝነት እንድናሳይ ልባዊ ጸሎታችን ነው።

[ገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

እሁድ

ሰኞ

ማክሰኞ

ረቡዕ

ሐሙስ

ዓርብ

ቅዳሜ

ለመጋቢት 2002 የግል የመስክ አገልግሎት ፕሮግራም

የመጽሔት ቀን

የመጽሔት ቀን

የመጽሔት ቀን

የመጽሔት ቀን

የመታሰቢያው በዓል

ጸሐይ ከጠለቀች በኋላ

የመጽሔት ቀን

በመጋቢት ረዳት አቅኚ ለመሆን 50 ሰዓት ማገልገል የሚያስችል ፕሮግራም ልታወጣ ትችላለህ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ