የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/02 ገጽ 8
  • ‘ከንቱ ነገርን’ ከመከታተል ተጠበቁ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ከንቱ ነገርን’ ከመከታተል ተጠበቁ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ወንጌል በኢንተርኔት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • በኢንተርኔት እንዳትጭበረበር ተጠንቀቅ!
    ንቁ!—2012
  • ኢንተርኔት​—ዓለም አቀፉን የመረጃ መረብ በጥበብ መጠቀም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • “ተላላ ቃልን ሁሉ ያምናል”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 9/02 ገጽ 8

‘ከንቱ ነገርን’ ከመከታተል ተጠበቁ

1 በዛሬው ጊዜ በስፋት ከተለመዱት የመገናኛ ዘዴዎች መካከል አንዱ በኮምፒውተር አማካኝነት የሚደረገው የመልእክት ልውውጥ (E-mail) ነው። በዚህ የመገናኛ ዘዴ ተጠቅሞ የግል ገጠመኞችንና ሐሳቦችን ከወዳጅ ዘመድ ጋር መለዋወጡ ተገቢ ቢሆንም ገደብ የለሽ የኤሌክትሮኒክ መልእክት ልውውጥ እንደ ‘ከንቱ ነገር’ ተደርጎ ሊቆጠር የሚችለው እንዴት ነው?​—⁠ምሳሌ 12:11

2 በኮምፒውተር የሚደረግ የመልእክት ልውውጥን በሚመለከት ጠንቃቃ መሆን:- አንዳንዶች ትኩስ ወሬ ነው ብለው የሚያስቡት ነገር በኤሌክትሮኒክ መልእክት መለዋወጫ ዘዴ ሲደርሳቸው ከይሖዋ ድርጅት ጋር ይበልጥ የተቀራረቡ ሆነው ይሰማቸዋል። ይህ ትኩስ ወሬ ተሞክሮዎችን፣ በቤቴል የተፈጸሙ ክንውኖችን፣ ስለ ተፈጥሮ አደጋዎች ወይም ስለ ስደት የሚናገሩ ዘገባዎችን አልፎ ተርፎም በመንግሥት አገልግሎት ትምህርት ቤቶች ላይ የተነገሩ ምስጢር ነክ ጉዳዮችን የሚጨምር ሊሆን ይችላል። ሌሎች ደግሞ እንዲህ ዓይነት ወሬዎችን ማንም ሳይቀድማቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ለመንገር ከመጠን በላይ የሚጓጉ ይመስላል።

3 አንዳንድ ጊዜ መረጃዎችና ተሞክሮዎች ይዘታቸው ተዛብቶ ወይም ከመጠን በላይ ተጋንኖ ይነገራሉ። እንዲህ ዓይነት ወሬዎችን ለሌሎች ለመናገር የሚጣደፉ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ስለነገሩ የተሟላ መረጃ አይኖራቸውም። (ምሳሌ 29:20) እንዲህ ዓይነት የተዛባ ወይም ሌሎችን የሚያሳስት ወሬ ‘ከተረት’ ተለይቶ አይታይም። ይህም ለአምላክ ከማደር ባሕርይ ጋር የሚስማማ አይደለም። (1 ጢ⁠ሞ. 4:6, 7) የተሳሳተ ወሬ ለሌሎች ብታስተላልፍ በዚህ ሳቢያ ለሚደርሰው ሐዘንም ሆነ ግራ መጋባት ኃላፊነቱን የምትወስደው አንተ ነህ። ወንድሞቻችንን የሚያሳስት ወይም ተስፋ ቆርጠው ወደ ኋላ እንዲሉ የሚያደርግ ነገር ማድረግ እንደማንፈልግ የተረጋገጠ ነው።

4 አምላክ የሚጠቀምበት የሐሳብ ማስተላለፊያ መስመር:- ሰማያዊው አባታችን ሐሳቡን ለማስተላለፍ “ታማኝና ልባም ባሪያን” እንደ መሣሪያ አድርጎ እንደሚጠቀምበት ማስታወስ ይኖርብናል። ይህ “ባርያ” ለእምነት ቤተሰቦች ምን ዓይነት መረጃ መቅረብ እንዳለበትና መረጃው መገለጽ ያለበት ‘ተገቢ ጊዜ’ መቼ እንደሆነ የመወሰን ኃላፊነት ተሰጥቶታል። ይህ መንፈሳዊ ምግብ የሚቀርበው በቲኦክራሲያዊው ድርጅቱ በኩል ብቻ ነው። አስተማማኝ መረጃ ለማግኘት መጠበቅ ያለብን አምላክ ከሚጠቀምበት የሐሳብ ማስተላለፊያ መሥመር እንጂ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ከሚያዘጋጁት የመረጃ አውታር አይደለም።​—⁠ማቴ. 24:45

5 የኢንተርኔት ዌብ ገጾች (Web Sites):- www.watchtower.org የተባለ የራሳችን የኢንተርኔት የዌብ ገጽ አለን። ይህ የዌብ ገጽ ለሕዝብ በቂ የሆነ መረጃ ይዟል። ስለዚህ የትኛውም ግለሰብ፣ ኮሚቴ ወይም ጉባኤ የይሖዋ ምሥክሮችን የሚመለከት የኢንተርኔት ዌብ ገጽ ማዘጋጀት አያስፈልገውም። በተጨማሪም ለትርፍ ማግኛም ሆነ እንዲሁ በነጻ ለማደል በይሖዋ ምሥክሮች የሚዘጋጁ ጽሑፎችን በኤሌክትሮኒክ ፋይሎች ማባዛትም ሆነ ማሰራጨት የባለቤትነት መብት ሕጎችን መጣስ ነው። አንዳንዶች እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት ወንድሞችን ለመጥቀም ሲባል የሚደረግ እንደሆነ አድርገው ቢያስቡም ተቀባይነት ስለሌለው ከአሁን በኋላ እንዲህ ያለው ልማድ መቀጠል አይኖርበትም።

6 በኤሌክትሮኒክ መልእክት መለዋወጫ ዘዴዎች አጠቃቀማችን ረገድ ጥሩ የማመዛዘን ችሎታና ጤናማ አስተሳሰብ መያዛችን አእምሮአችን “ከከበረውና ካማረው ሀብት” እንዲሞላ ያደርጋል።​—⁠ምሳሌ 24:4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ