የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/04 ገጽ 5
  • ልከኛና የሚያስከብር አለባበስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ልከኛና የሚያስከብር አለባበስ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አለባበሳችንና ውጫዊ ገጽታችን ሊያሳስበን የሚገባው ለምንድን ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ሥርዓታማ አለባበሳችን ለአምላክ አክብሮት እንዳለን ያሳያል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • በታላቅ ጉባኤ መካከል ይሖዋን አመስግኑ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • አለባበሳችሁ አምላክን ያስከብራል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 8/04 ገጽ 5

ልከኛና የሚያስከብር አለባበስ

1 “እንደ የይሖዋ ምሥክሮች ያለ ማንም የለም! ሰዎቻችሁ ጥሩ አለባበስ ያላቸው ከመሆናቸውም በላይ ደግና ለሌሎች ጥልቅ አክብሮት ያላቸው ናቸው።” ባለፈው ዓመት በተደረገ አንድ የአውራጃ ስብሰባ ላይ ስለተገኙ ወንድሞችና እህቶች እንዲህ በማለት የተናገረው የአንድ ሆቴል ኃላፊ ነበር። በሌላ የአውራጃ ስብሰባ ላይ ደግሞ አንዲት የሆቴል ሠራተኛ “በአለባበሳችሁ አምላክን ለማስደሰት እንደምትፈልጉ በግልጽ ይታያል” ብላለች። አዎን፣ በአውራጃ ስብሰባ ላይ ለመገኘት የሚመጡ ልዑካን የሰዎችን ትኩረት ይስባሉ። በመሆኑም አለባበሳችን ‘ለወንጌል እንደሚገባ’ እንዲሆን የምንፈልግ ሲሆን ይህም አብዛኛውን ጊዜ የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ ሰዎች ስለ እኛ አዎንታዊ አስተያየቶችን እንዲሰነዝሩና የአምላክ አገልጋዮች መሆናችንን እንዲገነዘቡ ያደርጋቸዋል። (ፊልጵ. 1:27) በአውራጃ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ስንዘጋጅ ስለ አለባበሳችን አስቀድመን ልናስብበት ይገባል።

2 ደቀ መዝሙሩ ያዕቆብ “ከሰማይ የሆነችው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት” በማለት ጽፏል። (ያዕ. 3:17) አለባበሳችን ልከኛ እንዲሆን ማድረግ ፈታኝ ሊሆን ይችላል። ምግባረ ብልሹ የሆነው የሰይጣን ዓለም ሰዎች ልከኛ ያልሆኑ፣ የጾታ ስሜትን የሚያነሳሱና ከተለመደው ያፈነገጡ የአለባበስ ዘይቤዎችን እንዲከተሉ ተጽዕኖ ያሳድራል። (1 ዮሐ. 2:15-17) በመሆኑም አለባበስንና አጋጌጥን የሚመለከቱ ውሳኔዎችን ስናደርግ “በኀጢአት መኖርንና ዓለማዊ ምኞትን ክደን፣ በአሁኑ ዘመን ራሳችንን በመግዛት . . . እንድንኖር” የሚያዘውን የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር መከተል ያስፈልገናል። (ቲቶ 2:12) ወንድሞቻችንም ሆኑ የሆቴል ወይም የምግብ ቤት ሠራተኞች አሊያም ሌሎች ተመልካቾች በአለባበሳችን ቅር እንዲሰኙ እንደማንፈልግ የታወቀ ነው።​—⁠1 ቆ⁠ሮ. 10:32, 33

3 ጨዋነት የሚንጸባረቅበት ልከኛ ልብስ፦ ለአውራጃ ስብሰባ ስትዘጋጁ እንዲህ እያላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ:- ‘አለባበሴ ልከኛ ነው? ወይስ ከልክ በላይ የሰዎችን ትኩረት ይስባል? ለሌሎች ስሜት እንደማስብ ያሳያል? ሸሚዜ የአንገቱ ቅድ በጣም የወረደና ደረትን የሚያጋልጥ ወይም ቁመቱ በማጠሩ የተነሳ እምብርትን የሚያሳይ ነው? ቀሚሴ ሰውነቴን የሚያሳይ ወይም ጥብቅ ያለ ነው? ልብሶቼ ንጹሕና ከመጥፎ ሽታ የጸዱ ናቸው? ከስብሰባው ውጪ ባለው ሰዓት የምለብሰው ልብስ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ምሥክርነት ለመስጠት እንዳፍር ያደርገኛል?’​—⁠ሮሜ 15:2, 3፤ 1 ጢ⁠ሞ. 2:9

4 በመንፈሳዊ የጎለመሱ ክርስቲያኖች አስተያየት እንዲሰጡን መጠየቅ እንችላለን። ሚስቶች አለባበሳቸው በሌሎች ላይ ምን ስሜት እንደሚያሳድር ባሎቻቸውን ሊጠይቁ ይችላሉ። ክርስቲያን ወላጆች በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ልጆቻቸውን በዚህ ረገድ ሊረዷቸው ይችላሉ። ከዚህም በላይ በጉባኤው ውስጥ ያሉ የተከበሩ አረጋውያን እህቶች “የእግዚአብሔር ቃል በማንም ዘንድ እንዳይሰደብ” ወጣት ሴቶች በአለባበሳቸው “ራሳቸውን የሚገዙና ንጹሓን” እንዲሆኑ ሊመክሯቸው ይችላሉ። (ቲቶ 2:3-5) በጽሑፎቻችን ላይ ልከኛና ጨዋነትን የሚያንጸባርቁ አለባበሶችን የሚያሳዩ ጠቃሚ ሥዕሎች ወጥተዋል።

5 ለይሖዋ ውዳሴ የሚያመጣ ይሁን፦ የአውራጃ ስብሰባዎች በፕሮግራሙ ላይ ክፍል ላላቸው ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም ይሖዋን የምናወድስበት ግሩም አጋጣሚ ይሰጡናል። ክርስቲያናዊ ምግባራችንና አነጋገራችን እንደሚያስከብረው የታወቀ ነው። ሆኖም በርካታ ታዛቢዎች በመጀመሪያ የሚያስተውሉት አለባበሳችንንና አጋጌጣችንን ነው። ሁላችንም ንጹሕና የሚያስከብር ልብስ በመልበስ ለይሖዋ ውዳሴ እናምጣ።​—⁠መዝ. 148:12, 13

[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]

1. ለአውራጃ ስብሰባ ስንዘጋጅ ለአለባበሳችን ትኩረት መስጠት ያለብን ለምንድን ነው?

2. አለባበሳችን ልከኛ እንዲሆን ማድረግ ፈታኝ የሆነው ለምንድን ነው?

3. የትኞቹ ጥያቄዎች አለባበሳችንን ለመመርመር ይረዱናል?

4. አለባበሳችን ጨዋነትን የሚያንጸባርቅ እንዲሆን ሌሎች ሊረዱን የሚችሉት እንዴት ነው?

5. በአውራጃ ስብሰባዎች ላይ ሁላችንም ለይሖዋ ውዳሴ ማምጣት የምንችለው እንዴት ነው?

[በገጽ 5 ላይ የሚገኝ የሥዕል መግለጫ]

አለባበሳችን የሚያስከብር እንዲሆን የሚረዱን ነጥቦች

◼ የአምላክ ቃል

◼ ራሳችን አለባበሳችንን መመርመር

◼ የሌሎች አስተያየት

◼ በክርስቲያናዊ ጽሑፎች ላይ የሚወጡ አለባበሶች

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ