የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/02 ገጽ 2
  • የጥያቄ ሳጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሳጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የጥያቄ ሳጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • አለባበሳችንና ውጫዊ ገጽታችን ሊያሳስበን የሚገባው ለምንድን ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ይምጡና ይጎብኙ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 6/02 ገጽ 2

የጥያቄ ሳጥን

◼ የቤቴል መኖሪያ ቤቶችንና ቢሮዎችን ስንጎበኝ ምን ዓይነት አለባበስና የፀጉር አያያዝ ሊኖረን ይገባል?

ለጉብኝት ወይም የቤቴል ቤተሰብ አባላትን ለመጠየቅ ወደ ቤቴል ስንመጣ “ልብሳችን፣ ፀጉራችንና ጠባያችን በመንግሥት አዳራሹ ወደሚደረገው ስብሰባ ለአምልኮ ስንሄድ እንድናሳየው ከሚጠበቅብን ጋር አንድ ዓይነት መሆን ይገባዋል።” (አገልግሎታችን 131) ይሁን እንጂ አንዳንድ ወንድሞችና እህቶች ቅርንጫፍ ቢሮውን ሲጎበኙ ለአለባበሳቸው ትኩረት እንደማይሰጡ ተስተውሏል። ወደ ቤቴል ስንመጣ በአለባበሳችን ረገድ ግድየለሽ መሆን የለብንም። አለባበሳችን ምሳሌ የሚሆን፣ ያልተዝረከረከ፣ ልከኛ እንዲሁም ከይሖዋ አምላክ አገልጋዮች የሚጠበቀውን ሥርዓታማነትና ክብር የሚያንጸባርቅ መሆን አለበት።​—⁠1 ጢ⁠ሞ. 2:9, 10

በተለይ የቤቴል መኖርያዎችንና ቢሮዎችን በምንጎበኝበት ጊዜ እንዲህ ማድረጋችን በጣም አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ለጉብኝት በምንመጣበት ጊዜ የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ በርካታ ሰዎች ይመለከቱናል። እነዚህ ሰዎች ከሚመለከቱት ነገር በመነሳት ስለ አምላክ ሕዝቦችና ስለ ድርጅቱ አንድ ዓይነት አመለካከት ሊይዙ ይችላሉ። ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችም ሆነ ቤቴልን ለሚጎበኙ ሌሎች ሰዎች በአለባበስና በፀጉር አያያዝ ረገድ ሥርዓታማ መሆን አስፈላጊ እንደሆነ ብትነግሯቸው መልካም ነው። በዚህ ረገድ ለምናደርገው ጥረት የቤቴል ቤተሰብ አመስጋኝ ነው።

ክርስቲያን አገልጋይ እንደመሆናችን መጠን በአለባበሳችን ሌሎችን እንዳናሰናክል መጠንቀቅ ይኖርብናል። (2 ቆ⁠ሮ. 6:3, 4) ከዚህ ይልቅ አለባበሳችንንና የጠጉር አያያዛችንን ክብር የተላበሰ በማድረግ ዘወትር “የአዳኛችን የእግዚአብሔር ትምህርት በነገር ሁሉ እንዲከበር” የምናደርግ እንሁን።​—⁠ቲቶ 2:10 የ1980 ትርጉም

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ