የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/04 ገጽ 3
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሰዓት መጠበቅና ጊዜን ማመጣጠን
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ትክክለኛ መደምደሚያና የጊዜ አመዳደብ
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • ስብሰባዎችን በሰዓቱ ጀምራችሁ በሰዓቱ ጨርሱ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ለአገልግሎት ስብሰባ መዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 1/04 ገጽ 3

የጥያቄ ሣጥን

◼ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ የተመደበልንን ሰዓት ማክበር የምንችለው እንዴት ነው?

ከወዳጆቻችን ጋር አንድ አስደሳች ነገር በምንጫወትበት ጊዜ ሰዓቱ ሳናስበው ይሄዳል። በዚህም ምክንያት በጉባኤ የሚቀርቡ ክፍሎችን በተመደበላቸው ሰዓት መጨረስ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ክፍሎቹን በሰዓታቸው ለማጠናቀቅ ምን ማድረግ እንችላለን?

በሰዓቱ ጀምሩ። በጉባኤ ስብሰባ ወቅት ፕሮግራሙ የሚጀመርበት ሰዓት ከመድረሱ አንድ ወይም ሁለት ደቂቃ ቀደም ብሎ አድማጮች ቦታ ቦታቸውን እንዲይዙ በመጋበዝ ስብሰባው ልክ በሰዓቱ በሥርዓት እንዲጀመር ማድረግ ይቻላል። (መክ. 3:1) እንደ መስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ባሉ በትናንሽ ቡድኖች በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ አርፍደው የሚመጡ ወንድሞችን ለመጠበቅ ሲባል ዘግይቶ መጀመር አያስፈልግም።

በሚገባ ተዘጋጅ። ክፍሉን በሰዓቱ ለመሸፈን የሚረዳው አንዱ ቁልፍ ነገር አስቀድሞ መዘጋጀት ነው። የክፍሉ ዓላማ በግልጽ ይግባህ። ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች ለይተህ አውጣ፤ ትምህርቱን ስታቀርብ እነዚህን ነጥቦች አጉላ። እምብዛም አስፈላጊ ባልሆኑ ዝርዝር ጉዳዮች ትኩረትህ እንዳይወሰድ ተጠንቀቅ። አቀራረብህ ቀላል ይሁን። ክፍሉ ሠርቶ ማሳያዎችንና ቃለ ምልልሶችን የሚያካትት ከሆነ አስቀድማችሁ ተለማመዱ። በተቻለህ መጠን ሰዓትህን እየተቆጣጠርክ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ተለማመድ።

ትምህርቱን ከፋፍለው። ክፍሉ በንግግር የሚቀርብም ሆነ ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት ትምህርቱን መከፋፈሉ ጠቃሚ ነው። በእያንዳንዱ ክፍል ላይ ምን ያህል ጊዜ እንደምታሳልፍ ከወሰንክ በኋላ ደቂቃውን በማስታወሻህ ኅዳግ ላይ ጻፍ። ከዚያም ትምህርቱን በምታቀርብበት ጊዜ በሰዓትህ እየሄድክ መሆኑን ተመልከት። ትምህርቱ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ ከሆነ አድማጮች በመግቢያው አንቀጾች ላይ ብዙ ሐሳብ እንዲሰጡ በመፍቀድ በኋላ ላይ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነውን ክፍል በጥድፊያ ለመሸፈን እንዳትገደድ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብሃል። የመጠበቂያ ግንብ ጥናት የሚመሩ ወንድሞች በክለሣ ሣጥኑ ላይ ለመወያየት በቂ ጊዜ ማስቀረት ይኖርባቸዋል። ከዚህም በላይ ለመደምደሚያ መዝሙርና ጸሎት የተመደበውን ሰዓት እንዳይወስዱ መጠንቀቅ አለባቸው።

በሰዓቱ ጨርሱ። እንደ አገልግሎት ስብሰባ ያለ ከአንድ በላይ ክፍሎች የሚቀርቡበት ስብሰባ ላይ እያንዳንዱ ተናጋሪ ክፍሉ የሚጀምርበትንና የሚያበቃበትን ሰዓት ሊያውቅ ይገባል። አንዳንዶቹ ክፍሎች ከተመደበላቸው ሰዓት በላይ ቢወስዱስ? ሌሎቹን ክፍሎች የሚያቀርቡት ወንድሞች ዝርዝር ሐሳቦችን ትተው በዋና ዋናዎቹ ነጥቦች ላይ በማተኮር ሰዓቱን ማካካስ ይችላሉ። ይህን ማድረግ መቻል ጥሩ ልምድ ያለው አስተማሪ መለያ ነው።

በስብሰባው ላይ የተገኘን አድማጮችም አጠር ያሉና ነጥቡ ላይ ያተኮሩ መልሶች በመስጠት ትምህርቱን የሚመራውን ወንድም ልንደግፈው እንችላለን። እንግዲያው ሁላችንም ስብሰባው “በአግባብና በሥርዐት” እንዲካሄድ አስተዋጽኦ ማድረግ እንችላለን።​—⁠1 ቆ⁠ሮ. 14:40

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ