የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/04 ገጽ 9
  • በምግባራችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በምግባራችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “በአሕዛብ መካከል መልካም ምግባር ይዛችሁ ኑሩ”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • በመንፈሳዊ የምንታደስበት የሦስት ቀን ስብሰባ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • ይሖዋን በከፍተኛ ጉጉት ተጠባበቁ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • መልካም በማድረግ ምሳሌ ሁኑ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 8/04 ገጽ 9

በምግባራችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ

1 ቅዱስ የሆነው አምላክ የይሖዋ አገልጋዮች እንደመሆናችን በኑሯችን ሁሉ ቅዱሳን ለመሆን ጥረት እናደርጋለን። (1 ጴ⁠ጥ. 1:​15, 16) ይህም ሲባል በሁሉም የሕይወታችን ዘርፎች የይሖዋን የአቋም ደረጃዎች ተግባራዊ እናደርጋለን ማለት ነው። በዚህ ዓመት የሚደረገው የአውራጃ ስብሰባ ቅዱስ ምግባር ለማሳየት የምንችልበት ጥሩ አጋጣሚ ይሰጠናል።

2 እባካችሁ በመኪና ማቆሚያ ቦታውም ሆነ በአዳራሹ ውስጥ አስተናጋጆች የሚሰጧችሁን መመሪያ ተግባራዊ አድርጉ። (ዕብ. 13:​17) ቤተሰቦች አንድ ላይ መቀመጥ አለባቸው። ወላጆች በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኙትንም ጨምሮ ልጆቻቸው ከሌሎች ወጣቶች ጋር በቡድን ሆነው እንዲቀመጡ ሊፈቅዱ አይገባም። ማንኛውንም የመቅረጫ መሣሪያ በመሰብሰቢያው ቦታ ካለው የኤሌክትሪክ መሥመር ወይም የድምጽ መሣሪያ ጋር ማገናኘት የማይቻል ከመሆኑም በላይ በእነዚህ መሣሪያዎች ስንጠቀም ሌሎችን ላለመረበሽ መጠንቀቅ አለብን። ፎቶግራፍ ማንሳት ከፈለጋችሁ ስብሰባው እየተካሄደ ፍላሽ መጠቀም አይኖርባችሁም። ሞባይል ስልኮች የሌሎችን ትኩረት እንዳይሰርቁ መጠንቀቅ ይኖርብናል። ወላጆች ልጆቻቸው ይሖዋን የሚያስከብር ምግባር እንዲኖራቸው ሊከታተሏቸው ይገባል እንጂ እንደፈለጉ እንዲሆኑ መልቀቅ የለባቸውም።​—⁠ምሳሌ 29:15

3 ምግባራችን ከሌሎች ተለይተን እንድንታወቅ የሚያደርገን ከመሆኑም በላይ አምላካችንን ያስከብራል። (1 ጴ⁠ጥ. 2:​12) በአውራጃ ስብሰባው ላይ ሰዎች ምግባራችንን ይመለከታሉ። እንግዲያው በምታደርጉት ሁሉ ቅዱሳን ለመሆን ቁርጥ ውሳኔ አድርጉ።

[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]

1. በኑሯችን ሁሉ ቅዱሳን መሆናችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

2. በአውራጃ ስብሰባው ላይ ጥሩ ምግባር ማሳየት ምን ነገሮችን ያካትታል?

3. በአውራጃ ስብሰባዎች ላይ ምግባራችን አምላክን የሚያስከብረው እንዴት ነው?

[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ የሥዕል መግለጫ]

ቅዱስ ምግባር ይኑራችሁ

◼ ልጆቻችሁ ከዓይናችሁ አይራቁ

◼ ለሌሎች አሳቢነት አሳዩ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ