የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/03 ገጽ 5
  • መልካም በማድረግ ምሳሌ ሁኑ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መልካም በማድረግ ምሳሌ ሁኑ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘ሁልጊዜ መልካም ለማድረግ ትጉ’
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • “በአሕዛብ መካከል መልካም ምግባር ይዛችሁ ኑሩ”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • በምግባራችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ይሖዋን በከፍተኛ ጉጉት ተጠባበቁ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 7/03 ገጽ 5

መልካም በማድረግ ምሳሌ ሁኑ

1. በአውራጃ ስብሰባ ላይ ለምግባራችን ልዩ ትኩረት መስጠት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?

1 በአውራጃ ስብሰባዎች ላይ በርከት ብለን በምንሰበሰብበት ጊዜ የምናደርጋቸው ነገሮችና ሌሎችን የምንይዝበት መንገድ ለታዛቢዎች ይበልጥ በግልጽ ይታያል። በመሆኑም እያንዳንዳችን ጤናማ አስተሳሰብ በመያዝ “በነገር ሁሉ መልካምን በማድረግህ ምሳሌ የሚሆን ራስህን አሳይ” ለሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ልዩ ትኩረት መስጠት ይኖርብናል። (ቲቶ 2:​6, 7) ‘ለራሳችን የሚጠቅመንን ብቻ ሳይሆን ለባልንጀራችን የሚጠቅመውን መመልከት’ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ሊጠይቅብን ይችላል። (ፊልጵ. 2:​4) በቅርቡ በምናደርገው “ለአምላክ ክብር ስጡት” በተባለው የአውራጃ ስብሰባ ላይ ይህን ማበረታቻ በሥራ የምናውልባቸውን አንዳንድ መስኮች እስቲ እንመልከት።

2, 3. ልጆች ይሖዋን ማስመስገን የሚችሉት እንዴት ነው? በዚህ ረገድ ወላጆች ምን ኃላፊነት አለባቸው?

2 ወላጆችና ልጆች:- ብዙ ወጣቶች ጥሩ ሥነ ምግባር በማያሳዩበት በዚህ ዓለም ውስጥ ልጆቻችን የተለዩ መሆናቸው ይሖዋንና ድርጅቱን ያስመሰግናል። አንዳንድ ጊዜ ግን ልጆች ተገቢ ቁጥጥር ሳይደረግላቸው በመቅረቱ ምክንያት ችግሮች ተፈጥረዋል። (ምሳሌ 29:​15) ወላጆች በሚያርፉበት ቦታም ሆነ በአውራጃ ስብሰባው ላይ ልጆ​ቻቸውን ብቻቸውን መልቀቅ የለባቸውም።

3 አንዳንድ ወላጆች በአውራጃ ስብሰባው ወቅት ልጆቻቸው ምን ዓይነት ጠባይ ማሳየት እንዳለባቸው ጊዜው ከመድረሱ በፊት መወያየቱን ጠቃሚ ሆኖ አግኝተውታል። (ኤፌ. 6:​4) እውነተኛ ክርስቲያናዊ ፍቅር ‘የማ​ይገባውን እንደማያደርግና የራሱን ጥቅም እንደማይፈልግ’ ልጆቻቸውን ያስረዷቸዋል። (1 ቆ⁠ሮ. 13:​5) የአውራጃ ስብሰባው ከይሖዋ የምንማርበት ጊዜ በመሆኑ ልጆችም ሆኑ አዋቂዎች በስብ​ሰባው ቦታና በሌሎች ቦታዎችም በሚያሳ​ዩት ጠባይ ለዚህ ዝግጅት ያላ​ቸውን አክብሮት መግለጽ ይችላሉ።​—⁠ኢሳ. 54:​13

4. መልካም ጠባያችን በሌሎች ላይ ምን ውጤት ሊኖረው ይችላል?

4 መልካም ምግባራችን ሰዎች ያላቸውን የተሳሳተ አመለካከት ለማስተካከልና ወደ እውነተኛው አምልኮ ለመሳብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል። (ማቴ. 5:​16፤ 1 ጴ⁠ጥ. 2:​12) በአውራጃ ስብሰባችን ላይ ለምናገኛቸው ሰዎች ሁሉ በድርጊታችንና እነርሱን በምንይዝበት መንገድ መልካም ምሥክርነት እንስጥ። በዚህ መንገድ ‘መልካም በማድረግ ምሳሌ ሆነን’ የምንገኝ ከመሆኑም በላይ የይሖዋን ስም እናስከብራለን።​—⁠ቲቶ 2:​7

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ