ደም አልወስድም—የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል ከተባለው ፊልም ተጠቀሙ
ያለ ደም በሚሰጥ ሕክምና መስክ ስላሉት አማራጮች ምን ያህል ግንዛቤ አለህ? ያለ ደም ሕክምና ማድረግ የሚቻልባቸውን ዘዴዎችና እነዚህም ዘዴዎች እንዴት እንደሚሠሩ ታውቃለህ? ይህን የቪዲዮ ፊልም ተመልከትና በሚከተሉት ጥያቄዎች አማካኝነት እውቀትህን ፈትሽ።—ማሳሰቢያ:- ቪዲዮው ቀዶ ሕክምና ሲደረግ የሚያሳዩ ክፍሎች ስላሉት ወላጆች ትናንሽ ልጆች ፊልሙን ሊያዩት ይገባ እንደሆነና እንዳልሆነ አመዛዝነው መወሰን ይኖርባቸዋል።
(1) የይሖዋ ምሥክሮች ደም የማይወስዱበት ዋነኛ ምክንያት ምንድን ነው? ይህ መሠረታዊ መመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የት ቦታ ላይ ይገኛል? (2) በሕክምና ረገድ ፍላጎታችን ምንድን ነው? (3) ታካሚዎች ምን መሠረታዊ መብት አላቸው? (4) አንድ ሰው ደም አልወስድም ማለቱ አስተዋይ አይደለም ወይም ኃላፊነት አይሰማውም ሊያሰኘው የማይችለው ለምንድን ነው? (5) ከባድ የሆነ የደም መፍሰስ ሲያጋጥም ሐኪሞች ሊያከናውኗቸው የሚገቡ ሁለት ተቀዳሚ ተግባራት የትኞቹ ናቸው? (6) ደም መውሰድ ሊያስከትላቸው የሚችሉ አንዳንድ የጤና ችግሮች ምንድን ናቸው? (7) ሐኪሞች በቀዶ ሕክምና ወቅት ብዙ ደም እንዳይፈስ ለማድረግ እንዴት ባሉ ዘዴዎች ሊጠቀሙ ይችላሉ? (8) ማንኛውንም በደም ምትክ የሚሰጥ ሕክምና በሚመለከት ሕመምተኞች ማወቅ ያለባቸው ነገር ምንድን ነው? (9) ደም ሳይሰጥ ከባድ የሆኑና የተወሳሰቡ ቀዶ ሕክምናዎችን ማድረግ ይቻላል? (10) ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ የሕክምና ባለሞያዎች ለይሖዋ ምሥክሮች ምን ለማድረግ ፈቃደኛ ሆነዋል? ውሎ አድሮ ለሁሉም ታካሚዎች ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው የሕክምና ዘዴ የትኛው ነው?
በቪዲዮው ላይ የቀረበውን ማንኛውንም ዓይነት የሕክምና አማራጭ ለመቀበል የሚደረገው ውሳኔ ለእያንዳንዱ ግለሰብ ሕሊና የተተወ ነው።—መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 15, 2004 ገጽ 22-24, 29-31 እና ጥቅምት 15, 2000 ገጽ 30-31 ላይ የወጣውን ሐሳብ ተመልከት።